ምድረ በዳነት በምድር ላይ በአየር ንብረት እና በሰው ልጆች ተጽዕኖ ውጤት ነው፡፡ ባለፉት አራት አስርት አመታት ምድረ በዳነት በርካታ ገበሬዎች የተሻለ የመኖሪያ ስፍር ፍለጋ ቀዬአቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ያደረገና በሱዳን በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋት ላይ ነው፡፡ ምድረ በዳነት እንዲስፋፋ በማድረግ ረገድ የላቀ አስተዋኦ በማድረግ ከሚጠቀሱት ምክንያቶች አንደኛው ችግሩን ለመቀነስ የሚያስችሉ ድጋፎችን ለህዝቡ መስጠት የሚገባቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት አለመኖር ነው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ውስጥ ድርቅና ምድረ በዳነትን የሚጨምር ስለመሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ለዚህም ነው የአለማችን ሀገሮች ምድረ በዳነትን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በሱዳን ምድረ በዳነት በሀገሪቱ ለሚለማ መሬት ከፍተኛ ስጋት ሆኗል፡፡ ምንም አይነት ድጋፍ የሌላቸው ገበሬዎች ምርጫቸው በተናጥል ምድረ በዳነትን በኑሯቸው ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ መታገል አሊያም በጋራ ችግሩን ለመቀነስ ከመስራት ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው መተው፡፡ ‹‹ይህንን ለውጥ ለመቋቋም በግሌ የምችለውን ሁሉ ብጥርም የበለጠ አስቸጋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ እኔ ኤክስፐርት አይደለሁም፡፡ ነገር ግን መንግስት ሊያግዘን ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ቤተሰቤን ለመርዳት ግብርናውን ትቼ ሌላ ስራ እፈልጋለሁ፡፡ ሌሎች ገበሬ ወዳጆቼም ይህንኑ መንገድ ለመከተል ነው የሚያስቡት›› ሲል በደቡብ ምስራቅ ሱዳን የሚገኘው ገበሬ መሀሙድ ሀሰን ተናግሯል፡፡
ምድረ በዳነትን መከላከል ግንዛቤ፣ ችግሩን ማቅለልና የፈጠራ ስራ
ምድረ በዳነትን መከላከል ግንዛቤ፣ ችግሩን ማቅለልና የፈጠራ ስራ
Like this article?
Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp
Leave a comment
Related Posts
በሞቃታማው የጥቁር አባይ ምንጭ ዙሪያ ለመኖር የሚደረግ የህልውና ትግል
May 8, 2023
በውሀ የበለጸገችዋ ኢትዮጵያ በዝቅተኛ መስኖ ልማት የምግብ ዋስትናዋ ስጋት ገጥሞታል
August 29, 2022