የጨለለቃ ሀይቅ የመድረቅ ስጋት ገጥሞታል

የጨለለቃ ሀይቅ የመድረቅ ስጋት ገጥሞታል

 

የጨለለቃ ሀይቅ ከዚህ በፊት የሚታወቀው በባህላዊና በሞተር ጀልባዎችም እንዲሁም በእግር እየተዟዟሩ ሲመለከቱት እጅግ የሚደንቅ ማራኪ የመሬት አቀማመጥ ያለው የመዝናኛ ማዕከል በመሆኑ ነበር፡፡

አሁን ግን በውሀ ተሸፍኖ የነበረው 80 በመቶ የሚሆነው የሀይቁ አካል ደርቋል፡፡ የእርሻ መሬት ሆኗል፡፡ በተለይም ደግሞ በሀይቁ የሰሜን እና ምስራቃዊ ክፍል ሰፋፊ የእርሻ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያልተከለከሉ የከብቶች ግጦሽ አካባቢዎችም አሉ፡፡

የጨለለቃ ሀይቅ በቢሾፍቱ ከሚገኙ ስምንት ሀይቆች መካከል አንደኛው ሲሆን፤ ከተማዋን ዙሪያዋን ከከበቧት ተራራዎች ከሚወርድ ከዝናብ ፏፏቴ እንደተሰራ ይታመናል፡፡ ሀይቁ በተለየ ሁኔታ የሚታወቀው ከመስከረም እስከ ህዳር ባለው ጊዜ ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ ወፎችና በምስራቅ አፍሪካ ለመልሶ እርባታ ተሰደው ለሚመጡ የፍላሚንጎዎች መኖሪያ በመሆኑ ነው፡፡ በሀይቁ ላይ እጅብ ብለው የሚበሩና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚኖሩ ፍላሚንጎዎችን ማየት ይማርካል፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts