ባዮሎጂ እንደሚነግረን ከሆነ ህይወት እርስ በእርስ የመፈላለግ ውጤት ነው፡፡ ማንኛውም ነገር በራሱ የሚቆም አይደለም፡፡ ያለ እጽዋትና እንስሳት መኖር የማይችለውና ተፈጥሮን ሙሉ በመሉ የመቆጣጠር ሀይል ያለው የሰው ልጅ እንኳ የዚህ የመረዳዳት ውጤት ነው፡፡ ይህንን በመረዳትም ኢትዮጵያ አካባቢን ከመጠበቅ አንጻር ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ጥረቶችን የሚያግዝ የአረንጓዴ ልማት መርሀግበሮችን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነች፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ የደን ጥበቃና አያያዝን በሀገር አቀፉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዷን በ2020 አሁን ካለበት አራት ከመቶ ወደ ስምንት ከመቶ ለማሳደግ እየጣረች ነው፡፡ በተመሳሳይ አመት የሀገሪቱን የደን ሽፋን መጠንን ከ15.5 ከመቶ ወደ 20 ከመቶ ለማሳደግም እየተሰራ ነው፡፡