የርዋንዳ ወጣቶች የንባያሮንጎ ተፋሰስን ለመንከባከብ በመሪነት ተገኝተዋል

የርዋንዳ ወጣቶች የንባያሮንጎ ተፋሰስን ለመንከባከብ በመሪነት ተገኝተዋል

በአማብል ትዋሂርዋ

ኪጋሊ፤ እለቱ በደቡባዊ ርዋንዳ በተራራማዋ ወረዳ በንያማጋቤ ሞቃታማ ሰኞ ማለዳ ነው፡፡ ወጣት ወንድና ሴቶች ቁልፍ የሆኑ ልምዶች ለመለዋወጥ ተሰባስበዋል፡፡ ይኸውም በአፈር መሸርሸር የተነሳ በተደጋጋሚ ወደ ጎረቤት ወንዝ ታጥቦ የሚሔደውን አፈር ለመጠበቅ በተግባር የተደገፈ ልምዳቸውን ለመለዋወጥ ነው የተሰባሰቡት፡፡

ይህ ተነሳሺነት የንያባሮንጎ ወንዝ ማጠራቀሚያን ለመጠበቅ በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ህብረሰተብ አቀፍ ጥረት አካል ሲሆን፤ 1.9 ሚሊዮን ስምምነት የፈጸሙ ገበሬዎችን በማሳተፍ የናይል የላይኛው የውሀ ክፍል አካል በሆነው በዚህ የወንዝ ዳርቻ አጠገብ የእርከን ስራን፣ አግሮ ፎርስትሪን እና ደን ማልበስን በመተግበር በመስራት፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘላቂ ጥቅም ማስገኘትን ያለመ ነው፡፡

‹‹በፕሮጀክቱ አማካኝነት የተለያዩ የእንክብካቤ ስራዎችን በመተግበር በመጠቀም በርካታ የተሻሻሉ የአስተራረስ ዘዴዎችን ተምረናል›› ይላል ‹‹አቢሽይዚሀምዌ›› የተባለው የአካባቢው የወጣት ገበሬዎች ትብብር ሀላፊ የሆነው አልፎንሲኔ ሙካንጋራምቤ፡፡

nyabarongo8

አቢሽይዚምዌ ‹በህብረት የቆሙ› የሚል ትርጓሜ ሲኖረው፤ በንያባሮንጎ ወንዝ በኩል ተጠርጎ የሚሄደውን አፈርና ውሀን ጠብቆ ለማቆየት የንያማጋቤ ወረዳ ነዋሪዎችን ለማሳተፍ በ2015 የተመሰረተ ነው፡፡

በማዕከላዊ ርዋንዳ በሙሃንጋ በሚገኘው በንያባሮንጎ ወንዝ ማጠራቀሚያ ወጣቱ የማህበረሰብ አባላት እርከኖችን አዘጋጅተዋል፡፡ ንያባሮንጎ የላይኛው የናይል ወንዝ አካል ሲሆን፤ በሰሜን አቅጣጫ 85 ኪ.ሜ. (53 ማይልስ) የሚፈስ ሲሆን፤ በምዕራባዊ እና ደቡባዊ ግዛቶች መካከል ድንበር ሰርቷል፡፡

መሰረታዊ የእርከን አስተራረስ

በኦገስት 2019 ወደ 138.452 ሄክታር የሚሆን የላይኛው የናባሮንጎ ወንዝ ማጠራቀሚያ አካባቢ በመሬቱ ባለቤቶች የተያዘ እንደነበር ተገምቷል፡፡

በትግበራው ምዕራፍ ወቅት የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ በመከላከልና የውሀ ጥራትን በማሻሻል የንያባሮን ውሀ ተፋሰስን ለመጠበቅ ፕሮጀክቱ የሙሃንጋ (ማዕከላዊ ደቡብ)፣ የንጎሮሬሮ (ምዕራብ)፣ የሩሃንጎ (ደቡብ)፣ የንያማጋቤ (ደቡብ) የጋኬንኬ (ሰሜን) ወረዳዎችን ጨምሮ ከተመረጡ የተወሰኑ ወረዳዎች እንደ ግብርና ባለ በተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ 

የላይኛው የንያባሮንጎ ማጠራቀሚያ የናይል ተፋሰስ አካል ሲሆን፤ ከደቡብ ወደ ሰሜናዊ የርዋንዳ ክፍሎች ከ3.348 ኪሜ ስኩዌር በላይ በሆነ አካባቢ ይፈሳል፡፡

የውሀ መጠራቀሚያው የርዋንዳ የውሀ ማማ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ በርካታ ገባር ወንዞችን ቁጥር ከፍ አድርጓል፡፡ ከእነሱም መካከል በጣም ጠቃሚ የሚባሉት (ከደቡብ ወደ ሰሜን) የምዎጎ ወንዝ (81.1ኪሜ) ፣ የሩካካ ወንዝ (47.4 ኪሜ ከሩበይሮ እና ንያሩቡጎይ ወንዞች)፣ የምቢሩሩሜ ወንዝ (51.6 ኪሜ)፣ የማሺጋ ወንዝ (12.2 ኪሜ)፣ የኪርያንጎ ወንዝ (10.4 ኪሜ)፣ የሙዛንጋ ወንዝ (24.4 ኪሜ)፣ የሚጉራሞ ወንዝ (15.0 ኪሜ) እና የሳቲንሲይ ወንዝ (59.7 ኪ.ሜ.) ናቸው፡፡

Copy of Story 2 viz 2

በንያባሮንጎ የውሀ ተፋሰስ ኢኒሺየቲቭ አማካኝነት በንያማጋቤ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ የሚሰራው አይነት መሰረታዊ የእርከን ቴክኒክ ለአካባቢ ጥበቃ መፍትሔነት የሚመከር ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በንያባሪንጎ ወንዝ ማጠራቀሚያ መሬት ላይ የሚገኙ የማህበረሰቡ ሁሉም አባላት በፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ ድጋፍ እንዲያገኙና ለናይል ውሀ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጡ የርዋንዳ ባለስልጣናት ጋር ተባብረው ለመስራት ተመዝግበዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ለገጠር ወጣቶችና ለወጣት ገበሬዎች ትኩረት የሰጠ ቢሆንም፤ በዚህ የሰው ሀይል ዘርፍ በውሀ መሸርሸር የሚፈጠረውን የአፈር መጥፋትን ለመቀነስ በእርከን አስተራረስ የተሻለ ጥቅም እንዲያገኙ ይበረታታሉ፡፡ 

ወንዙን ለመጠበቅ በተለያዩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት በሙሃንጋ (ማዕከላዊ) እና በንጎሮሬሮ (በምዕራብ) ዲስትሪክቶች በእርከን ስራ በአግሮ ፎረስትሪ እና በደን ልማት እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የማዕድን ማውጣት ስራን በማበረታታት በተሰራ ስራ የንያባሮንጎ ማጠራቀሚያ ከያዘው ከ1.102 ሄክታር 912 ያህሉን መልሶ ማልማት እንደተቻለ ይፋዊ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ምስጋና ለዚህ ፕሮጀክት በንያማግቤ በርካታ ወጣት ገበሬዎች የፉርኖ ዱቄት ዛፍ፣ ድንች፣ ስኳር ድንች፣ በቆሎ እና ባቄላ የመሳሰሉ ዋና ዋና የሰብል እህሎችን ማምረት ችለዋል፡፡ 

ወጣት ገበሬዎች በንያባሮንጎ ወንዝ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እና በዘላቂነት ምግብ ለማቅረብና ገቢያቸውን ለማረጋገጥ መሬታቸውን በደገደላማ ቁልቁለቶች ላይ በማልማት ያደረጉት እነዚህ ጥረቶች ለውጥ እንዲመጣ ማድረጋቸውን ሙካንጋራምቤ ተናግረዋል፡፡

በርዋንዳ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለስልጣን የተቀናጀ የዝናብ ውሀ ማኔጅመንት ሀላፊ ፍራንኮይስ ዣቪየር ቴቴሮ የአካባቢው ማህበረሰብ ወጣቶችን ያካተተ ትክክለኛ የማጠራቀሚያ እቅዶችን በማዘጋጀት የዩጋንዳን የውሀ ሀብት በበቂ እና በአግባቡ መጠቀም ይቻላል፡፡

ይሁንና ከከተማ ርቀው የሚገኙት ወጣቶቹ ገበሬዎች በመሰል ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ ለመሳተፍ በቂ እድሎችን አለማግኘታቸውን ነው ሙካንጋራምቤ በአጽንኦት የተናገሩት፡፡ 

Copy of Story 2 viz 3

‹‹ወጣት ገበሬዎች ከማንም በላይ የችግሩ ተጎጂ ናቸው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶች ሲኖሩ ከገጠር አካባቢዎች የሚሳተፉት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው›› ብለዋል፡፡

የእርከን አስተራረስ ዘዴ በአሁኑ ወቅት በንያባሮንጎ ወንዝ የአፈር መሸርሸርን ሊቀንስ ይችላል፡፡ የአካባቢው አስተዳደር መሪዎች እነዚህን እርከኖች በማስተዳደር ላይ የወጣቶች ተሳትፎን የማጎልበት አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡

በናይል ወንዝ ተፋሰስ ሀያልነትን መጋፈጥ

የንያባሮንጎ ወንዝ ማጠራቀሚያ ፕሮጀክት የተዘጋጀው በ2010 ርዋንዳ የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ትብብር አጀንዳ ስምምነትን ካጸደቀች በኋላ ነበር፡፡ ስምምነቱ ለግብርና ፕሮጀክቶች፣ ለውሀ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና አቅራቢዎች፣ ለሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች እና ሌሎችም ውሀ የመጠቀም ፈቃዶችን ለሚፈልጉ ፕሮጀክቶች በቂ ውሀን ለማረጋገጥ ነው፡፡ 

ይህ ህግ በ2010 የጸደቀ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ሀገር በተናጥል ለራሳቸው ልማት የጋራ ሀብቶችን መጠቀምን የሚፈቅድ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የትኛውም አዲስ ልማት የሌላው ሀገር ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆን እንደሌለበት የሚያስገነዝብ ነው፡፡

በአስራ አንድ ሀገሮች በኩል 6.853 ኪሜ ያህል የሚፈሰው ናይል ለግማሽ ቢሊዮን ህዝቦች የህይወት ምንጭ ነው፡፡

ወንዙ የሚፈስባቸው ሁሉም ከተሞች መገኘት ህልውና በዚህ ውሀ የተነሳ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ለግብጽ በተለይ ይህ እውነት ነው፡፡ ናይል ባይኖር ኖሮ ሌላ የሳራ በርሀ ክፍል ይኖር ነበር፡፡

ግብጽ በወንዙ ላይ ብቸኛ ተጠቃሚ ለመሆን በመሻት ለዘመናት የወንዙ አለቃ ለመሆን ሞክራለች፡፡ ይሁንና አሁን አሁን የላይኛው ተፋሰስ ሀገሮች ርዋንዳን ጨምሮ ከላይኛው ተፋሰስ የወንዝ ማጠራቀሚያ ድርሻቸውን ለመጠቀም በመጣር የግብጽን የበላይነት በመጋፈጥ ላይ ናቸው፡፡ 

ግብጽ እና ሱዳን አሁንም ድረስ የ1929 እና 1959 ስምምነቶችን እንደ ቴክኒካል ገዢ ህግ እንደተቀበሏቸው ሲሆኑ፤ ሌሎኞቹ የላይኛው ተፋሰስ የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ነጸ ከወጡ በኋላ በቅኝ ገዢዎች ዘመን የተፈረሙትን ስምምነቶች መቃወም ጀምረዋል፡፡

የ1959 ስምምነት 75 ከመቶ የሚሆነው የወንዙ ውሀ የግብጽ ድርሻ እንደሆነ ሲገልጽ፤ ቀሪውን ደግሞ ለሱዳን ይሰጣል፡፡

ግብጽ ለዚህ የበላይነቷ ሁልጊዜም የምትሰጠው ምክንያት በመልክአምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይኸውም ያለ ናይል ህይወት የማይኖራት በረሀማ ሀገር መሆኗንና በአንጻሩ ደግሞ የላይኞቹ ተፋሰስ ሀገሮች ደግሞ በመስኖ ለማጠጣት ሳይገደዱ በዝናብ ውሀ ግብርናቸውን ለማሳደግ በቂ ዝናብ መቀበል የሚችሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ነው፡፡

በተፋሰሱ ሀገሮች መካከል ያለውን የጋራ ውሀና ተዛማጅ ሀብቶችን በጥምረት መጠበቅና መጠቀምን አላማ በማድረግ በ1999 የተመሰረተው የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ኢኒሺዬቲቭ፤ አለመግባባቶችን ለመፍታት ቀጠናዊ ስምምነት ሆኖ በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ስለ ውሀ አስተዳደር ከደረጃው ዝቅ ያለ ሆኖ ቀርቷል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ኢኒሺዬቲቭ በተቋም ደረጃ ባለስልጣን አይደለም፡፡ የናይል ውሀ አጠቃቀምን በተመለከተ ለሚፈጸመው ስምምነት መሻገሪያ ነው፡፡ በመሆኑም መቀመጫውን በዩጋንዳ እንዲያደርግ ከተፈጸመው ስምምነት ባሻገር ህጋዊ ሰውነት የለውም፡፡ 

አሁንም ድረስ መፍትሔ ባላገኙ ልዩነቶች የተነሳ የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ኢኒሺዬቲቭ ትኩረት ያደረገው በቴክኒካል፣ በአንጻራዊነት ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶች ላይ ነው፡፡ ግብጽ ቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ መስመሮች የማይነጣጠሉ አድርጋ የምታይ በመሆኗ ተቋሙን ደካማ አድርጎታል፡፡ ስለዚህም ካይሮ በብዙዎቹ የናይል ተፋሰስ ኢንሺዬቲቭ ተሳትፎዎች ራሷን አቅቧ በመቆየቷ የተቋሙ ፖለቲካዊ አቅም ሊሟጠጥ ችሏል፡፡

nyabarongo6

የአቅም ግንባታ

የንያባሮንጎ ተፋሰስ ጥበቃ ስራ በሀገሪቱ ለተሻለ የውሀ ሀብት አስተዳደርና የተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳደር አቅምን ለማሳደግ መልካም ተሞክሮ መሆኑን የርዋንዳ ባለስልጣናት ያምናሉ፡፡

‹‹በ2024 እነዚህ ጥምር ጥረቶች በሁሉም ባለድርሻ አካላት ወጣችን ጨምሮ የተደረጉ እነዚህ ጥረቶች የንያባሮንጎ ወንዝን ወደ ንጹህ ውሀነት ሊቀይሩት ይችላሉ›› ኦብሰርቭስ ብለዋል፡፡

ውሀ ለርዋንዳ እድገት የተባለው ቡድን መሪ የሆኑት ኢምቤል ስሚድት በቅርቡ ኪጋሊ ላይ በሰጡት ቃለምልልስ የላይኛው የንያባሮንጎ ማጠራቀሚያ በርዋንዳ በመሬት ገጽታ አጠባበቅና የሀይድሮ ፓወር ተከላ ጥበቃ ላይ ይፋ የሆነ የመጀመሪያው ፕሮጀክት እንደሆነ ነው፡፡

‹‹ከላይኛው የናይል ተፋሰስ ጋር በተያያዘ በውሀ አስተዳደር ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን አቅምና ችሎታን ለማሳደግ እየሞከርን ነው›› ሲሉ ስሚድት ተናግረዋል፡፡

በርዋንዳ መንግስትና ባለድርሻ አካላት የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ ከዝናብ ተገኝቶ በእነዚህ ወሰኖች በሚፈሰው እና የጋራ መውጫ ወደ ሆነው መንገድ ወደታች ቁልቁል የሚወርደው የከርሰ ምድር ውሀ ላይ ነው፡፡

በርዋንዳ መንግስትና ባለድርሻ አካላት የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ ከዝናብ ተገኝቶ በእነዚህ ወሰኖች በሚፈሰው እና የጋራ መውጫ ወደ ሆነው መንገድ ወደታች ቁልቁል የሚወርደው የከርሰ ምድር ውሀ ላይ ነው፡፡

አሁን የአካባቢው አስተዳረደር አካላት ንጹህ የመጠጥ ውሀን ለማረጋገጥ የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበው ወጣቶችን ማሳተፍ ወጪ ቆጣቢ መንገድ መሆኑንም ተረድተዋል፡፡

አሁን የአካባቢው አስተዳረደር አካላት ንጹህ የመጠጥ ውሀን ለማረጋገጥ የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበው ወጣቶችን ማሳተፍ ወጪ ቆጣቢ መንገድ መሆኑንም ተረድተዋል፡፡ 

በንያባሮንጎ ወንዝ ላይ እንደተሰራው አይነት የተፋሰስ ልማት ጥበቃ ፕሮግራም ወጣት ገበሬዎች አፈርና ውሀ ጥበቃ ቴክኒኮችን እንዲጠቀሙ ይከፈላቸዋል- ይህ ክፍያም ማህረሰቡን የሚጠቅም ክፍያ ነው ሲሉ በንያማጋቤ ወረዳ የሶሺዮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ምክትል ከንቲባ ላምበርት ካባቲዛ ተናግረዋል፡፡ 

ይህ ዘገባ የተጠናከረው በኢንፎናይል እና ሲቪከስ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts