ሊጠፋ የተቃረበው የአሳ ዝርያና ምክንያቶቹ

ሊጠፋ የተቃረበው የአሳ ዝርያና ምክንያቶቹ

By Janet Murikira

  • በ 2015 አባይ የቲላፒን ጣት ጣቶች በኬንያ በኩል በጂፒ ሐይቅ ተዋወቁ
  • ሥር የሰደደ በሽታ የሌለባቸው የዓሣ ዝርያዎች መጀመራቸው አሳ አጥማጆችንና ተመራማሪዎችን ይህ በሐይቁ ውስጥ ውድድርን ከፍ ያደርገዋል የሚል ስጋት አሳድሯቸዋል ፣ ይህ ደግሞ በአደጋው
  • ​​ላይ የሚገኘውን የጂፕ ቲላፒያን ህዝብ የበለጠ ይከፋል ፡፡
    ጂፒ ቲላፒያ በ 20 ዓመታት ውስጥ የመጥፋት 50% ዕድል አለ ፡፡

ስቴቨን ኦሞንዲ ቀደም ባሉት ጊዜያት አሳ በማጥመድ ያሳለፈውን ጊዜ ፈጽሞ አይዘነጋውም፡፡ የ30 አመቱ ወጣት ኑሮው በጂፔ ሀይቅ ዳርቻ አጠገብ ባለው በንግሆኒ መንደር ነው፡፡ ሐይቁ በታይታ ታቬታ እና በኪሊማንጃሮ ክልሎች የሚገኝና ኬንያ እና ታንዛኒያ የሚጋሩት ነው፡፡

ኦሞንዲ በጂፔ ሐይቅ የአሳ እርባታ ስራ የጀመረው በ2009 ነው፡፡ ይኸውም የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት ጂፒ ቲላፒያን የተባለው የሐይቁ የአሳ ዝርያ ለመጥፋት ከተቃረቡት መካከል አንዱ አድርጎ ከመዘገበው ከሶስት አመት በኋላ ማለት ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ታዲያ ማለት በ20 አመታት ውስጥ የሐይቁ አሳ ጨርሶ የመጥፋቱ ነገር 50 በመቶ ነው ማለት ነው፡፡

በ2015 የሐይቁን ህይወት ለመታደግ ተብሎ በኬንያ በኩል ወደ ሐይቁ እንዲገቡ የተደረጉ የናይል ቲላፓይን ዝርያዎች ከመጡ በኋላ ወዲያው ነበር የእሱም ገቢ ለውጥ ማሳየት የጀመረው፡፡ ሁኔታው የእሱንም ሆነ የሌሎች አሳ አርቢዎችን ህይወት ስጋት ላይ ጥሏል፡፡ 

ኦሞንዲ ባራካ ኤፍኤም ቃለ መጠይቅ ባደረገለት እለት ምንም እንኳን ህጻን ቢሆንም ዘጠኝ ኪሎ ግራም የሚመዝን ናይል ቲላፒያ አሳ ይዞ ነበር፡፡ ጂፔ ቲላፒያ አሳን ከሚያጠምድበት የቀድ ጊጊው አንጻር እፎይታ ነው የሰጠው፡፡  

 

READ ALSO:Kilifi fishermen feel effects of dwindled  Parrotfish populations

“እኛ አሲሊያ የምንለውን ጂፔ ቲላፒያ አሳን ለመያዝ የፈለገ ሰው ቢኖር፤ በሩቩ ወንዝ አፍ አጠገብ እድሉን መሞከር አለበት፡፡ በእርግጥ ይህም ራሱ አስተማማኝ ባይሆንም እንኳ” ይላል ኦሞንዲ፡፡

አሳው በ2015 ወደ ሐይቁ እንዲመጣ ከመደረጉ በፊት በታንዛኒያ በኩል የሚሰራው የፓይለት ፕሮጀክት ስህተት ከሆነ በኋላ ወደ ሐይቁ እየተጓዘ ነበር፡፡ 

ይህንን የሚናገሩት በታዛኒያ በሶኮይን ዩኒቨርስቲ የባህር ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ጆንሰን ግሬይሰን ናቸው፡፡

“በታንዛኒያ የአሳ አርቢ ገበሬዎች አማካኝነት ለሙከራ የተለዩ የተወሰኑ የናይል ቲላፒያ አሳ ዋሻዎች የጠፉ ሲሆን፤ ከጥቂት ወሮች በኋላም ገበሬዎቹ በቪክቶሪያ ሐይቅ ብርቅዬ የሆኑትን የናይል ቲላፒያ አሳን በጂፔ ሐይቅ ማግኘት ጀመሩ” ይላሉ ዶክተር ምሻና፡፡

የናይል ቲላፒያ በጂፔ ሐይቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1983 ከተገኘው ከሲንጊዳ ቲላፒያ ቀጥሉ ሁለተኛው ብርቅዬ ያልሆነ የቲላፒያን አሳ ዝርያ ነው፡፡

 

አንዳንድ ተመራማሪዎች እንዳመለከቱት የሲንጊዳ ቲላፒያ አሳ በ1970ዎቹ በታቬታ ክፍለ ግዛት ከባድ ዝናብ መከሰት በኋላ ተጠርጎ በሉሚ ወንዝ በኩል ነው ወደ ሐይቁ የመጣው፡፡ በ1988 ለህትመት በበቃው በምስራቅ አፍሪካ የተፈጥሮ ታሪክ ማህበረሰብ እና ብሔራዊ ሙዚየም የተዘጋጀው ጥናት paper ላይ አሳው ወደ ጂፔ ሐይቅ እና ሌላኛው የጋራ በሆነውና በታንዛኒያ በኩል በሚገኘው ወደ ቻላ ሐይቅ እየተጓዘ እንደነበር ነው የተመለከተው፡፡

“ሲንጊዳ ቲላፒያ (Oreochromis esculentus), ሬድብረስት ቲላፒያ (Tilapia rendalli)እና ፓንጋኒ ቲላፒያ (O.p.pangani) የሚባሉት የአሳ ዝርያዎች ከታንዛኒያ በኩል ለመገኘታቸው ምንም ጥርጣሬ የለንም፡፡ ሆን ይህ ተብሎ ወይም በጂፔ ሐይቅ ደግሞ በስደት መልክ ሊሆን ይችላል” ሲል የጥናቱ መረጃ ያመለክታል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ደግሞ ብርቅዬ ያልሆኑ የአሳ ዝርያዎች ወደ ሐይቁ መምጣት አንዳንድ አሳ አርቢዎች እና ተመራማሪዎችን በሐይቁ ላይ ፉክክር ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል፡፡ ለከፍተኛ አደጋ ለተጋለጠው ለጂፔ ታሊፒያ የአሳ ዝርያ ተጨማሪ አደጋ እንደሆነም ያስባሉ፡፡ 

“በብዙ ምክንያቶች አዳዲሶቹ የአሳ ዝርያዎች በነባሮቹ ዝርያዎች ላይ የበለጠ የበላይ ሊሆኑ ይችለሉ፡፡ በቀደሙት አመታት ለጂፔ ቲላፒያ መቀነስ አንደኛው ምክንያት እንደ ሲንዲጋ ቲላፒያ አይነት አዳዲስ ዝርያዎች መገኘት ነው” ይላሉ ዶክተር ምሻና፡፡

ምንም እንኳ ዶክተሩ የናይል ቲላፒያ በሐይቁ ላይ ማስተዋወቅ የፈጠረውን ጫና ማረጋገጥ ባይችሉም ቁጥሮችና የአካባቢው አሳ አርቢዎች የተለየ ታሪክ ነው የሚናገሩት፡፡

እንደ ኬንያዊው አሳ አርቢ ጆን ኦድሂያምቦ አስተያየት በሐይቁ ላይ የናይል ቲላፒያ መገኘት ለመጥፋት የተቃረበውን ጂፔ ቲላፒያን ፍጻሜ የበለጠ የሚያፋጥን ነው፡፡

ኦድሂያምቦ አሁን ለመጥፋት የተቃረበውን የአሳ ዝርያ ቲላፒያን ለመጨረሻ ጊዜ ያጠመደው ከሶስት አመት በፊት ነው፡፡

“ጂፔ ቲላፒያን ማጥመድ በጣም የማይቻል እየሆነ መጥቷል፡፡ አሳ አጥማጆች ሊያገኟቸው ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከስንት አንዴ ነው፡፡ ለዚያውም ደግሞ በሩቩ ወንዝ አፍ ላይ ማጥመድ የግድ ይላል” ይላል፡፡

በኬንያ ባህር እና አሳ እርባታ ምርምር ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ፖል ኦሪና እንደሚገልጹት፤ በሁለቱ ቲላፒያን ዝርያዎች መካከል ያለው ድንበር ዘለል ፉክክር የጂፔ ቲላፒያ ዝርያዎች አነስተኛ ፉክክር ወዳለበት አካባቢ እንዲሔዱ ሊያስገድዳቸው ችሏል፡፡

“የእነሱን አይነት ዝርያዎች ሲመጡ እና በተመሳሳይ መጠን ሲመገቡ ውስን በሆነው ሐብት ላይ እኩል መፎካከር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እንደ ናይል ቲላፒያ አይነቱ የሚመጣ ከሆነ ደግሞ በጂፔ ቲላፒያ ላይ በጣም ሀይለኛ ይሆናል፡፡ እናም በጊዜ ሒደት በጥቂት አመታት ውስጥ ጂፔ ቲላፒያ ለበጎ በሆነ ምክንያት ቦታውን ጥለው ሊሔዱ ይችላሉ” በማለት ዶክተር ኦሪና ያስረዳሉ፡፡

ዶክተር ኦሪና አክለውም እንዳስረዱት በአፕሪል እና ሜይ እንዲሁም በጁን ወር መካከል በሐይቁ ማጥመድ ከተቻለው 15.7 ቶን አሳ የጂፔ ቲላፒያ ዝርያ 5 ከመቶ ብቻ ነው፡፡ ናይ ቲላፒያ ከፍተኛውን መጠን ይይዛል፡፡

ይሁንና ይህ የጂፔ ቲላፒያ መሽቆልቆል ከ2016 አመት ጋር ሲነጻጸር ማለትም ናይል ቲላፒያ ወደ ሐይቁ ከመጣ በቀጣዩ አመት፤ 26.3 ሜትሪክ ቶን አሳ ማግኘት እንደተቻለ ከኬንያ አሳ እርባታ አገልግሎት የተገኘ ጥናት Fisheries  ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ አመትም ሐይቁ በኬንያ ከሚገኘው አሳ መጠን ውስጥ ያበረከተው ድርሻ ከ1 በመቶ ያነሰ ነው፡፡

ይሁንና ታዲያ የጂፔ ቲላፒያ አሳ ዝርያ መጥፋትን በተመለከተ በኬንያም ሆነ በታንዛኒያ በኩል ላሉ ባለስልጣናት አዳጋች ሆባቸዋል፡፡ በሁለቱም በኩል ያሉ አሳ አጥማጆች የሚያጠምዱትን የአሳ መጠን መዝግበው የማይዙ ሲሆን፤ አንዳንድ ጊዜ የታንዛኒያ አሳ አጥመጆች ከፍተኛ ፍላጎት ወዳለበት ወደ ኬንያ እየመጡ የሚሸጡበት ሁኔታ አለ፡፡

በማርች ወር ላይ በኬንያ የታይታ ታቬታ ግዛት አስተዳደር የአሳ አርቢዎች የሚያገኙትን አሳ እንዴት በአግባቡ መዝግበው መያዝ እንዳለባቸው ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በታይታ ታቬት ግዛት የግብርና፣ እንስሳትና አሳ እርባታ ሀላፊ ዴስ ምዋንጎማ እንደገለጹት፤ በአካባቢው ምን ያህል አሳ እንደተገኘ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ነው የሚናገሩት፡፡

“በጂፔ ሐይቅ 106 አባላት ያሉት ማህበር አለን፡፡ እናም ለአባላቶቻችን ስልጠና እየሰጠን ስለምንገኝ ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ የምንችል ይሆናል” ብለዋል፡፡

Jipe 9
Fishermen and traders sorting fish

ህገ ወጥ የአሳ ማጥመጃ መረቦች

አሳዎችን በአግበቡ ካለመያዝ በተጨማሪ ከደረጃ በታች የሆኑ ህገ ወጥ የአሳ ማጠመጃ መረቦች ራሳቸው የጂፔ ቲፒያ የአሳ ዝርያ እንዲጠፉ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡

በሐይቁ ላይ በጣም ቀጫጭን የሆኑ አሁንም ድረስ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ባራክ ኤፍ ኤም ለመመልከት ችሏል፡፡ በኬንያ በ2016 የአሳ እርባታ አስተዳደር እና ልማት ህግ ላይ ከሁለት ከተኩል ኢንች በታች የሆነ ሽቦ መጠን ያላቸው መረቦች የተከለከለ መሆኑ ቢመለከትም እየተሰራበት ነው

ይህ ደግሞ የጂፔ ቲላፒያ ዝርያዎች ጨርሶ እንዲጠፉ ገፊ ምክንያት መሆኑን ዶክተር ኦሪና ይገልጻሉ፡፡

“በጣም ጨቅላዎቹን አሳዎች ማጥመድ የጂፔ ሐይቅ መልሶ እንዲያገግም አያደርጉትም፡፡ አሳ ማርባት የማይፈቀድበት ወር ከሆነ ይህ በፖለቲካው በኩልም በፈጻሚዎችም በኩል መከበር አለበት” ሲሉም ይመክራሉ፡፡ 

 

የሐይቁ መመናመን

ለመሆኑ ግን ህገ ወጥ የሆነው የማጥመጃ መረብ እና እንግዳ ዝርያዎች በተመለከተ የወጡት ህጎች በሐይቁ ላይ ተግባራዊ ቢሆኑ እየጠፋ ያለውን የጂፔ ቲላፒያ ዝርያ ለማሻሻል ይረዳ ይሆን?

ተመራማሪዎች እና የአካባቢ ጉዳይ የማህረሰብ አንቂዎች ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች መቅረፍ ከተቻለ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ 

“የአሳ እርባታው ቀውስ በውሀው ጥራት መለወጥ (የጨዋማነት መጠን መጨመር እና የውሀው መደፍረስ በማህረሰቡ ተገልጿል)፣ በሰዎች እንቅስቃሴ የሚመጣ ደለል መጨመር የተነሳ ነው” ሲል በ2016 በታንዛኒያ በኩል ባለው ሐይቅ ላይ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ያደረገው የግሎባል ኔቸር ፈንድ ጥናት statement  አመልክቷል፡፡

 

የ70 አመቱ ዳሚዬን ምዋካ የኬንያ ገበሬ እና የአካባቢ ጉዳይ ማህበራዊ አንቂ እንደተናገሩት፤ በኢንደስትሪ እርሻዎች አማካኝነት የሚታየው ደካማ የመሬት አጠቃቀም ገበሬዎች የጂፔ ሐይቅ ውሀን አቅጣጫ ቀይረው እንዲጠቀሙ ማድረጋቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሐይቁን በከርሰምድር ውሀ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዲሆን ያስገድደዋል ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

ቀደም ባለው አመት የታይ ታቬታ ግዛት አስተዳደር ደለል የዘጋው የወንዙን አፍ የዘጋውን ደለል ለማንሳት እንደሚሰራ አስታውቆ ነበር፡፡

ይሁንና ይህ የመፍትሔ አማራጭ እየቀመነመነ ላለው ሐይቅ ዘግይቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የሆነው አነስተኛ ፕሮግራም ፕሮጀክት (Small Grants Program ) እንዳመለከተው ሐይቁ ከ50 በመቶ በላይ ውሀውን አጥቷል፡፡

“ሐይቁ አለምአቀፋዊ ጠቀሜታ ያለውና በአለም ላይ የጂፔ ዝርያ የሚገኝበት ብቸኛ ቦታ እና በመጥፋ ላይ የሚገኝም ነው” ይላል ፕሮጀክቱ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በላይ ማረስ፣ የደን መጨፍጨፍ እና አረም ሐይቁ በደለል እንዲሞላ ላደረገው ለአፈር መሸርሸር ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን ተመራማሪዎች ከመጠን ይገልጻሉ፡፡  

ሐይቁ የሚገኝበት የታቬታ ክፍለ ግዛት በ1960ዎቹ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል በተዋወቀው አረም አትክልቶቿ የተወረረባት አንደኛዋ ግዛት ናት፡፡

የሐይቁ ደለል ደግሞ ታይፋ ዶሞጌኒስ የተባለውና የሐይቁን 60 በመቶ የሚገመተውን ክፍል የሸፈነው የአረም ቅጠል እንዲባባስ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

“አረሙን የሚስያፋፉ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ካልተደረገ የታይፋ አረም መስፋፋትን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች ውጤታማ አይሆኑም” ሲልም መረጃው ጠቁሟል፡፡

 

የጋራ ሐይቅ እንዲ የጋራ ያልሆነ ኃላፊነት

የአካባቢው ህብረተሰብ ለመጥፋት የተቃበውን ጂፔ ቲላፒያን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች ደግሞ በሁለቱም ሀገሮች ዘንድ እየተመናመነ ያለውን ሐይቅ ለማዳን ስትራቴጂዎችን መንደፍ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

“ሐይቁን ለማስተዳደር የገጠመን ከፍተኛ ፈተና ይህ ነው፡፡ ይህ በጋራ የሚጠቀሙት የውሀ አካል ነው፡፡ ስለዚህ ሐይቁን ለመጠበቅም ደግሞ የጋራ የሆነ አጀንዳ ሊፈጠሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ሐይቁን ለማስተዳደር የጋራ የሆነ ጥረት ያስፈልገናል፡፡ አንዱ ሀገር ብቻ ሊሰራ አይችልም” ይላሉ ዶክተር ምሻና፡፡ 

በ2013 ላይ የኬንያ እና ታንዛኒያ ባለስልጣናት ሐይቁን ልክ እንደ ቪክቶሪያ ሐይቅ ሁሉ በጋራ ለመጠበቅ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፈርመው ነበር፡፡ 

ከሰባት አመት በኋላ ታዲያ ሰነዱ ገና አልተጠናቀቀም፡፡ 

በ2015 ሐይቁን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ያካሔዱት ዶክተር ምናሻ በሰጡት አስተያየት፤ የመግባቢያ ሰነዱ መጓተት በሐይቁ ላይ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት ድጋፍ እንዳያደርጉ አግዷቸዋል ብለዋል፡፡

 

“ከድጋፍ ሰጪዎቹ መካከል አንዱ ተቋም የገለጸልን የጋራ በሆነ ሐብትን በተመለከተ በታንዛኒያ በኩል ብቻ በሚቀርብልን ጥያቄ መሰረት ድጋፍ ልናደርግ አንችልም የሚል ነው፡፡ በኬንያና በታንዛኒያ በኩል በጋራ የቀረበ ጥያቄ ካልቀረበልን በስተቀር ገንዘብ ልንሰጣችሁ አንችልም ብለውናል” ይላሉ ዶክተር ምናሻ፡፡

“አሳው ትልቅ እና ወፍራም በነበረበት ጊዜ በቀን እስከ 300 ሽልንግ አገኛለሁ፡፡ ይህ ቤተሰቤን ለማስተዳደር በቂ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ከሐይቁ የሚገኘው አሳ በጣም ህጻን ሲሆን በ100 ሽልንግ ነው የምሸጠው” ትላለች አሳ አጥማጁ ሻፋራኒ፡፡

“ታዲያ አራት የልጅ ልጆቼን ይዤ በ100 ሽልንግ ምን ላደርግበት እችላለሁ?” ስትልም ትጠይቃለች፡፡

ምስጋና፡ ይህ ዘገባ የተጠናከረው ከኢንፎናይል (InfoNile)ጋር በመተባበር ከኮድ ፎር አፍሪካ እ ከጄአርኤስ ባዮዳይቨርስቲ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts