ስለ ደን ዛፍ ምርጥ ዘሮች ሰምተው ያውቃሉ? እርግጥ ነው ምርጥ ዘር ከሰብል እህል ጋር በተያያዘ ይታወቃል፡፡ አሉታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም አለማችን ደን ለማልማት የሚያስችሉ አዳዲስ ግኝቶችን እያስተዋወቀች ነው፡፡ የአየርንብረትን ለማሻሻል ከሚረዱ ከእነዚህ መንገዶችም አንደኛው የደን ዛፍ ምርጥ ዘሮችን መጠቀም ነው፡፡
ይህ ጥረትም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ለውጦችን ማስገኘቱን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ምርጥ ዘሮቹ በኢትዮጵያ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ምን ያህል እገዛ አድርገዋል የሚለው ነው፡፡
ዶክተር ይጋርዱ ሙላቱ በኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት የዛፍ ዘር ቴክኖሎጂ ማስተባሪያ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ ድርጅቱ ከተቋቋመ ጀምሮ የዛፍ ዘር ጥራት ደረጃ በ11 እጥፍ አድጓል፡፡
የተሻሻሉ የዛፍ ዘሮች እገዛ ለደን ልማት
የተሻሻሉ የዛፍ ዘሮች እገዛ ለደን ልማት
Like this article?
Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp
Leave a comment
Related Posts
በሞቃታማው የጥቁር አባይ ምንጭ ዙሪያ ለመኖር የሚደረግ የህልውና ትግል
May 8, 2023
በውሀ የበለጸገችዋ ኢትዮጵያ በዝቅተኛ መስኖ ልማት የምግብ ዋስትናዋ ስጋት ገጥሞታል
August 29, 2022