ግብጽ ባህረሰላጤውን እንዴት እንደምትመግብ

ግብጽ ባህረሰላጤውን እንዴት እንደምትመግብ

በናዳ አረፋት እና ሳኬር ኤል ኑር

በአድማሱ ላይ በስፋት የሚታየው ለም መሬት በመቶዎች የሚቆጠሩ የግብርና ሰራተኞችን በሚተካው ዘመናዊ ማሽን እየተሰራ ነው፡፡ በአለም ላይ ትልቅ የውሀ ማጠራቀሚያ ከሆኑ ከአንደኛው ጣቢያ አንዱ በሌላው ተቀጣጥሎ በተያያዙ ቦይዎች በኩል በሚመጣ ውሀ መሬቱ እየተሸከረከረ ውሀን በሚረጭ መሳሪያ በመስኖ ይጠጣል፡፡ በርካታ መሐንዲሶች በቶሽካ ፕሮጀክት ከበርካታ የባህረሰላጤው የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች የአንዱ ይዞታ በሆነው መሬት ላይ የከብቶች መኖ የሆነውን የአልፋልፋ ምርትን የሚካሔድባቸውን አዳዲስ አካባቢዎች ለማልማት የሚሰሩ የማስፋፊያ ስራዎችን ይቆጣጠራሉ፡፡

ይህ ቦታ ከሁለት አስርት አመታት በፊት አሸዋማ በረሀ የነበረና አረንጓዴያማ ለመሆን የተሰራው ስራ ፈጣን ለውጥ የታየበት የግብጽ ምዕራባዊ በርሀ አካባቢ ነው፡፡

የዚህ ለውጥ መነሻ የመጣው የግብርና ልማትና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት የሚለው ሀሳብ የግብጽ ህዝብን ‹‹በተሻለ ለመደገፍ›› አንደኛው መንገድ ሆኖ ሲቀርብ ነበር፡፡ ይሁንና ከዚህ አላማ በሚጻረር መልኩ በነዳጅ ሀብት የበለጸጉ ሀገሮች ከድንበራቸው ውጪ መሬትን በመያዝና በማልማት የምግብ ዋስትና ደህንነታቸውን የማረጋገጥ እቅዳቸው አካል በማድረግ ብዙ የባህረሰላጤው ሀገሮች ኮርፖሬሽኖች አብዛኛውን መሬት ይዘውታል፡፡ 

n ymMfPbohHzpmwnIVo0dnYKgCJSK oXbCFy40VzH7ze hl Ih05IWMH0izLg9UQIqsbcOq83o73QddsrtWDyl wPtUE jtKvKpxUu1F7nXIQ2eoLqRippVAWihBO7Q 6aFbXQOiOK3nSAfTIA

አሁን ላይ ያለው ገጽታ ያኔ የባህረሰላጤው ሀገሮች ቀድሞውኑ እጥረት ያለበት የውሀ ሀብታቸውን የመጠበቅ አስፈላጊነትን የተረዱበት ቅጽበት ውጤት ነው፡፡ በጃንዋሪ 2009 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የግብርና አቅም ባላቸው ሀገሮች ኢንቨስት በማድረግ የምግብ ዋስትና ደህንነትን የማረጋገጥ ዝርዝርን በማካተት ለባህር ማዶ የግብርና ኢንቨስትመንት የንጉስ አብደላህ ቢን አብዱልአዚዝ ኢንሺዬቲቭን ይፋ አድርጓል፡፡ 

ይህ ኢኒሺዬቲቭ መንግስት የግንባታ እና ምርት ወጪዎችን እስከ 60 በመቶ በመሸፈን ለሳውዲ ኢንቨስተሮች የገንዘብ ድጋፍ አቅርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መንግስት በውጭ ሀገሮች ለሚሰሩ ኢንቨስተሮች ቢዝነስ ለማመቻቸት እና ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ወደ ኪንግደሙ ለማጓጓዝ ከሌሎች ሀገሮች መንግስታት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ለመደራደር ቁርጠኛ ነው፡፡

ይህ የረጅም ጊዜ የግብርና ስትራቴጂ በአንድ የሚኒስትር ውሳኔ በ2005 የስንዴ ምርትን በመገደብ ጀምሮ ቀስ በቀስ እያደገ የመጣ ነው፡፡ በሀገሪቱ ግዛት ለ30 አመት የተያዘው የስንዴ ምርት እና የእርሻ መርሀ ግብር የውሀ ሀብት መሟጠጡ በፈጠረው ስጋት የተነሳ በ2008 ሙሉ ለሙሉ እስኪያልቅ ድረስ በየጊዜው እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ባለፈው አመት የሳውዲ መንግስት በስንዴ ምርት ላይ የጣለውን ገደብ በተወሰኑ ሁኔታዎች ሲያነሳ፤ የእጽዋት ምግቦች የማልማት ስራ ከስንዴ የበለጠ ስድስት እጥፍ ውሀ የሚፈልግ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ አግዷል፡፡ 

ሳውዲ አረቢያ የውሀ እጦት ቀውስ የገጠማት ብቸኛዋ የባህረሰላጤው ሀገር አይደለችም፡፡ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስም የውሀ ሀብት ማጣት ችግር የገጠማት ስትሆን፤ 90 ከመቶ የሚሆነውን ምግብን ከውጭ ሀገሮች ወደ ማስመጣት ፊቷን ለማዞር ተገዳለች፡፡ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስም እንዲሁ በውጭ ሀገሮች የግብርና ኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲጠናከሩ ግፊት ማድረግ ጀምራለች፡፡

ሁለቱ ሀገሮች ተመሳሳይ ፈተናዎች ስለገጠማቸው ባለፈው አመት የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ነው ያሉትን ‹‹ዘ ስትራቴጂ ኦፍ ሪሶልቭ›› (የመፍትሔ አቅጣጫ) በጋራ ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህም የግብርና እና እንስሳት እርባታ ምርትን ሙሉ አቅም ለመገደብ እና በጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ለመስራት በማቀድ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ የጋራ ስትራቴጂን ማቋቋምን ጨምሮ ያካተተ ነው፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ ኢምሬትስ ከ60 በሚበልጡ ሀገሮች 4.25 ሚሊዮን ፌዳን መሬትን ስትቆጣጠር፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ በመላው አለም 4 ሚሊዮን ፌዳን ያህል መሬትን ይዛለች፡፡ (አንድ ፌዳን 4200 ስኩዌር ኪ.ሜትር ነው)

አንዳንዶች የበለጸጉት ሀገሮች የግብርና አቅም ባላቸው ሀገሮች መሬትን በግዢ ወይም በሊዝ መልኩ ለመውሰድ የሚያደርጉትን ጥድፊያ ግብርናን በሚሰራበት ሀገር ውሀን ጨምሮ የማይታደሱ ሀብቶችን በመጠቀም ኢንቨስት የሚያደርጉ ሀገሮችን የምግብ ዋስትና ደህንነትን ያሳካ ኒዮኮሎኒያሊዝም እንደሆነ ይገልጹታል፡፡ 

የባህረ ሰላጤው ኢንቨስተሮች በናይል ሸለቆ እና ዴልታ ከአስቸጋሪው የሰብል አመራረትና ከባህላዊ ግብርና ዘዴ ይልቅ ሰብሎችን ወደ ውጭ ለመላክ ለግዙፍ ኢንቨስትመንትና ዘመናዊ ግብርና ቅድሚያ የሚሰጠውን የካፒታሊስት ግብርና ምርትን በሞዴልነት በተቀበለችው በግብጽ የሚፈልጉትን መፍትሔ አግኝተዋል፡፡

‹‹ከእኔ ጋር መጥታችሁ

በግብጽ ያለውን ተመልከቱ

ሀገራችን ምን መሆን እንደቻለች

ከሁለት ወይም ሶስት አመት በፊት ከነበራት ምስል ይለያል

በሁለት አገዛዞች መካከል ያለውን አላነጻጽርም ወይም አለያይም፣ ወይ ደግሞ በደስታ  

አልጮህም፤

ግብጽን፣ ሀገሬን ማየት

የልጆቼ መብት ነው፡፡

በሚሊኒየሙ እንደአዲስ ታንጸባርቃለች››

እንዲህ የሚለው ብሔራዊ መዝሙር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከአስዋን በደቡብ 225 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን የግብጽን ምዕራባዊ በርሀ በ1997 በጎበኙበት ወቅት በግብጽ በሁሉም የመንግስት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተላልፏል፡፡ በወቅቱ ሙባረክ የቶሽካ ፕሮጀክት መጀመርን ይፋ ሲያደርጉ ለመሐንዲሶቹ ሰላምታ ለመስጠት እጃቸውን ሲያነሱ የተነሱት ፎቶ ምስል በሙባረክ ዘመን አስደናቂ ፎቶግራፍ ለመሆን ችሏል፡፡

የፕሮጀክቱ እቅድ ተቀርጾ የነበረው ግንባታውን በ1997 መጀመርና በ2017 ማጠናቀቅ ነው፡፡ ዋነኛ አላማውም በምዕራባዊ በርሀ አዲስ የዴልታ ደቡብን ለመክፈል ሲሆን፤ እስከ 1 ሚሊዮን ፌዳን የእርሻ መሬትን ለመጨመር፣ አዲስ የኢንዱስትሪ እና የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር እና በ10 አመት ውስጥ ከ4-6 ሚሊዮን ለሚሆኑ ግብጻውያን በየአመቱ 45.000 አዲስ የስራ እድልን ለመፍጠር ነው፡፡

ነገር ግን አመታት ሲነጉዱ፤ ግብጽ ከቶሽካ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንዳልሆነች ነው መረዳት የተቻለው፡፡ በናይል ሽለቆ የህዝብ ብዛት መጨመር እና የምግብ ደህንነት ቀውስ መፍትሔ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ ይሁንና ፕሮጀክቱ ለተወሰኑ የውጭ ሀገር ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ጥሩ የሚባል ስኬትን አጎናጽፏል፡፡

በፕሮጀክቱ መጀመሪያ በ1997 አካባቢ ኢመሬትስ 100 ሚሊዮን ዶላር በአቡዳቢ ፈንድ ፎር ዴቨሎፕመንት በኩል ጥሩ ድጋፍ ማግኘት ችላለች፡፡ ገንዘቡም የፕሮጀክቱ ዋና የውሀ ቦይ ለመገንባትና መስመሩን ለመዘርጋት ውሏል፡፡ ወደ 51 ኪሎ ሜትር ያህል በማራዘምም በአቡዳቢው መሪ ስም ‹‹ሼክ ዛይድ ቦይ›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ 

ለፕሮጀክቱም የሚመለከታቸው ሀላፊዎች ግብጽን ከናይል ወንዝ ከምታገኘው ኮታ አንድ አስረኛውን ያህል (ከ55.5 ቢሊዮን ኩቢክ ጫማ ውስጥ 5.5 ቢሊዮን) ነው የመደቡት፡፡ ከናስር ሀይቅ ጋር የተያያዘውና በወራጅ ውሀ የተሞላው ባለ 250 ሜጋ ዋት የውሃ ማውጫ ጣቢያ ከቶሽካ ሸለቆ ውሀ እንዲያወጣና ወደ ሼክ ዛይድ ቦይ እንዲያጓጉዝ ተገንብቷል፡፡ 

በ2003 ወደዚህ ካናል ውሀ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባ ሲሆን፤ ብዛት ያላቸው የባህረሰላጤው ሀገር ኢንቨስተሮችንም ወደ ቶሽካ አካባቢ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወደ 450.000 ፌዳን ስፋት ሲኖረው 100.000 ያህሉ በሳውዲ አረቢያ መቀመጫውን በአደረገው አልራጂ ኢንተርናሽናል ፎር ኢንቨስትመንት ኩባንያ የተያዘ ሲሆን፤ ሌላው 100.000 የሚሆነው ደግሞ በኢምሬትስ በሚገኘው አል ዳህራ ፎር አግሪካልቸራል ዴቨለፕመንት ኩባንያ የተያዘ ነው፡፡

ግብጽም በበኩሏ ከፕሮጀክቱ የራሷ ድርሻ አላት፡፡ 25.000 ፌዳን በአሁኑ ወቅት ፤ በ2017 መሬት ከአል ዋሊድ ታላል ኪንግደም ኦፍ አግሪካቸራል ካምፓኒን በገዛው በግብጽ ናሽናል ሰርቪስ ፕሮዳክትስ ኦርጋናይዜሽን ስር ነው፡፡ ሌላ 62.000 ፌዳን ደግሞ በሳውዝ ቫሊ ፎር ዴቨሎፕመንት ስር ሲሆን፤ 92.000 ፌዳን መሬት በቅርቡ ለግብጽ ካንትሪ ሳይድ ዴቨለፕመንት ኩባንያ ተሰጥቷል፡፡ሁለቱም ኩባንያዎች የመንግስት የግብርና መልሶ ልማት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ አስር ሺህ ፌዳን መሬት ደግሞ አዲስ የቶሽካ ከተማን ለመፍጠር ተብሎ ለቤቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተሰጥቷል፡፡ 16.000 ፌዳን ደግሞ እስከ አሁን ለማንም ሳይሰጥ ይገኛል፡፡

የባህረሰላጤው ኩባንያዎች የሆኑት አል ራጂህ እና አል ዳህራ ከአጠቃላዩ በፕሮጀክቱ ከለማውን መሬት 49.4 በመቶ የሚሆነውን ይዘዋል፡፡

lLYR0T5PZhPylD7arZTsA1PURpY3o5KudG9rUIiYRu TXMMo5KFSf1ZKELnA5bDi5cMnPQY27V2

የባህረሰላጤው ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች በቶሽካ መሬትን የሚያገኙት በመሬት ስምምነት አማካኝነት ነው፡፡ ይኸውም ኩባንያው የመሬት ባለቤት የሚሆው በተለያዩ ምዕራፎች ነው፡፡ በእያንዳንዱ ምዕራፍ የሚጠየቀው የመሬት ፌዳን ቁጥር ብዛት እያንዳንዱ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ነው፡፡ የመሬት ባለቤትነት ወደ ኩባንያው የሚተላለፈው ኩባንያው የተመደበውን መሬት በሙሉ እስኪይዝ ድረስ ነው፡፡

በ2014 በሴንትራል ኦዲቲንግ ባለስልጣን የታተመው ሪፖርት እንደሚያትተው ከሆነ መሬቱ በፌዳን 3 የአሜሪካን ዶላር ተሸጧል፡፡ በዚያን ወቅት ግን በገበያ ላይ የነበረው ዋጋ በአንድ ፌዳን 635 ዶላር ነበር፡፡ የግብጽ መንግስት የቦይ ሲስተሙን ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ የሚሸፍን ሲሆን፤ ኢንቨስተሮቹ ደግሞ በያዙት መሬት ላይ የሚካሔደውን የግብርና መልሶ ልማት እና የመስኖ ቦይ፣ የፍሳሽ ሲስተም እና ውሀ ማውጫ ጣቢያዎች ቅርንጫፎችን አጠቃላይ ግንባታ ወጪዎችን ሸፍነዋል፡፡

*****

ውስብስብ የኢንቨስትመንት ትስስር

የባህረሰላጤው ሀገሮች በግብጽ ያላቸው የግብርና ኢንቨስትመንት ትስስር የተወሳሰበ ነው፡፡ የግብጽ እና የባህረሰላጤው ኢንቨስተሮች የንግድ ፍላጎት ግብጽ እና የባህረሰላጤው ሀገሮች በመካከላቸው ካለው የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት ጋር የተሳሰረ ነውና፡፡ 

አል ራጅሂ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መቀመጫውን በሳውዲ ያደረገ በአል ራጅሂ ቤተሰብ ስር የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡ በንጉስ አብደላ የውጭ ኢንቨስትመንት ኢኒሺዬቲቭ ውስጥ ባለድርሻ በሆኑት በሱሌማን አል ራጅሂ የተቋቋመ ነው፡፡ ወደ ግብጽ ገበያ የገባው በ2009 ነበር፡፡ 

በአሁኑ ወቅት አል ራጅሂ ታቡክ አግካቸራል ዴቨሎፕመንት ኩባንያን የያዘ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሳውዲ አረቢያው የጃናት አግሪካቸራል ኢንቨስትመንት ኩባንያ አንደኛው አጋር ነው፡፡ ሌሎች በሳውዲ መቀመጫቸውን ያደረጉ አል ካሪፍ ፎር ፒቮት ፎር ኢሪጌሽን ሲስተምስ እና አል ማራጅን ጨምሮ ስድስት ሌሎች ኩባንያዎች በጃናት ስር በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ እየሰሩ ነው፡፡

የሳውዲው ጃናት አግሪካልቸራል ኢንቨስትመንት ኩባንያ በግብጹ ራክሀ ፎር አግሪካቸራል ኩባንያ ውስጥ 78 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ ይህ ኩባንያ የመስኖ ሲስተም ኩባንያ የሆነውን የግብጽ መንግስት ተቋም የሆነውን REGWA ባለቤት ሲሆን፤ በምዝበራ እና በመሬት ወረራ በርካታ ክሶች ተመስርተውበታል፡፡

ራክሀ ፎር አግሪካልቸራል ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በምግብ ምርት ላይ ከሚሰራው ከሳውዲው ኩባንያ ዋፍራሀ ፎር ኢንደስትሪ ኤንድ ዴቨሎፕመንት ጋር ግንኙነት አለው፡፡

አል ዳህራ በግብርና ዘርፍ ካተኮረው እና ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የምግብ ደህንነት ዋስትና ባለስልጣን የእንስሳት ምግብን የሚያቀርብ የኢመሬትስ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባልና የነገስታቱ የአቡዳቢ ምዕራባዊ ክልል ተወካይ በሆኑት በሀሚድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ባለቤትነት የሚተዳደር ሲሆን፤ የመንግስት እቅድ በሆነው የኢመሬትስ የምግብ ደህንነት ፕሮግራም በከፍተኛ ሁኔታ ተሳታፊ ነው፡፡

ኩባንያው በግብጽ ስራውን የጀመረው በ2006 ሲሆን፤ በ2007 አል ዳህራ ግብጽን አቋቋመ፡፡ ናቪጌተር ፎር አግሪካቸር ኢንቨስትመንት በተባለው ድርጅቱ በኩልም ከግብጽ እና ኢመሬትስ መንግስታት ጋር በትብብር ይሰራል፡፡

አል ራጅሂምም ሆነ አል ዳህራ ከመንግስታቸው ጋር ጠንካራ ትስስር ያላቸው ሲሆን፤ በሳውዲ አረቢያና በኢመሬትስ በተጀመረው እንደ ‹‹ስትራቴጂ ፎረ ሪሶልቭ›› አይነት የውጭ ሀገር የግብርና ኢንቨስትመንት ኢኒሺየቲቮች ላይ በጥልቀት ተሳታፊ ናቸው፡፡

የባህረሰላጤ የምግብ ደህንነት ኢኒሺዬቲቭ ከተጀመረ በኋላ የኢምሬቱ ኩባንያ አል ዳህራ በግብጽ ቶሽካ 116.000 ፌዳን ፣ በኢስት ኦዌናት፣ በሳለሄያ እና ኑባሪያ ክልሎችን ጨምሮ በመላው አለም 400.000 ፌዳን መሬትን ተቆጣጥሯል፡፡ የሳውዲው አል ራጅሂ ደግሞ በቶሽካ ካለው 100.000 ፌዳን በተጨማሪ 120.000 ፌዳን በሞሪታንያ ሲኖረው፤ በሱዳን 450.000 ፌዳን ለመውሰድ አቅዷል፡፡

UXJ7VW7IXBkuOM6oL64SMdP DJH3P9Ivv9OENPwwIkgM09HXNInycsn7BxGktG56UJLIxgB1DwmjQllZkXJjHuEMB4Gt fpnUcf2N8Un4gr4HF USOPj7mMrQJmi2J3 reR81pt77zLuvkYg

ጥቂት የማይባሉ የህግ ባለሞያዎች ከላይ ከተጠቀሱት ኩባንያዎች በተወሰኑት ላይ ክስ መስርተዋል፡፡ አንዳንዶቹ የኮንትራት ስምምነቱ አንቀጾች የግብጽን ህገ መንግስት የጣሱ መሆናቸውንና የሀገሪቱን ሀብት የሚያሟጥጡ መሆናቸውን ክሳቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡ ጉዳዩን ከያዙ ባለሞያዎች አንደኛው እንደሚገልጹት ከፍተኛ ኮርፖሬሽኖች በብዙ ኩባንያዎች ሙሉ ለሙሉ ገበያውን ለመቆጣጠር  በተወሳሰበ ኢንቨስትመንት ፍላጎት ስር መንቀሳቀስን ስትራቴጂ አድርገውታል፡፡ 

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የህግ ባለሞያ እንደገለጹት ይህ ስትራቴጂ አንድ ኢንቨስተር በገበያ ላይ ምን ያህል ጥቅም እንዳገኘ ለመሸፈን የሚረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም ድርሻዎቹ ለብዙ ኩባንያዎች የሚከፋፈሉ ሲሆን፤ ይህም ታክስን ለመሸሸግ የሚያመች ነው፡፡

ይህ ሁኔታ የሁሉም ባላድርሻ አካላት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ለምሳሌ የእንስሳት መኖ የሚሆን አልፋልፋን የሚያመርተው የሳውዲው ኩባንያ አል ራጅሂ ኩባንያ የወተት ምርት ኩባንያ የሆነው የአልማሪያ አካል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመስኖ ውሀ የማጠጣት ዘዴ ላይ የሚሰራው የአልክሆራዬፍ አካልም ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ኩባንያዎች ገበያቸውን ለማስፋት እና የአቅርቦታቸውን ፍላጎት ለማሳካት በሚረዳቸው በሳውዲው የግብርና ኢንቨስትመንት ጃኔት ስብስብ ስር ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡ እንዲሁም የጥራጥሬና ፓስታ ላይ ከሚሰራው ከሳውዲው ዋፍራህ፣ የእንስሳት መኖ ምርት ላይ ከሚሰራው የግብጹ ማሪና ከመሳሰሉ ኩባንያዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆኑ ስምነነቶችን ያስተባብራል፡፡ ይህ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ከምርት እቃዎች ጀምሮ እስከ ምርቱ እና የኢንዱስትሪ ሒደቱ ድረስ፣ በመጨረሻም ገበያ ላይ በምግብ ሸቀጦች ላይ ብቸኛ አቅራቢ ለመሆን የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ያለመ ነው፡፡

***

አጠራጠጣሪ ውሎች

በግብጽ መንግስት እና በባህረሰላጤው ኢንቨስተሮች መካከል የተፈጸሙ ውሎች በተለይም በቶሽካ የተፈጸሙ ቀደም ሲል በሚዲያ የታተሙ ሪፖርቶች ላይ በሰፈረው መረጃ መሰረትም ሆነ በማዳ ማስር የሚገኘው ይፋዊ ሰነዶች ቅጂዎች ላይ እንደሚታየው ጥሰት የተሞላባቸው ናቸው፡፡

በግብጽ መንግስት እና በሳውዲው ቢሊየነር ኢንቨስተር ታል ዋሊድ ቢን ታላል መካከል የተደረገው ስምምነት የተጀመረው በ1998 ነበር፡፡ በወቅቱ ኪንግደሙ በቶሽካ መሬት የገዛ የመጀመሪያው የባህረሰላጤው ኩባንያ ነበር፡፡ በፌዳን 3 ዶላር ሒሳብ 100.000 ፌዳን መሬትን ይዟል፡፡ ከዚህ ውስጥም 20 በመቶ የሚሆነው ብቻ ስምምነቱ በተፈረበት ጊዜ የተከፈለው፡፡ በስምምነቱ ላይም ቀሪው ክፍያ የሚከፈልበትን መንገድ ሆነ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች አልተካተቱም፡፡ ቀሪው ገንዘብ ይከፈል አይከፈል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ኮንትራቱ ኢንቨስተሩ ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ማረጋገጫ ሳይፈልግ የፈለገውን አይነት ሰብል ማምረት የሚስያችለው ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ያለ መንግስት ፈቃድ ከውጭ ሀገር ዘሮችን የማስገባት መብትን የሰጠ ነው፡፡ የስምምነቱ አንቀጾች ተጨማሪ ኢንቨስተሩን አጠቃላይ ታክስ ነጻ የሚያርግ ነው፡፡

በ2011 አብዮት ከተካሔደ በኋላ በተደረገ ጥልቅ ምርመራ የተወሰኑ የስምምነቱ አንቀጾች ተሻሽለዋል፡፡ የቢን ታላል ኩባንያም የተወሰነውን የመሬት ክፍል ለመመለስ ተስማምቶ ነበር፡፡ መሬቱ አሁንም ድረስ ያልተመለሰ ሲሆን፤ አጠቃላይ 75.000 ፌዳን ይዞታ አለው፡፡ በ2017 የግብጽ ወታደራዊ ሀይል ቀሪውን 25.000 ፌዳን 1.25 ሚሊዮን በሆነ በግብጽ ገንዘብ ከቢን ታላል ገዝቷል፡፡

በተመሳሳይ በ2011 የግብጹ ሴንተር ፎር ሶሻል ኤንድ ኢኮኖሚክ ራይትስ የተባለ ተቋም የአል ዳህራ የፈጸመው ውል እንዲፈርስ በመጠየቅ ክስ መስርቷል፡፡ በክሱ ላይ እንደተመለከተው በቶሽካ ለተጠቀሰው ኩባንያ የተፈጸመው የ100.000 ፌዳን መሬት ሽያጭ የህዝብ ገንዘብ እንዲባክን ያደረገ ነው፡፡ የመንግስት መሬት ሲሸጥም ከተገመተው በታች በሆነ ዋጋ ነው፡፡ መሬቱ በወቅቱ በፌዳን በአማካይ 637 ዶላር ቢሆንም የተሸጠው ግን በ3 ዶላር ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በማዕከሉ ይፋ የሆነ ሪፖርት እንደሚያለክተውም የግብጽ መንግስት ካውንስል ባወጣው መግለጫ ላይ ኮንትራቱ እንዲሰረዝ አሳስቧል፡፡ ይሁንና የአቃቤ ህግ ቢሮ ተጨማሪ ምርመራ እንዲካሔድ ፈጽሞ አላደረገም፤ ጉዳዩም ያለምንም አይነት ውሳኔ ተዘግቷል፡፡

እነዚህ የህግ ጉዳዮች ቢኖሩም በቅርቡ የግብጽ መንግስት በመንግስት እና ኢንቨስተሮች መካከል በሚደረግ ስምምነት ላይ በኮንትራቱ ላይ ድርሻ ካላቸው አካላት በስተቀር ሶስተኛ ወገን እንዳይገባ የሚከለክል ህግ አውጥቷል፡፡ ይህ ህግ የጸደቀው የቀድሞው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድሊይ መንሱር ህጉ የኢንቨስትመንት ህጉ ላይ የተሟጋቾች መብቶችን በሚነኩት ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በ2014 ሲያደርጉ ነው፡፡ 

የህግ ጥሰቶቹ በውል አዘገጃጀቱ ላይ ባሻገር የኮንትራቱ ግዴታን ያለማሟላት እና መሬትን መልሶ ማልማት ትክክለኛ ሒደቱን አለመተግበርም የሚታዩ ናቸው፡፡ 

ለምሳሌ አል ራጅሂ በአምስት ምዕራፍ ለማልማት ተስማምቶ ከነበረው 100.000 ፌዳን ውስጥ 25.000 ያህሉን ተረክቧል፡፡ በ2010 መጀመሪያ ላይ ኩባንያው የመጀመሪያውን 25.000 ፌዳን የማልማት ሒደቱን ማጠናቀቁን በመግለጽ ምዘና እንዲካሔድ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ባለፈው አመት የግብርና ልማት ፕሮጀክቶች ዋና ባለስልጣን ኩባንያው ሁለተኛውን ምዕራፍ የግብርና ልማት ስራውን እንዲጀምር ለኩባንያው 17.000 ፌዳን መሬት ማስረከቡን አረጋግጧል፡፡ ይሁንና በሳተላይት የተወሰደ ምስል የሚያስረዳው ይህንን ሀቅ አይደለም፡፡ በ2013 አጠቃላይ የለማው አካባቢ ስፋት ወደ 6.000 ፌዳን የሚጠጋ ሲሆን፤ በ2019 ደግሞ 10.402 ፌዳን ሆኗል፡፡

ሌላ በአል ዳህራ የተፈጸመውን ጥሰት ያጋለጠው በአቡ ሲምቤል በሴንተር ፎር ወተር ሪሰርች ውስጥ የሚገኝ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ይኸውም ኩባንያው ከመሬቱ አምስት በመቶ የሚሆነውን ብቻ አልፋልፋ እንደሚያለማ የተገለጸውን ስምምነት በመጣስ አጠቃላዩን 18.351 ፌዳን መሬት በአልፋልፋ ምርት እንዳለማ የሳተላይት ምስል አሳይቷል፡፡

0sDauRJ5DnYJKItVPEbGA4l2lDqgX5ofq3 w0R56uE 5fAw0 vjHjcmZLGaOQgzUWCHte5zqiuHV9Ob0QKzp1OCFzLG2YRDLI4aMuMdqRmEmVKAIERi9AhGKU2RtoUvRhKkUvxdyt fgOzj Mg

የግብርና ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሀምዲ አብደል ዳዬም ለማዳ ምስር እንዳረጋገጡት ብዙ ስምምነቶች የውሀ ሀብትን ለመጠበቅ ኢንቨስተሮች 5 በመቶ ያህል ብቻ የአልፋፋ ምርት እንዲያለሙ የሚገድቡ ነው፡፡ የቀድሞ የግብርና እና መስኖ ጉዳይ የፓርላማ ኮሚቴ ምክትል የሆኑት ራኤፍ ቴምራዝ ደግሞ በቶሽካ እና ኒው ቫሊ ግዛት ከለማው መሬት 25 በመቶ የሚሆነው በአልፋልፋ ምርት የተሸፈነ ነው፡፡ ብዛት ያለው የአልፋልፋ ምርት ወደ አረብ ሀገሮች በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኢመሬትስ እንደሚላክም ቴምራዝ ገልጸዋል፡፡

***

ብክነት በሁሉም ደረጃ 

በካይሮ ዩኒቨርስቲ የግብርና ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር የሆት ጋማል ሲያም የቶሽካ ፕሮጀክት ክስረት በህዝብ ዘንድ መነጋገሪያ ሲሆን፤ የመስኖ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የቶሽካ ፕሮጀክ ከተጀመረ ከሁለት አመት በኋላ ዩኒቨርስቲው የትግበራ ጥናት እንዲያደርግ መጠየቁን ያስታውሳሉ፡፡

እንደ አትክልትና ቅጠላቅጠል ያሉ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ምግቦች መልሶ በሚለሙ መሬቶች ላይ ለኢኮኖሚ እድገት አማራጭ መሆናቸውን ሲያም ያስያረዳሉ፡፡ ይኸውም ምግቦቹ ተጨማሪ ዋጋንና ስራን በሚፈጥር እና የሀገር ገቢን በሚያሳድግ የምርት ሒደት የሚያልፉ በመሆናቸው ነው፡፡ 

እንዲህ አይነቱ የውጭ ኢንቨስትመንት ለመንግስት መልሰው የሚሰጡት አንዳችም ነገር እንደሌላቸው ነው የሚገልጹት፡፡ ምክንያቱም ኢንቨስተሮች ውሀን በርካሽ እንዲገዙ የሚፈቅድ፣ መሬትን በአነስተኛ ወጪ እንዲይዙ እና አብዛኛውን ምርት ወደ ውጭ ሀገር እንዲልኩ የሚፈቅድ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የእነዚህ ድርጅች ካፒታል የሚገኘው በግብጽ አይደለም፡፡ ስለዚህም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እውነተኛ የሆነ አንዳችም ጥቅም የለም፡፡

እንደ ሲያም ከሆነ መንግስት ከኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ጋር ከአጭር ጊዜ የገንዘብ ጥቅም ይልቅ የረጅም ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለሚሰጡ ስምምነቶች ላይ ማተኮር አለበት፡፡ እንደዚህ አይነት ስምምነቶች የባረሰላጤው ኮርፖሬሽኖችን በግብጽ ምድር ላይ የራሳቸውን ዞን ለማቋቋም እና ባለመብት የሚያደርጋቸው ነውና፡፡ አንድ ፌዳን የበረሀ መሬት በአሁኑ ወቅት እስከ 2.311 ዶላር የሚያወጣ ሆኖ ሳለ፤ መንግስት ለውጭ ኢንቨስተሮች በፌዳን 3 ዶላር ለመሸጥ የፈቀደበትን ውሳኔ ላይ ጥያቄ አላቸው፡፡ ‹‹ይህ ዋጋ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ቢል አሳማኝ ቢሆን እንኳ ይህ ጥቅም ለምን ለውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች ቀረበ?›› ሲሉም ሲያም ይጠይቃሉ፡፡ 

እሳቸው በአዘጋጁት የኢኮኖሚ ትግበራ ጥናት እንደሚያስረዱት በሁለቱም ኩባንያዎች የለማው መሬት ወደ 29.000 ፌዳን ነው፡፡ በአመት የሚጠቀሙት አማካይ የውሀ መጠን 210 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ሲሆን፤ ለመስኖ ሚኒስቴር የሚከፍሉት አመታዊ ሂሳብ ወደ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ያን ያህል የውሀ መጠን በገበያ ዋጋ ብንተምነው በኩቢክ ሜትር 0.12 ዶላር ሂሳብ ኢንቨስተሩ 24.3 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ውሀ የገዛው በ1.2 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡ 

ይህ ‹‹የውሀ ሀብት ወረራ›› በአሁኑ ወቅት በለማው መሬት በ29.000 ፌዳን ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ሁለቱ ኩባንያዎች 200.000 ፌዳን መሬት በሚይዙበት ጊዜም የሚቀጥል ነው፡፡ የሲያም ትንታኔ በቶሽካ ከሚሰሩ ከሁለቱ ኩባያዎች በአንዱ በሚሰራ ሰው የተረጋገጠ ነው፡፡ አንደኛው የኢምሬቱ የአልፋልፋ ምርት አስመጪ ‹‹የምገዛው ውሀን እንጂ አልፋልፋን አይደለም›› ማለቱን ነው ውስጠ አዋቂው የገለጸው፡፡

ወደ 210 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር የሚሆን ተመሳሳይ የውሀ መጠን 84.000 ፌዳን ስንዴን ለማልማት በቂ መሆኑን ያስረዱት ሲያም፤ ይህም የግብጽን የሰብል ምርትወደ 62.000 ቶን የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡ ግብጽ በአመት16.000 ቶን ስንዴ የምትጠቀም ሲሆን፤ ከአለም ከፍተኛ የስንዴ አስመጪ ሀገር ናት፡፡ ባለፈው አመት ወደ 6 ሚሊዮን ቶን ስንዴን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብታለች፡፡

የግብርና ባለይዞታነትን በተመለከተ በወጣ ይፋዊ መግለጫ ኢንቨስተሮች የውሀ ሀብትንና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ሰብልን በማምረት በኩል የፕሮጀክታቸውን የረጅም ጊዜ ቆይታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡ የግብጽን ስንመለከት መንግስት ብዙ ግብጻውያንን የሚታደገውን ስንዴን እንዲያለሙ ኩባንያዎቹን ተጭኗል፡፡ ይሁንና መንግስት ኩባንያዎች የስንዴ ምርታቸው ላይ ቁጥጥር ማድረግ አልቻለም፡፡ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ በቱሽካ በአንደኛው የባህረሰላጤው ኩባንያዎች ውስጥ የሚሰራ ምንጭ እንደገለጸው ከሆነ በኩባንያው የሚመረተው አጠቃላይ የስንዴ መጠን 15.000 ቶን ነው፡፡ ይህም ማለት በስንዴ የለማው አጠቃላይ የመሬት ስፋት 6.000 ብቻ ነው፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ በ2007 ሳውዲ አረቢያ የአልፋልፋ ምርትን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የውሀ ፍጆታዋን ለመቀነስና ለመቆጣጠር ወሰነች፡፡ የአልፋልፋ ምርት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሀ የሚፈጅ በመሆኑ (በእያንዳንዱ ፌዳን ላይ አልፋልፋ ለማልማት ወደ 8.000 ኩቢክ ሜትር ውሀ ያስፈልጋል) የሳውዲ የሚንስትሮች ካውንስል የወተት ልማት ስራዎች ወደ ውጭ ከሚልኩት ምርቶች እኩል የእንስሳት ምግብን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ የሚያስገድድ ህግ በ2011 አጸደቀ፡፡ በ2015 ካውንስሉ የእንስሳት ምግብ ልማትን ሙሉ ለሙሉ ከለከለ፡፡ ይህም ማለት ሳውዲ የወተት ምርት ስራዎች እንደ ግብጽ ባሉ በውጭ ሀገሮች በሚካሔዱ ኢንቨስትመንቶች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የእንስሳት ምግቦች ላይ ጥገኛ አደረጋቸው ማለት ነው፡፡

የግብጽ የግብርና ሚኒስትር ስትራቴጂ ለ2030 ያቀደው ብዙ ውሀና ለመቆጠብ በናይል ዴልታ በመስኖ ውሀ የማጠጣት ዘዴ እና በግብጽ ገበሬዎች ዘንድ አትራፊ እንደሆነ የሚቆጠረውን እንደ ሩዝ ያሉ የተወሰኑ ሰብሎችን ልማት መቀነስ ነው፡፡ በዚህ ዘዴም መንግስት በናይል ሸለቆና ዴልታ ከሚገኙ መሬቶች እከ 14.5 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ውሀን መቆጠብ ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥም የተወሰነው ውሀ በመስኖ በማጠጣትና በማልማት በመንግስት ለተያዙ ለተለያዩ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች የሚውል ይሆናል፡፡ ይህም ማለት መንግስት ከአካባቢው ገበሬዎች ውሀን ወስዶ መልሶ ለውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች ይሰጣል፡፡ እነሱም የሀገሪቱን ሀብት አሟጠው በመውሰድ አልፋልፋን ማምረትና ወደ ውጭም ምርቶችን መላክ ይችላሉ፡፡

L7CbwHeQOan25HR5ghcBeH V8MKBx

ይህ በውጭ ኢንቨስተሮች የሚፈጸመው የሀገሪቱን ሀብት ምዝበራ ወደ ሀይልም የሚመያራ ነው፡፡ የውጭ ሀገሮቹ ዘመናዊ የማምረት ስራ ውሀን ወደ አካባቢው ለማቅረብና በመስኖ መስመሮቹ ወደ እርሻዎች ለማከፋፈል ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለው ሀይልን የሚፈልግ ነው፡፡ በ አል ራጅሂ ኩባንያ የሚሰራ አንድ የመረጃ ምንጭ እንደገለጸው ኩባንያው በወር 1.5 ሚሊዮን ኪሎዋት ይጠቀማል፤ አል ዳህራ ደግሞ ወደ 2 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሀይል በወር ይጠቀማል፡፡ ይህ ማለት የሁለቱም ኩባንያዎች የሀይል ፍጆታ አንዱ የካይሮ ሜትሮ (የከተማ ባቡር) የሀይል መስመር ከሚፈልገው 28 በመቶ ያህል ነው፤ ይህም በወር 12.5 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ማለት ነው፡፡

ምንም እንኳ በሁለቱ የባህረሰላጤው ኩባንያዎች ሰፊ መሬት የተያዘ ቢሆንም፤ በአንደኛው ኩባንያ የሚገኝ ሰራተኛ በተገኘ መረጃ እያንዳንዳቸው ያላቸው የሰው ሀይል ቁጥር ከ200 ሰራተኛና ተቀጣሪዎች አይበልጥም፡፡ ይህ ቁጥር በኒው ቫሊ እና ዴልታ ግዛቶች ከሚለማ ተመሳሳይ የመሬት ስፋት መጠን ከሚፈልገው የሰው ሀይል ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በየአመቱ 450.000 የስራ እድል የማመንጨት እቅድና በእነዚያ አካባቢዎች ከ4 እስከ 6 ሚሊዮን ዜጎች የከተማ ሰፈራን በማሳደግ ከ4 እስከ 6 ሚሊዮን የሚደርስ ዜጎችን ለማኖር ካለመው ከቶሽካ አንደኛው ግብ ጋር የሚቃረን ነው፡፡

ግብጽ በባህረሰላጤው ኮርፖሬሽኖች የግብርና መሬት ባለይዞታነት ትኩረት የተደረገባት ብቸኛዋ ሀገር አይደለችም፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ግን ይህን መሰል ኢንቨስትመንትን መግታት ጀምረዋል፡፡ ሱዳን የእርሻ መሬትን ለእስሳት መኖነት ልማት መሬት በሊዝ መስጠት የጀመረች አንደኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በቅርቡ አንዳንድ የሱዳን ፓርላማ አባላት የሀገሪቱ የከርሰ ምድር ውሀ ሀብት እያለቀ መሆኑ ያደረባቸውን ስጋት በመግለጻቸው ሀገሪቱ ተጨማሪ የግብርና ኢንቨስትመንት ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኗን አስታውቃለች፡፡ በ2013 መሬት ለባህረሰላጤው ኢንቨስተሮች መከፋፈሉን በመቃወም በርካታ ተቃውሞዎች ተነስተው ነበር፡፡

በደሰርት ሪሰርች ካውንስል የአግሪካልቸራል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ሸሪፍ ፋያድ በግብጽ በረሀን መልሶ የማልማት ስራ ያለበትን ችግር ሲያረዱ የአካባቢውን ሀብት አቅም ለመገደብ የሚያስችል ግልጽ የሆነ ስትራቴጂ በመንግስት በኩል አለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡ ያለውን ሀብት በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም በበረሀ፣ በናይል ሸለቆ እና ዴልታ አካባቢ ምን ሊለማ እንደሚችል ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ ለአሮጌው ናይል ሸለቆ የተጠኑ ሰብሎችን ማምረት ሰብሎች እምብርት መሆኑ ስሜት የሚሰጥ ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሰብሎች (ለምሳሌ ጥጥ) የሰው ሀይልን የሚፈልጉ ሲሆኑ፤ ሌሎች ደግሞ (እንደ ስንዴ ያሉት) በጣም ብዙ ለም መሬትን፤ እንደ ሩዝ ያሉት ደግሞ በርካታ ውሀን የሚፈልጉ ናቸው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የእነዚህ እህሎች መዳረሻ ገበያ ከለሙበት ወይም የምርት ሒደታቸው ከተካሔደበት አካባቢ በጣም የቀረቡ ናቸው፡፡ ለበረሀማ መሬት ውሀን በብዛት የማይፈልጉ አንዳንድ መአዛ ካላቸው ተክሎችና እጽዋቶች በተጨማሪ እንደ ወይን፣ ሮማን ያሉ ፍራፍሬዎችና ሌሎች ፍራፍሬዎች ልማት በጣም የተመቸ መሆኑን ፋያድ ተናግረዋል፡፡

ግብጽ የማህብረሰቡን መብቶች የሚያስከብሩ ወይም የትኞቹ ሰብሎችን ማልማትና እንዴት ባለ ተስማሚና ዘላቂ በሆነ ሁኔታ ሀብቶችን ማስተዳደር እንደሚቻል የሚገልጹ የጋራ ተሳትፎን ያካተተ ምንም አይነት ተቋማዊ ፖሊሲ የላትም ብለዋል፡፡

ማንኛውም ኢንቨስተር ከስምምነቱ የላቀውን ጥቅም የማግኘት አጀንዳ ይዞ ቢመጣም፤  መንግስት ደግሞ ከግሉ ሴክተር ጋር የገባውን ስምምነት የራሱን አጀንዳ ለማስፈጸም ጫና መፍጠር አለበት ይላሉ ፋይድ፡፡ ፍላጎቶቹን ለማሳካት ኢንቨስተሮችን የሚያስገድድበት አንዳች አሰራር ሊኖረውም ይገባል፡፡ ኢንቨስተሩ ገንዘብ፣ ባለሞያዎችና ቴክኖሎጂን ያቀርባል፡፡ መንግስት ደግሞ ውሀን፣ ሀይልን፣ ርካሽ የሰው ሀይል፣ ኤሌትሪክ እና ምቹ ሁኔታን ያቀርባል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሀብቶች የህዝብ ናቸው፡፡

ኢንቨስተሮች መሬት ባለቤት በመሆን ያወጡትን ገንዘብ መልሰው ሲያገኙ፤ ለውሀ፣ ለመሬትና ለአየር ንብረት መዘዝ ግን ምንም ነገር አይፈይዱም ሲሉም ፋያድ ይናገራሉ፡፡

‹‹እንደዚያ የሚቀጥል ከሆነ፤ ታዲያ ሀገራችንን ለምን አናከራያትም?›› ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ የመንግስት ምንም አይነት ራዕይ በሌለበት ሁኔታ የኢንቨስተሩ ራዕይ ህዝብ መብቱን እንዲያጣ የሚያደርግ እንደሆነም አክለው ተናግረዋል፡፡

ለባህረሰላጤው ሀገሮች የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ሲባል የግብጽ የተፈጥሮ ሀብቶችን ስለመያዝ የተጠናከረው ይህ ዘገባ የተሳካው በኢንፎናይል እና ፑልቲዘር ሴንተር ድጋፍ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts