ከአስር ዓመት በፊት የቱሪስቶች ቡድን መንደሮቹን በመናድ ወደ ማያራራ ሐይቅ በመሄድ ዛፍ የሚወጡ አንበሶችን ፣ የአራዊት ዝርያዎችን ፣ ሌሎች ተፈጥሮአዊ ድንቅ ነገሮችን የሚፈልሱ የፍላሚንጎ መንጋዎችን ለመዳሰስ ነበር ፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከ 90 በመቶ በላይ ቀንሷል
ገቢ የማመንጨት ሥራዎች ግብርና ፣ ዓሳ ማስገር ፣ የእንሰሳት እርባታ እና የከሰመ ቱሪዝም ናቸው
በሲልቨስተር ዶማሳ
ከአስደናቂዋ የምቶ ዋ ምቡ የጎብኝዎች መዳረሻ ከተማ በአንድ ወቅት የታንዛንያ ሁለተኛዋ ጨዋማ ሐይቅ ወደ ሆነው ወደ ማንያራ ሐይቅ ዳርቻ የአስር ደቂቃ የእግር ጉዞ በኋላ የአካባቢው የሐይማኖት መሪ የሆኑት ግለሰብ መንገዱን ተሻግረው እጃቸውን ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱ በዝምታ ጎርፍ በጸጥታ ይመለከታሉ፡፡ ቤቶችንና በአቅራቢያቸው ያሉ እርሻዎችን ያወደመውን ጎርፍ በዝምታ ይመለከታሉ፡፡
የሐይማኖት መሪው ናሴብ ኢድ ናሲብ ከአስር አመት በፊት የነበረውን ሁኔታ ልክ እንደ ቅርብ ጊዜ ክስተት ሁሉ በርከት ያሉ የጎብኝዎች ቡድኖች ዛፍ ላይ የሚወጡ አንበሶችን፣ የጫካ አውሬዎችን፣ የተጓዥ ፍላሚንጎዎች መንጋዎችን የመሳሰሉ አስደናቂ ፍጡራንንን ለመመልከት ወደ ማንያራ ሐይቅ መንደሮች ይመጡ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡
አሁን ላይ ግን በአንድ ወቅት ምቹ የመዝናኛ ቦታ የነበረው ሰፊው አካባቢ ተሸራርፎ በበጋ ወቅት መኪኖች የሚሔዱበት ወደ ደረቅ መሬትነት ተለውጧል፡፡ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜም ከተከለለው መሬት አንድ ማይል ርቀው ወደ ሚገኙ መንደሮች ይሔዳል፡፡
ከሀገሪቱ የተፈጥሮ ሐብት እና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ጉባኤ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ሐይቁ በ1950ዎቹ አካባቢ 20 ሜትር ያህል ጥልቀት ነበረው፡፡ ምንም እንኳ በ1981 በተባበሩት መንግስታት የተጠበቀ የስነ ህይወት አካባቢ ቢሆንም ባለፉት ሁለት አስርት አመታትም ሐይቁ ከ90 ከመቶ በላይ እየቀነሰ ነው፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳስታወቀው ከሆነ ሐይቁ በየአመቱ 5 በመቶ ያህል እደረቀ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የሐይቁ ጥልቀት ወደ 20 ሴንቲ ሜትር ያህል ይደርሳል፡፡
እንደ ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪና መንግስት ሁሉ የሐይማኖት መሪው ናሲብ ለሐይቁ መድረቅ የዱር እንስሳት ጥበቃው እና የሰው ልጆች እንቅስቃሴዎች ሚዛናዊ አለመሆንን በምክንያትነት ይጠቅሳሉ፡፡ የማንያራ ሐይቅ ቀደም ሲል የሚታወቀው የተባበሩት መንግስታት አንደኛው አካል የሆነው BRAAF (Biosphere Reserves for Biodiversity Conservation and Sustainable Development in Anglophone Africa) ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ለሐይቁ ስነ ህይወት ዘላቂ ልማት እንደ ንብ ማነብ አይነት ያሉ ገቢ አምጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማስተዋወቅ ነበር፡፡
አሁን ላይ ግን ምንም አይነት መሰል እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ አይደለም የሚሉት ተሰናባቹ የአካባቢው የፓርላማ ተወካይ የሆኑት ጂቱ ሶኒ ናቸው፡፡ “ገቢ የሚያስገኙ እንቅስቃሴዎች የግብርና ስራ፣ አሳ እርባታ፣ እንስሳ እርባታ እና በመጥፋት ያለው የቱሪዝም ስራዎች ብቻ ናቸው” ይላሉ፡፡ “ነገር ግን የኢንደስትሪው የጀርባ አጥንት የሆነው ሐይቁ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ከጀመረ በኋላ ሁሉም ነገር ሞቷል” ብለዋል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጨዋማው ውሀ የጉማሬዎች መኖሪያ፣ የሮዝ ፍላሚንጎዎች እና ከ400 በላይ የወፍ ዘርያዎች በዋናነትም የውሀዳር ወፎች መኖሪያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቱሪዝም ኢንደስትሪው ታዛቢዎች በሰጡት አስተያየትም በፈረንጆቹ አፕሪል እና ሜይ ወር ላይ በሐይቁ ዙሪያ ባለው ደን በኩል ወፎችን ለመመልከት በጣም ምርጡ ጊዜ ነው፡፡ በነዚህ ወራቶች አሁን ላይ በዚህን ወቅት ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያለው ጎርፍን ያስተናግዳል፡፡ ይህ የሚጎዳው ደግሞ በምግብ በበለጸገው ሐይቅ የሚሰበሰቡትን ተጓዦቹን ሮዝ ፍላሚንጎዎች፣ ይብራ የተሰኙ ወፎችን እና ባለረጅም አንገት የባህር ወፍ የሆኑት እንስሳትን ብቻ አይደለም፡፡ በአጠቃላይ የቱሪዝም ሰንሰለቱም ጭምር ነው የሚቆረጠው፡፡
“ሁላችንም ብንሆን ልንረዳ የሚገባው ነገር ቢኖር ይህ ለስደተኛ የዱር እንስሳቶች እና ወፎች ከማንያራ ብሔራዊ ፓርክ ወደ ታራንጊሬ ብሔራዊ ፓርክ መተላለፊያ መሆኑን ነው፡፡ እዚህ ለምግብ እና ለመራባት እዚህ ነው የሚሰባሰቡት፡፡ ይሁንና በሐይቁ ላይ በሰዎች እንቅስቃሴ የሚፈጠር ማንኛውም ተግባር የእነዚህ ፍጥረት ስነ ህይወት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል” በማለት የተናገሩት በምቶ ዋ ምቡ የባህል ቱሪዝም ፕሮግራም ስነ ጥበቃ ባለሞያ ጆርጅ ዳንኤል ናቸው፡፡
አናስታሲያ ሙስጠፋ የማክሮ ባዮሎጂ ባለሞያ ሲሆኑ፤ በሐይቁ ላይ የተፈጠረው ስጋት ፍላሚንጎዎች እንዲቀንሱ አድርጓል ብለዋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ፍላሚንጎዎች ለመራባት የማንያራ ሐይቅን ይመርጡታል፡፡ በአቅራቢያው በሚገኘው ናትሮን ሐይቅ ይጠለላሉ፡፡ ያልተረጋገጡ መረጃዎች መሰረት አሁን ላይ ከ500,000 ያነሱ ወፎች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ፡፡ “እነዚህ ዝርያዎች የሚመገቡት ጋር ያሉትን በጨዋማ ሐይቆች የሚገኙትን ሰማያዊ አረንጓዴ ከቀይ አልጌ ጋር ነው፡፡ ነገር ግን በማያራ የተከሰተው አይነት የሐይቅ ጎርፎች መጠለያ ጎጇቸውን አይደለም የመራቢያ አካባቢያቸውን ያውከዋል” ሲሉ ባለሞያዋ ያስረዳሉ፡፡ የማንያራ ሐይቅ ጨዋማነት መጠንን በተመለከተ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ዳታ የለም፡፡ ነገር ግን መጠኑ መቀነሱን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ በ2016 ላይ ስፕሪንገር ኢንተርናሽናል በተባለ ተቋም ለህትመት የበቃ “ጨዋማ ሐይቆች በምስራቅ አፍሪካ” የተሰኘ አንድ ጥናት /study/ እንደ ብሔራዊ ፓርኮች አይነት ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች መቋቋም ለሐይቁ ምንም አይነት ጥበቃ አለማድረጋቸውን አመልክቷል፡፡ የታንዛኒያ የዱር እንስሳት ምርምር ማዕከል በበኩሉ በአካባቢው የዱር እንስሳት ዝርያዎች በአጠቃላይ ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቁን አሳውቋል፡፡ የዚህም ምክንያት እየጨመረ በመጣው የሰዎች እንቅስቃሴ መተላለፊያ መንገዶቹ በመቋረጣቸው እና መሬቱን እንደ ግብርና፣ እንስሳት እርባታ፣ ሰፈራ፣ ማዕድን ቁፋሮ እና አሳ እርባታ አይነት ላሉ ስራዎች ጥቅም ላይ በመዋሉ በተፈጠረው ግጭት የተነሳ ነው፡፡ ከሐይቁ ዙሪያ ያሉ ከ70 ከመቶ በላይ የሚሆኑ የበቆሎ፣ ሩዝ፣ እና አምራች ገበሬዎች የውሀውን ፍሰት ወደ እርሻዎቻቸው የሚቀይሩ ኩሬዎችን በዋና ወንዞች ላይ ሰርተዋል፡፡ የግብርና ባለሞያዎች እና የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሞያዎችም ቅርንጫፍ ወንዞቹ ፍርስራሾችን ወደ ወንዞች እና ቀጥሎም ወደ ሐይቁ የማጓጓዣ መንገዶችም ነበሩ፡፡
የሐይቁ ቀውሶችን መጋፈጥ
የማንያራ ሐይቅ የሚያመነጨው ውሀ የሌለው ሲሆን፤ በከርሰምድር ተፋሰሶች እና በርካታ ወንዞች የሚገብሩት ነው፡፡ በስምጥ ሸለቆ አሰራር አማካኝነት የተፈጠረ ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በ1974 የብሔራዊ ፓርክ አካል ከመሆኑ በፊት በ1920ዎቹ ላይ ለአደን ተመራጭ የሆነ ቦታ ነበር፡፡
አና ማታዮ ከሐይቁ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በሐይቁ ላይ የሰዎች እንቅስቃሴ ተጽዕኖ አሁን ላይ በግልጽ መታየቱን ትናገራለች፡፡ መኖሪያ ቤቷ በቅርቡ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎነፋስ ባመጣው ጎርፍ የወደመባት ስትሆን፤ ለዚህ ቀውስም ገበሬዎቹን ትወቅሳለች፡፡
“የሐይቁ ጥልቀት መጠን አሁን ላይ ምንም አይነት የዝናብ ውሀን መያዝ የማይችል ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በአካባቢው ወዳሉ መንደሮች እንዲመለስ አድርጎታል” ይላሉ የሐይማኖት መሪው ናሲብ፡፡
በማንያራ ብሔራዊ ፓርክ የተፈጥሮ ጥበቃ ከፍተኛ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ኖኤላ ማይንጋ በበኩላቸው የማንያራ ሐይቅ ደለል መጨመር እና በተደጋጋሚ መድረቅ ለግብርና እና ለሰዎች ፍጆታ በሚወጣው ውሀ የተነሳ እንደሆነ ነው የሚገልጹት፡፡ ይህ እንግዲህ በውሀ ማከማቻው አካባቢዎች ዘላቂ ያልሆኑ የግብርና ስራዎች በተጨማሪ መሆኑ ነው፡፡
“ሌላኛው ምክንያት በፓርኩ ዙሪያ የህዝብ ብዛት መስፈር፣ በከፍተኛ ቦታዎች ያሉ ደኖች መራቆት እና የአለም ሙቀት መጨመር ናቸው” ይላሉ ዶክተሩ፡፡ በ2009 በተደነገገው የውሀ አስተዳደር ደንብ መሰረት ውሀ ከሐይቁ ማውጣት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ እስከ 500,000 ሽልንግ ገንዘብ ወይም ስድስት ወር እስራት ያስቀጣል፡፡
የካራቱ ወረዳ ዋና ዳይሬክተር ዋዚሪ ሞሰስ እንደተናገሩት የአካባቢው ባለስልጣናት ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሲሰሩ ቢቆዩም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን የወሰዷቸው እርምጃዎች ችግሩን መቅረፍ አልቻሉም፡፡
በአካባቢው ለሚገኙ ለእንስሳት አርቢዎች እና ገበሬዎች ከሐይቁ ውሀ ማውጣት እና የዱር እንስሳት መተላለፊያዎችን መዝጋት የሚያስከትለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ግንዛቤ የመስጠት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ “ስኬታማ አይደለንም ማለቱን እመርጣለሁ፡፡ ነገር ግን ስራዎችን እየሰራን ነው፡፡ ሐይቁን ማትረፍ እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን” በማለት ዳይሬክተሩ ይናገራሉ፡፡
እርሻን ውሀ የማጠጣቱ ተግባር ጫና የፈጠረው በማንያራ ሐይቅ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ተመሳሳይ ተጽዕኖዎችም ሱምባዋንጋ በሚገኘው በሩክዋ ሐይቅ ላይም ተከስቷል፡፡
የካኤጌሳ አካባቢ ጥበቃ ማህበረሰብ ባለሞያ ግሬስ ሺኦ በሰጡት ምክረ ሐሳብ በመሞት ላይ ያለውን ሐይቅ ለማዳን የተሻለው መንገድ ውጤታማ የአሳ እርባታ እና የግብርና ዘዴዎችን ነው፡፡
ከፍተኛ የውሀ መጠን በሚወጣባቸው በካራቱ፣ በምቡሉ፣ በባባቲ እና በሞንዱሊ ወረዳዎች በጠብታ ውሀ የማጠጣት ዘዴ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቸኛው መፍትሔ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ዶክተር ምንይንግ እና ሌሎች የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሞያዎች ለአካባቢው ዙሪያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ምክንያታዊ የሆነ የመሬት አጠቃቀምን እንዲለማመዱ አማራጮችን እያስተማሩ ናቸው፡፡
እንደ ሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር ከሆነ በታንዛኒያ በ16,710 ሄክታር መሬት ላይ በጠብታ የማጠጣት ልምዱ 39 በመቶ ያህል ብቻ ነው፡፡ የሀገሪቱ ብሔራዊ ጉባኤ ባገበሬዎችን ከመጠን ያለፈ የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትሏቸው ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ እና የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል እና ድህነትን ለመቀነስ ባለፈው
ይህ የኢንፎናይል InfoNile story ዘገባ የተጠናከረው ከጄአርኤስ (JRS) ባዮዳይቨርስቲ ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ ነው