በታንጋኒካ ሀይቅ የመርከቡን ማረፊያ ቦታ ያሟጠጠው ምንድነው?

በታንጋኒካ ሀይቅ የመርከቡን ማረፊያ ቦታ ያሟጠጠው ምንድነው?

ላለፉት 100 አመታት በታንጋኒካ ሀይቅ ማረፍ ከአለማችን እድሜ ጠገብ መርከቦች መካከል ለምትጠቀሰውና ከ100 አመት በፊት በጀርመን ለተሰራችው ኤም ቪ ሌምባ እረፍት የለሽ የእለት ተእለት ተግባር ነበር፡፡

አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡፡ ያለ ምንም ችግር መርከብ ማቆም የማይቻል ሆኗል፡፡ የሀይቁ መጠን ቀንሷል፡፡ የወደቡ ዳርቻ ድንጋያማ ሆኗል፡፡ የኤም ቪ  ሊምባ የቆሙ መርከቦች እንደነገሩ ነው ውሀ ላይ የሚንሳፈፉት፡፡

‹‹የውሀው መጠን መቀነስ የወደቡ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጥሯል›› ሲሉ የሚናገሩት በኪስዋህሊ የኪጎማ ወደብ ዳርቻ አስተዳዳሪ ሞሪስ ምቺንዱዛ ናቸው፡፡

‹‹በባህር ዳርቻዎቹ ላይ እና በኪጎማ ወደብ አካባቢ የውሃ መጠን መቀነስ ኤምቪ ሌምባ እና ሌሎችም መርከቦች በተረጋጋ ሁኔታ እንዳያቆሙ ተጽዕኖ ፈጥሯል››

lake tanganyika

በዚህም የተነሳ መርከቢቱ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለውን የመሬት ላይ ጉዞን እንደተጋፈጠች ያምናሉ፡፡

የኪጎማ ወደብ የታንጋኒካ ሀይቅ ተፋሰሶች ክልል በታንዛኒያ፣ ብሩንዲ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ዛምቢያ ለሚገኙ ከ30 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የወደብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የታንጋኒካ ሀይቅ በመጠን ከአለም በሁለተኛው ሀይቅ ሲሆን፤ የአለማችን ሁለተኛው ጥልቀት ያለው ሀይቅ ነው፡፡

Kigoma Marine Parking area in Kigoma Port
Kigoma marine parking area in Kigoma Port

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts