በአፍሪካ ውቅያኖሶች ጥቅም ላይ ያተኮረ ውይይት በለንደን ይካሔዳል

ከአለም የውቅያኖሶች ቀን ጋር በተያያዘ የመጀመሪያው የአፍሪካ ብሉ ኢኮኖሚ ፎረም በመጪው ሰኔ ወር በለንደን እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይም የአፍሪካ ውቅያኖሶች ምጣኔ ሀብታዊ አስተዋጽኦን በተመለከተ የመንግስት ሚኒስትሮች፣ የቢዝነስ አመራሮች፣ የውቅያኖስ ባለሞያዎች፣ የአካባቢ ጥበቃና የመርከብ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ150 በላይ ተወካዮችና ተናጋሪዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

No tags for this post.