ስደተኞች የአየር ንብረትን ለመከላከል የሰው ልጅ ውጋጅን ወደ አማራጭ ሀይልነት ቀይረዋል

ስደተኞች የአየር ንብረትን ለመከላከል የሰው ልጅ ውጋጅን ወደ አማራጭ ሀይልነት ቀይረዋል

በሮበርት አሪያካ

በአሩራ ዲስትሪክት የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ሴቶች ቡድን ከሰው ልጅ ከሚወጣ ደረቅ ቁሻሻ የተዘጋጀውን የከሰል ጡቦችን እንደ ማገዶ እንጨት እና ከሰል ሆኖ የሚያገለግል የጡብ ከሰልን ያመርታሉ፡፡ 

‹‹የከሰል ጡብ ከሰው ከሚወጡ ደረቅ ቁሻሻ (ሰገራ) የሚሰራ ሲሆን፤ ከእንጨት እሳት ጋር ሲነጻጸር ለማብሰል በጣም ቀላልና ለ8 ሰአታት እየነደደ የሚቆይ ነው›› በማለት የምታስረዳው ቁሻሻን ለማብሰያነት መለወጥ የቻለው የሎኬታ ሴቶች ቡድን አባል የሆነችው ወጣቷ ሮዳ ሴልዋ ናት፡፡

Tabu Regina the secretary Loketa women group in Ariwa village in Rhino Camp explains how they make briquettes using crop residues and human waste Photo By Robert Ariaka

የሎኬታ ሴቶች ቡድን በኦክስፋም ካናዳ አማካኝነት የጡብ ከሰልን የመስራት ስልጠናን አግኝተው ካተረፉ በሪህኖ መጠለያ፣ በኢምቬምቢ፣ በኡሙጎ እና ቢዲቢዲ የሥደተኞች መጠለያዎች ከሚገኙ አምስት ቡድኖች አንዱ ነው፡፡ 

ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው ከሰብል ተረፈ ምርቶች ከተገኙ ደረቅ ቁሻሻዎች የጡብ ከሰልን መስራት ላይ ነበር፡፡ ይሁንና ሴቶቹ በኬንያ ናኩሩ ስልጠናን ከተካፈሉ በኋላ ከሰው ልጅ የሚወጣን ደረቅ ቁሻሻን ወደ ጡብ ከሰልነት ለመቀየር የሚያስችል አዲስ ክህሎትን መልመድ ችለዋል፡፡

በሪህኖ ካምፕ አሪዋ መንደር የሚገኘው የሎኬታ ሴቶች ቡድን ጸሐፊ የሆነችው ታቡ ሬጂና እንደተናገረችው ቡድኑ የሰብል ተረፈ ምርትና የሰው ልጆች ውጋጅን በመጠቀም የጡብ ከሰልን ለመስራት ከኦክስፋም ድጋፍ አግኝቷል፡፡

የጡብ ከሰል የሚሰራው ከማሽላ አገዳ፣ ከሰሊጥ አገዳ፣ ከባቄላ አገዳ እና ከሙዝ ቅጠሎች ነው፡፡ ‹‹መጀመሪያ ተረፈ ምርቶቹን እናቃጥላቸዋለን፣ ወደ ጥቁርነት ሲለወጥም በማሽኖች ይሰባበራል፤ ጡብ ከሰል እንዲሆንም ከፉርኖ ዱቄት ከተሰራ ገንፎ ጋርም ይደባለቃል›› ስትል ሬጂና አሰራሩን ታስረዳለች፡፡

በኦክስፋም በማህበረሰብ ጤና ፕሮሞተርነት የሚሰራው ራሺድ ማዌጄ ለስደተኛ ሴቶቹ ለስልጠና እና አስፈላጊ ለሆኑ ድጋፎች 373.3 ሚሊዮን ሽልንግ ማውጣታቸውን አስታውቋል፡፡

ማዌጄ እንደገለጸው ኦክስፋም የጡብ ከሰል ስራ ላይ ለተሰማሩ አምስት የስደተኛ ሴቶች ቡድን ድጋፍ አድርጓል፡፡ 

‹‹ደረቅ የሰብል ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ማዋል የመጀመሪያው መነሻችን ነበር፡፡ አሁን ግን ሴቶቹ የሰው ልጆች ደረቅ ቁሻሻን ወደ ጡብ ከሰል የመለወጥ ስራን እየሰሩ ነው›› ይላል ማዌጄ፡፡

ሬጂና በበኩሏ ስራቸው በሚስፋፋበት ጊዜ የጡብ ከሰል የዛፎች መቆረጥን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃ እንደሚረዳ ተስፋ ታደርጋለች፡፡

Mary Ajonye the chairperson of Loketa women group explains how the Charcoal Briquettes are made in different sizes ranging from the smollest to the biggest Photo By Robert Ariaka

መንግስት በስደተኞች መጠለያዎች የጡብ ከሰልን መስራት ከጀመሩና የአየር ንብረትን ለመከላከል ወጣቶችና ሴቶችን በብዛት በማሰልጠን በትብብር ለሚሰሩ ቡድኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቃለች፡፡ 

በየቡድኖቹ ውስጥ የሚገኙት ወጣቶች፣ ጎልማሶች እና ትልልቅ ሰዎች የተዋሀደው ንጥረ ነገር መጣበቁን ለማወቅ እጃቸውን ነው የሚጠቀሙት፡፡ ዝግጁ ሲሆንም ሴቶቹ ከትንሽ እስከ ትልቅ በተለያየ መጠን የጡብ ከሰል እንዲሆን ያጣብቁታል፡፡ 

ከደረቅ ተረፈምርት የጡብ ከሰል ባሻገር ቡድኑ የታከመ ኩስን በመጠቀም የጡብ ከሰልን ወደ ማምረቱ ቢዝነስ ሔደዋል፡፡ ኦክስፋም የታከመውን ኩስ ከሊራ አምጥቶ ያቀርብላቸዋል፡፡ 

ሴቶቹ ምርታቸውን በመደበኛነት ለማቅረብ በቀላሉ የሰው ልጆችን ደረቅ ቁሻሻ አግኝተው የሚሰሩበትን ማሽን ኦክስፋም በስደተኞች ሰፈራዎች ውስጥ እንዲገነባላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የጡብ ከሰሉ ለገበያ የሚያቀርቡት በመሆኑ ማከማቻ እንዲሆናቸውም መጋዘን ኦክስፋም ገንብቶላቸዋል፡፡

ሴቶቹ የጡብ ከሰል ስራን በ2018 ነው የጀመሩት፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም የኢኮኖሚ ገቢያቸው የተሻሻለ ሲሆን፤ ገንዘብም ይቆጥባሉ፡፡

የቡድኑ አባላት ምርታቸውን ወደ መጠለያዎቹ ለሚመጡ ጎብኝዎች በተጨማሪ እዚያው መጠለያ ለሚገኙ ስደተኞች ምግብ በሚከፋፈልበት ጊዜ ይሸጣሉ፡፡ 

‹‹ከእንጨት ለቀማ ጋር በተያያዘ በሚፈጠሩ ችግሮች የተነሳ በአሁኑ ወቅት እንጨት ለመልቀም ወደ ጫካ አንሔድም፡፡ የተወሰኑ ሴቶች እንጨት ለቀማ በሔዱበት ጫካ ውስጥ የመደፈር ደርሶባቸዋል›› ስትል ሬጂና ትናገራለች፡፡

Neima Gaba resident of Ariwa village in Rhinocamp refugee settlement now uses uses Charcoal Briquettes for cooking Photo By Robert Ariaka

ግብርና እንደ ተጨማሪ የኑሮ መላ

ሰሊጥ በአካባቢው በስፋት የሚመረት የሰብል ምርት በመሆኑ ወደ ሰሊጥ ግብርና ስራ ገብተዋል፡፡ የሰብል ምርቱን ተረፈምርት ደግሞ ጡብ ለመስራት ይጠቀሙበታል፡፡

ሬጂና እንደተናገረችው የጡብ ከሰል አካባቢን የሚጠብቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ ዛፎችን መቁረጥ እንዲያቆምና የጡብ ከሰልን እንዲጠቀም ለማስተማር ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

በስደተኞች የሰፈራ አካባቢዎች የሚሰሩ አጋር አካላት ስደተኞች የዛፍ ችግኞችን እንዲተክሉና አካባቢን እንዲጠብቁ የዛፍ ችግኞችን የማከፋፈል ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቃለች፡፡

እንደ ሬጂና ከሆነ የጡብ ከሰል ዋጋው ርካሽ፣ ለረጅም ጊዜ የሚቀጣጠል እና ምግብ ለማብሰል በቂ ግለትን ማጠራቀም የሚችል ነው፡፡ የማብሰያ ድስትን ንጽህናንም የሚጠብቅ ነው፡፡

ዛፍ በመቁረጥ ከሰልን የማግኘት ሒደቱ አድካሚ እንደሆነም ሬጂና ትገልጻለች፡፡ ‹‹በከሰል ስራ የተጎዱ ሰዎችን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን የጡብ ከሰል እጅግ አነስተኛ ጥረትን ነው የሚጠይቀው›› ብላለች፡፡

የጡብ ከሰልን መስራት በስደተኞች መጠለያ ለሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩንም ተናግራለች፡፡ የሎኬታ የሴቶች ቡድን የጡብ ከሰል በመስራት ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ 40 አባላት አሉት፡፡ 

ሴቶቹ በቀን ውስጥ 300 በላይ የጡብ ከሰልን ይሰራሉ፡፡ በስደተኞች ጣቢያዎችና በምዕራብ ናይል አካባቢዎች ለገበያ ያቀርቡታል፡፡

Copy of Story 4 viz 2

በማህበር መቆጠብ

ከጡብ ከሰል ስራ የሚገኘው ትርፍ የቡድኑ አባላት ለቤት ውስጥ ፍላጎታቸውን፣ ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ እና የተረፋቸውንም በቪሌጅ ቁጠባና ብድር ማህበር  ለመቆጠብ ያግዛቸዋል፡፡

ቡድኑ ሰሊጥ ለማምረት መሬት የተከራየ ሲሆን፤ የሚያገኙትን ትርፍን ቁጠባቸውን ለማስፋት ይጠቀምበታል፡፡ የሰብል ተረፈ ምርትን ግን ብዙ የጡብ ከሰል ለመስራት ነው የሚጠቀሙበት፡፡ አባላቶቹ ከቁጠባቸው የሚበደሩ ሲሆን፤ ቁጠባውን ለማሳደግም በወለድ ይከፍላሉ፡፡

አንዳንድ የቡድኑ አባሎች ከቡድኑ ገንዘብ በመበደር ወደ ንግድ ስራ ገብተዋል፡፡ የቁጠባ ቡድኑ ላጤ እናቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችንና ባል የሞተባቸውንና ያገቡትንም ሴቶች ኑሮ አሻሽሏል፡፡

‹‹እንደ ቡድን እርስ በእርሳችን በፋይናንስም ሆነ በስነ ልቦና እንተጋገዛለን፡፡ ከተቋማት ከፍ ያለ የፋይናንስ ድጋፍ ማግኘትና የቡድናችን ቁጠባና የብድር አቅም ማሳደግ እንፈልጋለን›› ስትል ሬጂና ፍላጎታቸውን አስታውቃለች፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሁሉም የቡድኑ አባላት ብድር በሚፈልጉ ጊዜ ገንዘቡ በቂ አይሆንም፡፡ ለዚህም ነው መንግስት እና ተባባሪ አካላት ከፍ ያለ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሊደግፉና ቁጠባውን ሊያሳድጉ ይገባል ብላ የምትናገረው፡፡

በአሁኑ ወቅት ሬጂና በአሪዋ የውበት ሳሎን ያላት ሲሆን፤ ከቡድኑ 300.000 ሽልንግ በመበደር ነው የጀመረችው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በመንደሯ 9 ሰዎችን በመንከባከብ የንጽህና አጠባበቅ አስተዋዋቂ ሆና ትሰራለች፡፡ ቡድኑ የሚሳተፍባቸው ሌሎች ስራዎች የሹራብ ስራ፣ ዳቦ መጋገር እና ዶቃዎችን በዲዛይን መስራትን ይጨምራል፡፡ ምርቶቹንም በስደተኞች መጠለያ ለሚሰሩ የግብረሰናይ ድርጅቶች ሰራተኞች ይሸጣሉ፡፡

የቡድኑ ጸሐፊ ሜሪ አጆንዬ እንደምትናገረው የጡብ ከሰሉ በስፋት የሚካሔደውን የዛፍ ቆረጣ ድርጊትን ለመቆጣጠር አግዟል፡፡ በኩስ አማካኝነት የተዘጋጀው የጡብ ከሰል ለምግብ ማብሰያ እንጨትና ከሰል የምናወጣውን ወጪ ይቀንሳል፡፡

አጆንዬ እንደምትናገረው ከሆነ ምግባቸውን ለማብሰል የተዘጋጁ ሴቶች ያለምንም ተጨማሪ ነገር ከሰው ልጅ ደረቅ ቁሻሻ የተሰራ የጡብ ከሰልን በመጠቀም ቁርስ፣ ምሳ እና እራትንም ጭምር ማብሰል ይችላሉ፡፡

ሴቶቹ የጡብ ከሰልን ከ1.000 እስከ 3.000 ሽልንግ ይሸጡታል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ስራው ጫካ ውስጥ በእባብ ከመነደፍና ከአስገድዶ መደፈር አደጋ አድኗቸዋል፡፡

አጆንዬ በመምህርነት በምታገኘው ገቢ በአሩዋ ከተማ በሰር አንድሪው አንደኛ ደረጃ የአዳሪ ትምህርት ቤት ለሚማረው ልጇ ክፍያ ትፈጽማለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገቢዋን ከፍ ለማድረግ አነስተኛ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ መክፈት ችላለች፡፡

የሶስት ልጆች እናት የሆነችው አጆንዬ ተጨማሪ ሶስት ልጆችን በጉዲፈቻ ታሳድጋለች፡፡ ባለቤቷ ስራ ባይኖረውም ቤተሰቡን ማስተዳደር ችላለች፡፡ እርሱ ቤት ውስጥ ስራዎችን በመስራትና አነስተኛ ጓሮን በመንከባከብ ያግዛታል፡፡

በአሪዋ ፕራይመሪ ፒ 6 ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ጄኒፈር ካና ለኒው ቪዥን እንደተናገረችው ምግብ ማብሰያ እንጨት ለመግዛት የተሰጣትን የምግብ ራሽን ትሸጣለች፡፡

አንድ እስር እንጨት 3.500 ሽልንግ መሆኑን በመግለጽ የጡብ ከሰል ጠቀሜታ የተሻለ መሆኑን ታስረዳለች፡፡

የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ስደተኛዋ ነኢማ ጋባ በበኩሏ የጡብ ከሰል ከመተዋወቁ በፊት በማገዶ እንጨትና ከእንጨት ከሰል ላይ ጥገኛ እንደነበረች ትገልጻለች፡፡

‹‹ኦክስፋም የጡብ ከሰል ማሽንን ሲያስተዋውቅ፤ እንጨት መጠቀሙን እርግፍ አድርጌ ተውኩት፡፡ አሁን የምጠቀመው ከእንጨት በተሻለ ምግብ ለማብሰል ለረጅም ጊዜ የሚነደውን የጡብ ከሰልን ነው›› ስትል ጋባ ተናግራለች፡፡

የጡብ ከሰል ሴቶችን የማያጨናንቅና ምግቡ እየበሰለ ሌላ ነገር ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑንም ገልጻለች፡፡

Jenifer Cana P6 Pupil of Ariwa Primary school in Ariwa village Rhinocamp Refugee settlement says she sells food ration to buy firewood Photo By Robert Ariaka

በሪህኖ ካምፕ ሁለት ቡድኖች፣ አንድ ቡድን ደግሞ ከኢምቬፒ እና ሁለት ቡድኖች ከቢዲቢዲ ካምፕ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

ከኩስ የጡብ ከሰልን መስራት እንደሚቻል የተማሩት የተሻለ ልምድ ለመማር ኬንያ በመሄድ ናኩሩን በጎበኙበት ወቅት ነበር፡፡

ኦክስፋም ሴቶቹ የጡብ ከሰልን በብዛት ለማምረት እንዲችሉ የሰው ልጆች ደረቅ ቁሻሻን ወደ ጡብ ከሰልነት መቀየር የሚያስችል ዘመናዊ የምርት ሒደት ፋብሪካ መትከያ ቦታን በዮሮ ካምፕ አግኝቷል፡፡

የተዘጋጀውንና የታከመውን ኩስ ለማጓጓዝና በቀላሉ ለማምረት እንዲያስችላቸው መጓጓዣ ቀርቦላቸዋል፡፡

ሶስት ጎማዎች ያላት ተንቀሳቃሽ እቃ መጫኛ አንደኛው የፋብሪካው አካል የሚሆን ሲሆን፤ ሴቶቹ ምርታቸውን በመጠለያ ቦታዎቹ እየተዘዋወሩ በመሸጥ ገበያ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ የገበያ ስትራቴጂ፣ የማህበረሰብ ተሳታፊነት እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ለይቶ የማወቅ አስፈላጊነት አካባቢ ለመጠበቅ፣ አማራጭ ሀይል ምንጭን ለማቅረብ እና የግብርናውን ዘርፍ ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ዘመቻ ለማስፋፋት ይረዳል፡፡

እያንዳንዳቸው የቡድኑ አባላት ከሚያመርቱት ምርት ሽያጭ በሚያገኙት ገቢ በህይወታቸው ላይ ብዙ ለውጥ መፈጠሩን ማዌጂ ትናገራለች፡፡

የከሰል ጡብን መስራት በስፋት የሚካሔደውን የዛፍ ቆረጣ ድርጊትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት አካባቢን ይጠብቃል፡፡

ማዌጂ እንደምትናገረው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከዝናብ ሁኔታ መለወጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰት አለምአቀፍ ጉዳይ ሲሆን፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለአካባቢ ጥበቃ እና አማራጭ የሀይል ምንጭ ለማቅረብ ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡

‹‹አማራጭ የሀይል ምንጭ ሳይኖር ስለ አካባቢ ጥበቃና ዛፍ ቆረጣ መነጋገራችን ብንቀጥል ምንም ትርጉም የለውም›› ትላለች ማዌጂ፡፡

ኦክስፋም የአካባቢ ጥበቃ ህጎችን ያረጋገጠ ሲሆን፤ የውሃ ጉዳይን በተመለከተ ደግሞ በፕሮጀክቱ ላይ ታሳቢ አድርጓል፡፡ በሪህኖ መጠለያ 65 አባላት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በኢምቬፒ 25 እና በቢዲቢዲ በሁለት ቡድኖች የተከፈሉ 50 አባላት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

Copy of Story 4 viz 1

የባዮማስ ጥናት

በ2018 በአሩራ ዲስትሪክት በሪህኖ መጠለያ እና በኢምቬምፒ የስደተኞች መስፈሪያ ቦታዎች የደን ሽፋን ባዮማስ ጥናትና ካርታ ስራ በአለም አግሮፎረስተሪ ሴንተር አይ ሲ አር ኤ ኤፍ ተከናውኖ ነበር፡፡

በጥናቱ የተካተተው አካባቢ 138.615.96 ሄክታር ሲሆን፤ የ2018 ከመሬት በላይ የባዮማስ (ስብስብ ህይወት) በማርች ወር 2018 ከተሰበሰበ ዳታ የተገኘ ነው፡፡ 

በመላው አካባቢው የተገኘው የባዮማስ መጠን 1.678.748.46 ቶን ነው፡፡ 

ከመሬት በላይ የባዮ ማስ መጠን በተለይ ለዛፎች 1.397.046.39 ቶን፤ ለቁጥቋጦ ደግሞ 281.702.07 ቶን ነበር፡፡

የሪህኖ ካምፕ ከመሬት በላይ የባዮማስ መጠን 501.972.95፤ የኢምቬፒ 194.045.31 ቶን እና ለግጭት መከላከያ 5 ኪ.ሜ. 701.028.14 ቶን ነው፡፡

በ2010 እና በ2015 ባሉት ጊዜያት የባዮማስ መጠን በ96.680.10 ቶን ያህል የጨመረ ሲሆን፤ ለዚህም ምክንያቱ ቀደም ባሉት አስተዳዳሪዎች የደን መሬት የተዘጋጀ ስለነበር ይሆናል፡፡ በ205 እና በ2018 አመታት ውስጥ ደግሞ 522.255.76 ቶን ያህል ቀንሷል፡፡

በሰፈራ ቦታዎቹ ከፍተኛ የሆነ የደን ሽፋን መራቆት አለ፡፡ በ2010 እና 2015 ባሉት አመታት የደን መሬትን በማዘጋጀት በተሰራው የደን ባዮማስ ማሻሻያ 96.680.10 ቶን ጭማሪ ማሳየት ተችሏል፡፡

ይሁንና በ2015 እና በ2018 ባሉት ጊዜያት ለማገዶነት፣ ለምሰሶ ግንባታ፣ ለጡብ ስራ፣ ለከሰል እና እንጨት ልማት የሚውለው ፍጆታ በመጨመሩ የባዮማስ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡ 

ይህ ሁኔታ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ብቻ 522.255.76 ቶን እንዲጠፋ አድርጓል፡፡ ይህ ማለት አመታዊ የእንጨት ባዮማስ ጉዳት 174.085.25 ቶን ነው ማለት ነው፡፡ በሰፈራ ቦታዎች የግጭት መከላከያን ሳይጨምር የሚገኘው አጠቃላይ የባዮማስ መጠን 696.018.26 ቶን፣ ስደተኞች በሰፈራ ቦታዎች ብቻ ባዮማስ ላይ ጥገኛ ቢሆኑ ለአራት አመት ብቻ ነው የሚበቃቸው፡፡ በመሆኑም ይህ የሚጠቁመው በሰፈራዎቹ ቦታዎች በደን የተሸፈነ ባዮማስን ለማሻሻል ፈጣን እርምጃ እንደሚያስፈልግ ነው፡፡

መልሶ ማልማት ስራ

በምዕራብ ናይል ገጠር ኢኒሺዬቲቭ የማህበረሰብ ማብቃት የፕሮግራም ማናጀር የሆኑት ጃክሰን ኦሌማ እንደገለጹት በ2018 የጠፉትን ዛፎችንና የደን ሽፋንን በስደተኞቹ ሰፈራ ቦታዎች መልሶ ለማልማት በተደረገው ጥረት 317.000 ዛፎችን በ288.18 ሄክታር ቦታ ላይ መትከል ተችሏል፡፡

ይህ ተግባር በ2019 የተሻሻለ ሲሆን፤ 1.041.729 ዛፎችን በ890.75 ሄክታር መሬት ላይ መትከል ተችሏል፡፡

የዛፍ ተከላው የተካሔደው በስደተኞች ቦታ የተፈጥሮ ሽፋን በመጥፋቱ አካባቢንና የተፈጥሮ ሽፋንን መልሶ ለማልማት ታስቦ ነው፡፡

ይህ ዘገባ የተዘጋጀው በኢንፎናይል እና ሲቪከስ ጎልኪፐር ዩዝ አክሽን አክስሌተር የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts