ኢንፎናይል InfoNile የናይል ተፋሰስ ውሀን በመጠቀም በተፋሰሱ ሀገሮች የሚገነቡ የሀይል ማመንጫ ግድቦች የሚሰጡትን ጥቅምና ጉዳቶች በተመለከተ ጥልቅ የሆነ የምርምራ ዘገባዎችን እንዲያቀርቡ በተፋሰሱ ሀገሮች የሚገኙ ጋዜጠኞችን ይጋብዛል፡፡

የዘገባው መነሻ ሐሳብ  

በቀጣዮቹ አመታት በመላው አለም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ግድቦችን የመገንባት እቅድ አለ፡፡ ከእነዚህ መካከልም የተወሰኑት በናይል ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ናቸው፡፡ ግድቦች በእርግጥ የታዳሽ ሀይል መገኛ ምንጭ ናቸው፡፡ ነገር ግን ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ግድቦቹ በሚገነቡበት ቦታ ባሉት አካባቢና በህብረተሰብ ክፍሎች ላይም አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ እነዚህ ተጽዕኖዎች በናይል ተፋሰስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ2700 አመት ጀምሮም ይገኛሉ፡፡

የናይል ተፋሰስ ኢኒሺየቲቭ Nile Basin Initiative በተፋሰሱ ውስጥ ያለው የሀይል ማመንጫ አቅም ከ20 ጊጋ ዋትስ በላይ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ይሁንና ከዚህ ውስጥ አሁን 26 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው መጠቀም የተቻለው፡፡ በተመሳሳይ የህዝብ ብዛት ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፤ በ2035 የሚኖረው የሀይል ፍላጎት አሁን ካለው በ300 በመቶ ያህል እንደሚልቅ ተመልክቷል፡፡

ግድቦች የሀይል አቅርቦትን ለማሳደግ፣ ለምጣኔ ሀብት እድገት፣ ለስራ እድል፣ ለጎርፍ መከላከል እና ለመስኖ ስራ ጥቅም የሚሰጡ ቢሆኑም፤ ስነ ምህዳሩን በማቃወስ፣ ሰዎችን ከአካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ፣ ጎርፍ እንዲጨምር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት እና የስራ እድል እንዲጠፋ በማድረግም አስተዋጽኦ አላቸው፡፡

የዘገባው ታሪክ ለቀጣዮቹ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ እንዲሆን ይጠበቃል

የግድብ ግንባታ ገንዘብ ድጋፍ እና ፖለቲካው

እንዴት ማመልክ ይቻላል

ዘገባውን ለመስራት ጋዜጠኞች በተናጥል ማመልከት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ ጋዜጠኞች ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው በጋራ ሆነው እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡ ቅድሚያ የማግኘት እድልም ይኖራቸዋል፡፡ ከሌሎች ጋር በጥምረት የሚያመለክቱ በአንድ የኢ-ሜይል መልዕክት ላይ ብቻ የሁሉንም የቡድን አባላት አስፈላጊ ሰነዶችን በማያያዝ ማመመልከት ይችላሉ፡፡ 

ማመልከቻውን በኢንፎናይል ኢ-ሜይል [email protected] ከሴፕቴምበር 10 ቀን 2021 በፊት እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ 

የዘገባ ፕሮፖዛላችሁ የሀይል ማመንጫ ግድቦች በተለያዩ ዘርፎች ወይም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማጣመር የዳታ ትንተና እና visualization ለመስራት እንደሚችል ማሳየት አለበት፡፡ ለአብነትም ዘገባው በሀይል በግብርና፣ በምጣኔ ሐብት ፣ በምግብ ደህንነት፣ በውሀ በመሬት፣ በአደጋዎች፣ በአኗኗር ሁኔታ እና መሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ተያያዥነት ያለው መረጃን ማጣመር አለበት፡፡ ካርታዎችንና ቪዥዋላይዝ የሆኑ ታሪኮችን የምንሰራባቸው ጂኦ “Geo-coded”  ወይም  geographical data ይበልጥ ተመራጭ ናቸው፡፡ ይሁንና ሌሎች ተአማኒነት ያላቸው ዳታዎችን ማቀናጀትና መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

የዘገባው የመጨረሻ ውጤት የጽሑፍ፣ ቪዲዮ፣ የፎቶግራፎች፣ የድምጽ፣ እና የዳታ መረጃዎችን/ ካርታዎችን ያካተተ ጥልቅ የመልቲ ሚዲያ ዘገባ In-depth Multimedia story መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በራዲዮ፣ ቴሌቭዥን፣ እና ህትመት ውጤቶች ላይ የሚቀርብ መሆን አለበት፡፡

    Apply now!


    Gender