በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ነዋሪ የሆነው ጆሴፍ ጄምስ ቤተሰቡን የሚያተዳድረው በቹንያ ዲስትሪክት በኢቱምቢ ሀምሌት ለወርቅ ማዕን ቆፋሪ ሰራኞች ውሀ በመሸጥ ነው፡፡
የታንዛኒያዋ ንገድድ ከተማ ዳሬሰላም ርቃ ወደምትገኘው የወርቅ አምራቿ አካባቢ የሄደው ከጥቂት አመታት በፊት ሲሆን፤ የተሻለ የስራ ተስፋ ሰንቆ እንጂ እጣፈንታዬ ውሀ መሸጥ ይሆናል ብሎ አልነበረም፡፡
በደቡባዊ ክልል ከፍተኛ ቦታ የምትገኘው በምቤያ ክልል የቹንያ ዲስትሪክት የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ስለገጠማት አሁን ላይ ውሀ በአካባቢው አነስተኛ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ስራ ለተሰማራው ማህረሰብ ውሀ አትራፊ ንግድ ነው፡፡
ጆሴፍ ከተከለከለ የማዕድን ጉድጓድ እያወጣ ከሚሸጠው ውሀ በቀን ከ30.000 እስከ 50.000 የታንዛኒያ ሽልንግ ያገኛል፡፡ በሀምሌት ሀያ ሊትር ጀሪካን በ500 የታንዛኒያ ሽልንግ ይገዛና ብስሌክቱን በመጠቀም ከ70 እስከ 100 እሽግ ቆርቆሮ ውሃ ይይዛል፡፡
‹‹የውሀ ንግድ ህይወቴ ነው፡፡ በዳሬሰላም የሚገኙ ቤተሰቦቼን የምረዳው በዚህ የውሃ ንግድ ነው›› ይላል፡፡
