ኢንጂነር ስመኘውን በመግደል የህዳሴን ግድብ ግንባታ ማቆም እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስታወቁ

ኢንጂነር ስመኘውን በመግደል የህዳሴን ግድብ ግንባታ ማቆም እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስታወቁ

ቆንጂት ተሾመ (ከአዲስ አበባ)

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ኢንጂነር ስመኘው በቀለን በመግደል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ግንባታን ማቆም እንደማይቻል ተናገሩ፡፡
ሐሙስ እለት የአሜሪካን የስራ ጉብኝታቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ቅዳሜ ምሽት በዋሺንግተን ዲሲ ለኢትዮጵያውያን ማሕበረሰብ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው ላይ ባለፈው ሐሙስ ህይወታቸው ያለፈውን ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ታላቅ የሀገሪቱ ጀግና መሆኑን በመግለጽ ያከበሩ ሲሆን፤ ኢንጂነሩን በመግደል የህዳሴ ግድቡን ግንባታ ማቆም እንደማይቻልም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
‹‹ኢንጂነር ስመኘው በቀለን መግደል እንጂ የህዳሴውን ግድብ ማቆም አይቻልም፡፡ ግድቡን ገንብተን እንጨርሰዋለን›› ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ግዙፉ የሀይል ማመንጫ እንደሚሆን የሚጠበቀውን የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክትን ከመጀመሪያው ጀምሮ በማናጀርነት ያገለገሉት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሐሙስ እለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ በጥይት ተመትው ሞተው መገኘታቸው ይታወሳል፡፡ የቀብር ስነ ስርአታቸውም እሁድ እለት ይከናወናል፡፡
ከኢንጂነሩ ሞት በስተጀርባ ማን እንዳለ እስከአሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ በጉዳዩ ላይም የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ይገኛል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 አመት ላይ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 65 ከመቶ በላይ እንደደረሰ ባለፈው መነገሩ ይታወሳል፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts