በክሌሜንቲኔ ኡዊማና
ኪጋሊ፡ በኪጋሊ ከተማ በምትገኘው ምዌንዶ መንደር የምትኖረው ፋጡማ ሙካሙዴንጌ ከመኖሪያ ቤቷ በእግር ጉዞ 45 ደቂቃ ርቆ ከሚገኘው ከንያባሮንጎ ወንዝ ውሀ ለመቅዳት ለአመታት ስትታገል ቆይታለች፡፡
ከቅርብ ወራቶች ወዲህ በኪጋሊ በርካታ መንደሮች ለመጠጥ፣ ለምግብ ማብሰያነት፣ ለልብስ እጥበት፣ እና ለሌሎችም የቤት ውስጥ አገልግሎቶች የሚውለው የውሀ ፍላጎት እያደገ መጥቷል፡፡ የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ፋጡማ፤ ቀን ላይ የረጅም ሰልፍ ወረፋን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን ከመጠበቅ ለመገላገል ውሀ ለመቅዳት ማልዳ ነው ወደ ወንዙ የምትሔደው፡፡
“አስቸጋሪውን የውሀ እጥረት ለመቋቋም የምንጭ ውሀን በመጠቀም የአካባቢው ነዋሪዎች ስንታገል ቆይተናል” ትላለች ሙካሙዴንጌ፡፡
የመንደሪቱ ነዋሪዎች ለእለት ፍጆታቸው የሚሆን ውሀ ለመቅዳት በተመረጡ ጥቂት የውሀ መውሰጂያ ቦታዎች ተሰልፈው ይውሉ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ምዌንዶ ያሉ መንደሮች ንጹህ የቧንቧ ውሀ በየጊዜው እየቀነሰ የውሀ አቅርቦት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ነዋሪዎች በአጎራባች ምንጮች እና በጥቂት የውሀ ጉድጓዶች ላይ ጥገኛ መሆን ጀመሩ፡፡
እንደ ምዌንዶ ያሉ ብዙ የከተማ መንደሮች የውሀ እጥረት በከፊል ተያይዞ የቆየው በኋላ ቀር የውሀ ማከፋፈያ ኔትወርክ እና ህገ-ወጥ ዝርጋታዎች የተነሳ ፍሳሽ በመፈጠሩ በተከሰተ የውሀ መጥፋት ነው፡፡
ይህንን እጥረት ለመፍታትም የስራ ኃላፊዎች በከተማ አካባቢዎች የውሀ አቅርቦት ለማሳደግ የሚያስችሉ 2.000 እና 10.000 ኪውቢክ ሜትር ውሀ የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት ትልልቅ የውሀ ማከማቻዎችን ለመገንባት አቅደዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ባለ 200 ዲያሜትር የውሀ ቱቦዎች በመዳከማቸውና በመሆናቸውና እና የወቅቱን የውሀ ፍላጎት ማሟላት ስለማይችሉ የውሀ ቱቦዎች ለመለወጥ ማቀዱን የመንግስት ተቋም የሆነው የወተር ኤንድ ሳኒቴሽን ኮርፖሬሽን (WASAC) ሀላፊዎች አስታውቀዋል፡፡
የከተማ ህዝብ ብዛት እድገት
የርዋንዳ ዋና ከተማ የሆነችው ኪጋሊ በ2012 ላይ 1.3 ሚሊዮን የነበረው የህዝብ ብዛት ቁጥሯ በ2020 ወደ ሁለት ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋዊ የስታስቲክስ መረጃ ያመለክታል፡፡
የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የስራ ሀላፊዎች እና የአካባቢ ጥበቃ ባለሞያዎችም የህዝብ ብዛት እድገት እና የከተማዋ መስፋፋት አሁን ባለው መሰረታዊ የውሀ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን ይስማማሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የተወሰኑ የማሻሻያ ቁሳቁሶች በኪጋሊ የሚገኙ የከተማ ነዋሪዎችን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ከእነሱም መካከል አንደኛው በቀን 40,000 ኪውቢክ ሜትር ውሀን ያወጣ የነበረውና ወደ 65,000 ኪውቢክ ሜትር ውሀ የማውጣት እንዲችል የተደረገው ንዞቬ አንድ (Nzove I) ተጠቃሽ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በቀን ከ25,000 ኪውቢክ ሜትር ወደ 40,000 ኪውቢክ ሜትር ውሀ እንዲያወጣ ባለፈው ዲሴምበር ወር ላይ የተሻሻለው ንዞቬ ሁለት (Nzove II) ነው፡፡
የርዋንዳ የከተማ ህዝብ ብዛት ቁጥር ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ብዛት 17.3 በመቶውን የሚይዝ ሲሆን፤ በየአመቱም በ3.6 በመቶ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ የውሀ አቅርቦት መጠን ሊጨምር አለመቻሉን ነው ይፋዊ መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡
በርዋንዳ ኢንቫይሮመንታል ማኔጅመንት ባለስልጣን በውሀ ጥራት ላይ የተካሔደ የቅርብ ጊዜ ጥናት የውሀ ጥራት ጉዳይ የሀገሪቱ ትልቅ ጉዳይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በኪጋሊ በ2005 እና በ2020 ባሉት ጊዜያት የውሀ ፍላጎት መጠን እጥፍ ያደገ ሲሆን፤ በከፊል ከተማ አካባቢዎች ደግሞ ደግሞ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፡፡
በአየር ንብረት ላይ የተዘጋጀ የመረጃ ቋት እና ደረጃቸውን የጠበቁ የከተማ ጠቋሚዎች ሳይኖሩ ለኪጋሊ ከተማ እና ለሌሎች የተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ከተሞች ከህዝብ ብዛት እድገት ጋር ቀጥታ የሚያያዘው የውሀ ሀብት አቅርቦት ጫናን መቋቋም ከፍተኛ ፈተና እየሆነ መጥቷል፡፡
በርዋንዳ ቤቶች ባለስልጣን ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት 48,000 መኖሪያ ቤቶች የከተማ አስተዳደሩን የውሀ አቅርቦት ከማግኘት በታገዱ ከፍተኛ አደጋ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የተገነቡ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹም ጥሩ መኖሪያ ቤት መከራየት በማይችሉ አነስተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች የተያዙ ናቸው፡፡
በኪጋሊ እጅግ ጥቂት ነዋሪዎች ከውሀ ሲስተም ጋር የተገናኘ ቧንቧ ያላቸው ሲሆን፤ መረጃዎች እንደሚሳዩትም 70 በመቶ የሚሆኑት የከተማዋ ነዋሪዎች ከ220 ሜትር ባነሰ ቦታ ውሀ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከተፈጥሮ ምንጮች ውሀ ለመቅዳት ረጅም የእግር ጉዞ ማድረግ አሁንም የተለመደ ነው፡፡ ከውሀ ወለድ በሽታዎች ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችም መቀጠላቸውን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
በውሀ ማጣሪያዎች ላይ የተፈጠሩ ጫናዎች
የአየር ንብረት ለውጥም እንዲሁ ለውሀ አቅርቦት ችግር ዋንኛ ምክንያት እንደሆነ ከርዋንዳ መንግስት ጋር በመተባበር በንጹህ ውሀ አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ የሚሰራው መንግስታዊ ያልሆነው አለምአቀፍ ድርጅት የወተር ኤይድ ባለሞያ በሀይሉ ሽፈራው ይናገራሉ፡፡
በገጠር አካባቢዎች የነበረው የህዝብ ብዛት ቁጥር መጨመር በስራ ፍለጋ ምክንያት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ከተሞች አካባቢ መለወጡ የተወሰኑ መንደሮችን ለተፈጥሮ ሀብቶች መራቆት አደጋ ገጥሟቸዋል፡፡
ርዋንዳ በመላ ሀገሪቱ በሚፈሱ ትልልቅ ወንዞቿ የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡ ነገር ግን የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ የሆነ የዝናብ መጠን እና ከፍተኛ ጎርፍን አስከትሏል፤ አገልግሎት የሚሰጡት የውሀ ማጣሪያዎችም በከፍተኛ ድፍርስ ውሀ ተሞልተዋል፡፡ ይህም ለውሀ ማጣሪያ የሚወጣውን ወጪን የሚጨምር መሆኑን የርዋንዳ ውሀ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ዋና ኦፊሰር ኤይሜ ሙዞላ ይገልጻሉ፡፡
በቅርብ ወራት ውስጥ የኪጋሊ ዋንኛ የውሀ ምንጭ የንያባሮንጎ ወንዝ የላይኛው የውሀ ማከማቻዎች ከፍተኛ ጎርፍ አስተናግደዋል፡፡ የንዞቬ እና ኪሚሳጋራ ውሀ ማጣሪያ ማሽኖች የውሀ ምርት በግማሽ እንዲቀንስ አድርጓል፡፡
“የንያባሮንጎ የላይኛው ተፋሰስ እና የውሀ ማከማቻዎች ከአፈር መሸርሸር የተከለሉ ባለመሆናቸው አፈር እና ጭቃ በጎርፍ ተወስደው ወደ ንያባሮንጎ ወንዝ ይገባሉ፡፡ ወንዙም በጣም ጭቃማ ይሆናል” የሚሉት ሙዞላ፤ “ይህ ችግርም የኪጋሊ ከተማ የውሀ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር በመፍጠር ተጠቃሽ ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡
በርዋንዳ ዩቲሊቲስ ሬጉላቶሪ ባለስልጣን በተባለ የመንግስት ተቋም በቅርቡ ይፋ በሆነ መረጃ ላይ ምንም እንኳን በከተሞች አካባቢ የውሀ ፈላጊ አመልካቾች ቁጥር በቅርብ አመታት ውስጥ በአንጻራዊነት ቢጨምርም የሚመረተው የውሀ መጠን ቀንሷል፡፡
በዲሴምበር 2019 ላይ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በየጊዜው የህዝብ ብዛት እየጨመረ በሚገኝባት በኪጋሊ ከተማ በየቀኑ የሚያስፈልገው የውሀ መጠን ቢያንስ 120,000 ኪውቢክ ሜትር ነው፡፡
የከተማ ማስተር ፕላኖች
ርዋንዳ በአሁኑ የከተማዋ የውሀ አቅርቦት ማሻሻያ አጀንዳ ላይ በ2020 የከተማ የውሀ ሽፋን መጠንን 100 ፐርሰንት ለማሟላት ነው ያቀደችው፡፡
ይሁንና በከተማ አካባቢዎች የውሀ አቅርቦት አሰራር ኋላቀር በመሆኑ ሀገሪቱ ፍላጎቷን ባለማሳካቷ የኪጋሊ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀላፊዎች አዲስ የውሀ አቅርቦት ማስተር ፕላንን በዚህ አመት አዘጋጅተዋል፡፡ በህዝብ ዘንድ እየጨመረ የመጣው ጥራቱን የጠበቀ ውሀ የማግኘት ፍላጎትን በ2021 ለማሟላት በጀት እንደሚያሰራጭ ይጠበቃል፡፡
የኪጋሊ ከተማ ነዋሪዎች በየቀኑ ለረጅም ሰአት የውሀ መቋረጥ ችግር ማስተናገዳቸውን በቀጠሉበት ጊዜ፤ የርዋንዳ መንግስት እና አጋሮች በዚህ አመት የውሀ እጥረትን በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ለማቅረፍ እስከ 300ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ይፋ አድርገዋል፡፡
እንደ ጃፓን ኢንተርናሽናል ኮኦፖሬሽን (ጃይካ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ካሉ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚተገበረው አዲሱ የውሀ አቅርቦት ማስተር ፕላን፤ በከተማ ህዝብ ብዛት የሚፈለገው የውሀ መጠን በመኖሪያ ቤቶች ቶፖግራፊ ስትራክቸር ጋር የተስማማ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በኪጋሊና ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ መዋለ ንዋይ ማፍሰስን ይፈልጋል፡፡
እስከ አሁን ድረስም መንግስት ለሁለተኛ ከተማነት ስድስት አረንጓዴ የከተማ ቦታዎችን ለይቷል፡፡ እነርሱም ሁዬ (በደቡብ)፣ ሙሃንጋ (በመሀል ደቡብ)፣ ንያጋታሬ (በሰሜን ምስራቅ)፣ ሩባቩ (በሰሜን ምዕራብ)፣ ሙሳንዜ (በሰሜን) እና ሩሲዝ (በደቡብ ምዕራብ) ናቸው፡፡
በርዋንዳ መንግስት ቤቶች ባለስልጣን ግሪን ኤንድ ስማርት ሲቲ ዴቨለፕመንት ኤክስፐርት የሆኑት ፓረፌይት ካሬኬዚ እንደሚያስረዱት፤ የዚህ አዲስ ስራ ዋንኛ ትኩረት ለነዋሪዎች በቂ ውሀ እና የንጽህና አቅርቦቶችን ያሟሉ አቅምን ያገናዘቡ ቤቶችን ያሏቸው ሁለተኛ ከተሞችን ማሳደግ ነው፡፡
በመንግስትና በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግለት የአሁኑ ጥረት በሁለተኛ ደረጃ ከተሞች የመኖሪያ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው እንዲሰሩ የስራ ሀላፊዎችን ያግዛል፡፡ ለአብነት ያህልም መስኮቶች በኤሌትሪክ ብርሀን ሀይል ቁጠባን መስጠት የሚችሉ ተገቢ ዲዛይን ያሟሉ..
“የሁለተኛ ከተሞች ማስተር ፕላኖች የሚተገበረው አዲሱ አቀራረብ በመጠጥ ውሀ ማጣሪያ ማሽን ዲዛይን እና አለቃቅ ላይ ያሉ አሉታዊ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ነው” ሲሉ ካሬኬዚ ያስረዳሉ፡፡
እንደ ርዋንዳ የስራ ሀላፊዎች ገለጻ፤ ይህ ማስተር ፕላን የርዋንዳን የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ግንባታን ያግዛል፡፡ ይህም ለሁሉም የከተማ ነዋሪዎች የውሀ አቅርቦትን በፍጥነት ለማድረስ አነስተኛ ከሆነው አማራጭ የራቀ ነው፡፡
አሁን፤ ነዋሪዎቿ እየጨመረ በመጣው የውሀ እጥረት ቅሬታ የሚያነሱባት የኪጋሊ ከተማ መንደር በሆነችው ማጌራጌሬ የሶስት ልጆች እና የሆነችው ጃኩሊን ሙካሙሶኒ፤ ከአጎራባች ወንዝ ውሀ ለመቅዳት ባለው ትግል በደረሰባት የጀርባ ጉዳት ለሶስት አመታት ስትሰቃይ ቆይታለች፡፡
“ለመንደራችን ውሀ ለማቅረብ የሚገቡ ቃልኪዳኖችን መስማት ሰልችቶናል” ትላለች፡፡
ሙካሙሶኒ ከአጎራባች ወንዝ ከንያባሮንጎ ወንዝ ውሀ ለመቅዳት በየቀኑ ከሁለት እስከ አራት ጊዜ የምትመላለስ ሲሆን፤ በእያንዳንዱ ጊዜም በጭንቅላቷ 15 ሊትር ውሀ ትሸከማለች፡፡