በአኒካ ማክጊኒስ
የአየር ንብረት፣ የግብርና ስራ፣ እና ግድቦች የኬንያ ረግረጋማ ቦታዎች ላይ ክፉኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል፡፡ ለሀገሪቱ ወቅታዊ የውሀ ችግር እና የአሳ ሀብት እጥረትም አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
ኢኮፋይንደር ኬንያ በኪሲሙ አካባቢ በዊናም ገልፍ ረግረጋማ ቦታዎች የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን፤ የሶስት አመት ፕሮጀክቱ በቪክቶሪያ ሐይቅ ረግረጋማ ቦታዎች ለሚኖሩ ቤተሰቦች ረግረጋማ ቦታዎችን እንዲጠብቁ ድጋፎችን አድርጓል።
የድርጅቱ ድጋፍ ለነዋሪዎቹ የሰው እና እንስሳትን አይነ ምድር ወደ ባዮጋስ ሀይል መቀየር የሚችሉበት መጸዳጃ ቤቶችን፣ በጸሀይ ሀይል የሚሰሩ መብራቶች፣ እና የጉድጓድ ውሃ ማውጫ መሳሪያዎችን ያካተተ ነው፡፡ ተሳታፊ አባወራዎችን ‹‹ገበሬ ለገበሬ መምህራኖች›› በማድረግ የግብርና ዘዴዎችን ለጎረቤቶቻቸው እንዲያካፍሉ አድርጓል፡፡
ከሶስት አመት በኋላም ደርቀው በነበሩት በረግረጋማ ቦታዎቹ እጽዋቶች መብቀል የጀመሩ ሲሆን፣ አሳዎችም ወደ ሀይቆቹ ተመልሰዋል፡፡