ታሪኮች

47338

የካይሮ የውሀ ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ ሊዘጋጅ ነው

  ግብጽ ከ53 ሀገሮች የተውጣጡ የውሀ ባለሞያዎች የሚሳተፉበትን ‹‹የካይሮ የውሀ ሳምንት›› ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ ነው፡፡ በፈረንጆቹ ወር ከኦክቶበር 14-18 ቀን በውሀ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውን ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስፖንሰር ማድረጋቸውን የሀገሪቱ የውሀ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር የእቅድ ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት ሰይድ አህመድ አስታውቀዋል፡፡
By:
somali

በሶማሌ ክልል በጎርፍ ምክንያት 98 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ

በሚያዝያ ወር በተደረገ ጥናት በሶማሌ ክልል በሸበሌ ዞን 165 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች በጎርፍ መጠቃታቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ 98 ሺሕ ያህል ሰዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በዚህ ሳምንት በወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት፣ በክልሉ በተከሰተው ጎርፍ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ አምስት ሺሕ ቤቶች መውደማቸውን፣ በሸበሌ ዞን የሚገኙ 72 ትምህርት ቤቶችና 63 የጤና ተቋማት […]
By:
222

የአፍሪካ ከተሞች በ2050 የካርቦን ልቀት መጠንን ዜሮ ለማድረስ ወስነዋል

በዚህ ሳምንት በናይጄሪያ በተካሔደ ስብሰባ ዘጠኝ የአፍሪካ ከተሞች በአውሮፓ አቆጣጠር በ2050 የካርቦን ልቀት መጠንን ዜሮ ለማድረስ ወስነዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሶስት አስርት አመታት የካርቦን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ቁርጠኛ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች መካከል አዲስ አበባም ትገኛለች፡፡ የደቡብ አፍሪካዎቹ ኬፕታውን እና ጆሀንስበርግ፣ የጋናዋ አክራ እና የናይጄሪዋ ላጎስ ከተማ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
By:
ttt2

በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የተደረገው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል

በቆንጂት ተሾመ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የተካሔደው ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ፡፡ ለ12 ሰአታት የተካሔደው ስብሰባ ሲጠናቀቅ የሶስቱ ሀገሮች ተወካዮች እንደገለጹት ሀገሮቹ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቀጣይ አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
By:
033 1

የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ታገደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ሚድሮክ ጎልድ በለገደምቢ በሚያካሂደው የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ፥ የኩባንያው የምርት ሂደት የአካባቢ ብክለት እያስከተለ ነው የሚል ቅሬታ ማንሳቱን ተከትሎ ነው […]
By:
somali 2

በሶማሌ ክልል በጎርፍ ምክንያት 98 ሺሕ ሰዎች ተፈናቀሉ

በሚያዝያ ወር በተደረገ ጥናት በሶማሌ ክልል በሸበሌ ዞን 165 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች በጎርፍ መጠቃታቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ 98 ሺሕ ያህል ሰዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በዚህ ሳምንት በወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት፣ በክልሉ በተከሰተው ጎርፍ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ አምስት ሺሕ ቤቶች መውደማቸውን፣ በሸበሌ ዞን የሚገኙ 72 ትምህርት ቤቶችና 63 የጤና ተቋማት […]
By:
35324

የህዳሴው ግድብ ፖለቲካዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ ጉዳይ ነው ሲሉ የግብጹ ባለስልጣን ተናገሩ

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሻኩሪ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ሳይንሳዊ መሆኑንና ፖለቲካዊ ትርጓሜ ሊሰጠው እንደማይችል ሰኞ እለት በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ሌሎቹ አካላትም ጉዳዩን በፖለቲካዊ አድልኦ ሳይሆን ሳይንሳዊ እውነታዎቹን እንዲቀበሉ መናገራቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቡ ዘይድ አስታውቀዋል፡፡
By:
888

በአባይ ግድብ ዙሪያ የግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን ውይይት ፍሬ አልባ ሆኗል

በአባይ ግድብ ግንባታ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ግብጽ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ውይይት በድጋሚ ፍሬ አልባ መሆኑን የግብጽ ባለስልጣን ማክሰኞ እለት አስታውቀዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ በሶስቱ ሀገሮች የመስኖ ሀብት ሚኒስቴሮች መካከል ለሁለት ቀናት የተደረገው ቴክኒካል ውይይት ያለምንም መፍትሔ መጠናቀቁን የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሆሳም ኤል ኢማም ለአሶሺትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡
By:
46228

የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ለህዳሴው ግድብ ስብሰባ ኢትዮጵያ ይገባሉ

በታላቄ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባና በካይሮ መካከል አለመግባባት ቢኖርም የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር መሀመድ አበደል አቲ አርብ እለት ኢትዮጵያ በመገኘት ከግድቡ ጋር በተያያዘ የቴክኒክ ጥናቶች በሚቀርብበት 18ኛው ዙር የሶስት ሀገሮች ብሔራዊ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ፡፡
By:
Eth PM

የህዳሴው ግድብ ግብጽን እንደማይጎዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን በመገደብ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግብጽ በምታገኘው የውሀ አቅርቦት ድርሻ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሱዳንን ወይም ግብጽን የመጉዳት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላትም ሐሙስ እለት በካርቱም ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ጋር ውይይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡
By: