የመስኖ ቴክኖሎጂ በታንዛኒያ

የመስኖ ቴክኖሎጂ በታንዛኒያ

በአኒ ሮቢ

መሀመድ ሙሳ በታንዛኒያ ሞሮጎሮ ክልል የረጅም አመት ነዋሪ ነው፡፡ ወጣቱና ታታሪው ልጅ ኑሮውን ለማሸነፍ በዝናብ ጠገብ መሬቶች ላይ ጥገኛ በመሆን ቲማቲም እና ካሮት ያመርታል፡፡

አሁን ላይ ግን የሙሳን ሰብሎች የታደገው ዝናብ እንደከዚህ በፊቱ ሊመጣ አልቻለም፡፡ የዝናብ ወቅቶችን በማዘግየትና ቆይታውንም አጭር በማድረግ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ሲያደርሱ፤ ለብዙ አመታት ህይወቱን ያቆየበት የቲማቲምና ካሮት ምርት ሊቀንስ ችሏል፡፡ 

“ባለፉት ጊዜያት ጥሩ ዝናብ እናገኝ ስለነበር የቲማቲም እና ካሮት እድገትም ጥሩ ነበር፡፡ አመቱን ሙሉ አመርት ነበር፡፡ አሁን ግን በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የተነሳ የማመርተው ምርት መጠን በየጊዜው እያነሰ ነው” ይላል ሙሳ፡፡

አሁን ላይ በምርት ወቅቶች እንኳ ዝናብ በመጥፋቱ ሙሳ ሐሩርን መቋቋም የሚችሉ እንደ ሰብሎችን ወደ ማምረት ተሸጋግሯል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን እንዴት መቋቋም እንደሚገባ መረጃ በማጣቱም፤ ሙሳ አሁንም ድረስ የሰብል ምርቶቹን እድገት መቋቋም የሚቻለው በዝናብ ብቻ እንደሆነ ያምናል፡፡

“ምንም እንኳ ውሀማ መሬቶችን ጠብቆ ለማቆየት የተለያዩ ልማዳዊ መንገዶችን ብጠቀምም፤ ጥሩ ምርት ማግኘት የምችለው ግን በዝናባማ ወቅቶች ብቻ ነው” ይላል፡፡

በታንዛኒያ ሞሮጎሮ ክልል በርካታ መንደሮች ላይ በዚህ ዘጋቢ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በአነስተኛ ግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ብዙ ገበሬዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የሚመርጡት ልማዳዊውን መንገድ ነው፡፡ ለአብነት ያህልም መሬቱ ውሀ ይዞ እንዲቆይ የሚያደርገውን ፍግ በመሬቱ ላይ ይጠቀማሉ፡፡

ይሁንና እንደዚህ ያሉ ዘዴዎች በአካባቢው ለገጠመው ወቅታዊ ለውጦች መፍትሔ እንዳልሆኑ የሚናገሩት በሞሮጎሮ ክልል የምሊማን መንደር የአካባቢ ገበሬዎች ማህበር ሰብሳቢ ሀጂ ምካንዳኖግዋ ናቸው፡፡

“ተጠባቂ የዝናብ ወቅቶች በመቅረታቸው የተነሳ አብዛኞቹ ገበሬዎች እንደ ቲማቲም፣ ካሮት፣ አትክልቶች እና ሌሎች የእጽዋት ሰብሎችን አይነት ፍሬ ለመያዝ ብዙ ውሀ የሚፈልጉ ሰብሎችን ማምረት አቁመዋል” በማለትም ያስረዳሉ፡፡

የአካባቢው ገበሬዎች የሰብል እህሎችን ለማምረት የሚያስልጋቸውን ውሀ እንዲያገኙ የግብርና ባለሞያዎችና መንግስት እገዛ እንዲኖር ምካንዳኖግዋ ይመኛሉ፡፡

ግብርና የታንዛኒያ ምጣኔ ሀብት የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ሶስት አራተኛ ለሚሆነው ለሀገሪቱ ህዝብ በተለይም በአነስተኛ የግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ገበሬዎች የመተዳደሪያ ምንጭ ነው፡፡ ሀገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች 15 በመቶ ያህሉን የሚይዝ ሲሆን፣ ለታንዛኒያ አመታዊ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ገቢ 27.8 በመቶው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

ነገር ግን የአየር ንብረት ለውጥ በዘርፉ ቀጣይነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ሆኗል፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአለምአቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ለሰብሎች ምርት የሚያስፈልገውን የውሀ ሀብቶችን እየቀነሰ ነው፡፡ በታንዛኒያም የአካባቢው ገበሬዎች ተጽዕኖውን በደንብ መረዳት ጀምረዋል፡፡

Tomato farm

የመስኖ ቴክኖሎጂ- በመተግበር ላይ ያለ መፍትሔ

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በውሀ የማምረት ቴክኖሎጂ በኩል የሚካሔደው አነስተኛ የመስኖ ልማት ለገበሬዎች የግብርና ምርትን ለማሳደግ፣ የምግብ ደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ እና ድህነትን ለመቀነስ ያግዛቸዋል፡፡ በውሀ የማምረት ቴክኖሎጂዎች ገበሬዎች የዝናብ ውሀን እንዲያከማቹና ጠብታ ውሀን በዝግታ እና በቀጥታ ለሰብሎቹ እንዲደርስ በሚያስችለው በአነስተኛ የመስኖ ቴክኖሎጂ ዘዴ እንዲጠቀሙቡት ያደርጋቸዋል፡፡

እነዚህ ቴክኖሎጂዎች እንደ ሙሳ ላሉ በአነስተኛ ደረጃ ላሉ ገበሬዎች ዝናብ በማይተነበይበት ጊዜ እንኳን በልማዳዊ መንገድ የሚያመርቱት ሰብሎችን ለማሻሻል እና ለማሳደግ የሚያስችላቸው አማራጮች ናቸው፡፡ ይሁንና እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በሞሮጎሮ ክልል እስከአሁን ተግባራዊ ያደረጉት ገበሬዎች ጥቂት ናቸው፡፡ 

የአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) (ፋኦ) እና ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ፎር ቴክኖሎጂ ኤንድ ሪሰርች ኢን ኢሪጌሽን ኤንድ ድሬኔጅ (IPTRID) የተባሉት አለምአቀፍ ድርጅቶች አነስተኛ ወጪና አመርቂ የውሀ አጠጣጥ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች አነስተኛ ዘርፍ የመስኖ ውሀ አጠጣጥ ዘዴን በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የመስፋፋት እድል እንዳላቸው፤ በተለይም ደግሞ የምግብ ደህንነት እና የቤተሰብ ገቢዎችን እንደሚያሻሽሉም መለየት ችለዋል፡፡ 

በአለም ላይ የመስኖ ውሀ አጠጣጥ በዝናብ ከሚለማ እርሻ ሶስትና አራት እጥፍ የበለጠ የሰብል ምርትን ይጨምራል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ፣ ኬንያ እነዚህን ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ስኬታማ ታሪክ አላት፡፡ በሀገሪቱ አጋዥ የመስኖ ውሀ አጠቃቀም የገበሬዎችን ህይወት ወደ የንግድ ወኪልነት ለውጧል፡፡ 

ኬንያ በተሻሻለ የመስኖ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት አነስተኛ ግብርናን ለማስተዋወቅ የገጠማት እድሎችና ፈተናዎች ለሌሎች ሀገሮች እና ለለጋሽ ማህበረሰብ ከዚህ “አዲስ መንገድ” ጋር እንዴት መቀጠል እንደሚቻል ጠቃሚ ትምህርቶችን ሰጥቷል፡፡     

በታንዛኒያ የገበሬዎች የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ልምድ አነስተኛ ነው፡፡ ይሁንና የታንዛኒያ መንግስት በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች በአነስተኛ ደረጃ ለተሰማሩ ገበሬዎች ምርታቸውን ለማሳደግ የአነስተኛ ደረጃ መስኖን የመተግበር እቅድ አውጥቷል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ታንዛኒያ 2,678 የመስኖ ቦታዎች ሲኖራት፤ አንዳንዶቹ ምርታማ አለመሆናቸውን የግብርና ሚንስትሩ ጃፌት ሀሱንጋ ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ የመስኖ ፖሊሲ እንደሚገልጸው ለዘላቂ የመስኖ አጠቃቀም ልማት ታንዛኒያ ተለይተው የታወቁ ወደ 29.4 ሚሊዮን ሄክታር ምርታማ ቦታዎችን በማልማት መጠቀም ይኖርባታል፡፡ 

ሀሱንጋ ለዴይሊ ኒውስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገበሬዎች ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ምርታቸውን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው ለማሳየት ሞዴል የመስኖ ቦታዎች በመላው ሀገሪቱ ይዘጋጃሉ፡፡

a section of mliman farming areas for local farmers in Moro

“በአነስተኛ የግብርና ስራ ለተሰማሩ ገበሬዎች የሰርቶ ማሳያ መሬት ሆኖ እንዲያገለግል የመስኖ ቦታዎችን በእያንዳንዱ አካባቢ እናዘጋጃለን” ብለዋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቅጣጫዎች በዝቅተኛ ወጪ በውሀ የማምረት ቴክኖሎጂ አማካኝነት አነስተኛ የመስኖ አጠቃቀምን ማስተዋወቅን ያካትታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሚንስቴሩ የብሔራዊ መስኖ አጠቃቀም ኮሚሽንን በመከለስ በወረዳ ደረጃ የመስኖ ቦታዎችን አስተዳደርን የሚመራ አዲስ አሰራርን እንዲፈጥር ወስኗል፡፡

ይህም በየወረዳው የመስኖ ኦፊሰሮችን ማብቃትና እና የመስኖ ሴክሬተሪያት ቢሮዎችን በክልል ደረጃ መመስረትን ይጨምራል፡፡

“ምልከታችን በሀገሪቱ ለዘላቂ የመስኖ ልማት አዋጪ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየትና ለማልማት ይመራል” ብለዋል፡፡

እቅዶቹን ተግባራዊ ለማድረግም መንግስት በአሁኑ ወቅት ለጋሾችንና የልማት አጋሮችን የገንዘብ ድጋፍ እየጠየቀ እንደሆነ ሀሱንጋ አስታውቀዋል፡፡ 

በዳሬ ሰላም ዩኒቨርስቲ የአካባቢ እና አየር ንብረት ለውጥ ኤክስፐርት የሆኑት ፒዩስ ያንዳ የመንግስትን ለገበሬዎች አነስተኛ ዘርፍ መስኖ አጠቃቀምን የማሳደግ እንቅስቃሴን አድንቀዋል፡፡

“መስኖ በታንዛኒያ በጣም አስፈላጊ ሀሳብ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚን ለማሳደግ በተነሳችበት ጊዜ የመስኖ አጠቃቀም ምርትን ለመጨመር አስፈላጊ ነው” ሲሉ ያንዳ ይናገራሉ፡፡

“መንግስት አነስተኛ የመስኖ ቦታዎች ከ10 እስከ 20 አመታት ውሀ ለማምረት የሚያስችሉና ዘላቂ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ስትራቴጂዎች ሊኖሩት ይገባል፡፡

“በቀጣይ ተግባራዊ የሚሆነው የመስኖ አጠቃቀም የወደፊቱን የአየር ንብረት ለውጥ ውጤቶችን የሚበተነብይ የመስኖ እቅድ መሆን አለበት” በማለትም አሳስበዋል፡፡

ምግብ እና ግብርና ድህነትንና ርሀብን ከማስቀረት ጀምሮ ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ መስጠትና የምድርን የተፈጥሮ ሀብቶችን እስከ መጠበቅ ድረስ በ2015 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተዘጋጀው የ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳ ማዕከል ናቸው፡፡ 

ግብ 2(2.) ላይ የሰፈረው ጥሪ በ2030 አለም የግብርና ምርቱን በእጥፍ እንዲያሳድግና የአነስተኛ የምግብ አምራች ገበሬዎችን ገቢ በተለይም ደግሞ የሴቶችን፣ የሀገሬውን ህዝብ፣ የቤተሰብ ገበሬዎችን፣ አርብቶ አደሮችንና አሳ አርቢዎችን ገቢ በእጥፍ እንዲያሳድግ ነው፡፡ ይህም የሚተገበረው “አስተማማኝና እኩል መሬት የማግኘት እድል፣ በሌሎች ምርታማ ሀብቶች እና ግብዐቶች፣ በእውቀትና የገንዘብ አገልግሎት ነው” 

የታንዛኒያ መንግስት ለየክኖሎጂ ትግበራ እና አነስተኛ መስኖ የዘላቂ ልማት አጀንዳን እንዲያሳኩና እና የአብዛኛውን ህዝብ ኑሮ እንዲያሻሻል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና አለው፡፡ 

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts