በቪክቶሪያ ሀይቅ ህገወጥ የአሳ ማጥመጃ መሳሪያዎች ቁጥጥር ፍሬያማ ሆኗል

በምዋንዛ ግዛት ሳንገሬማ ዲስትሪክት በምትገኘው በንያማቶንጎ መንደር በአቻዎቹ ዘንድ ‹‹ዘላዩ›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ስመ ጥሩ የአሳ አጥማጅ ጆሴፍ ካኖድ ምካማ ይገኛል፡፡ ሰውዬው ከአንድ ቢሊዮን የታንዛኒያ ሽልንግ (440.000) በላይ የሚያወጣ የአሳ ማጥጃ መረቦችን እንደያዘ በሕግ አካላት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ምካማ በቪክቶሪያ ሀይቅ መሰል ቁሶችን ለማስወገድ በተካሔደው በመጀመሪያው ምዕራፍ ዘመቻ መንግስት እስከ ማርች 1 ቀን ድረስ ህግ ወጥ አሳ አርቢዎች መሳሪያዎቻቸውን እንዲያስረክቡ የሰጠውን ቀን ገደብ ተላልፎ ነው የተገኘው፡፡ የተወሰኑ መሳሪዎቹን ደግሞ በእርሻ ውስጥና በግንባታ ላይ በሚገኝ ቤት ውስጥ በመቅበርም ደብቋቸው ነበር፡፡

‹‹በአካባቢው መልክዐ ምድር እና ሰብሎችም በማደጋቸው ህገወጥ መሳሪያዎችን በቀላሉ ፈልጎ ማግኘት አስጋሪ ነው›› ይላሉ የሰንገሬማና ቡቾሳ ዲስትክት ኦፕሬሽን ኮማንደር ዌንሴስላወስ ሩሀሳይል፡፡ ህገወጥ ንብረቶች እንዲወረሱ ላስቻለው ቡድንም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሀይቁ ላይ ለቁጥጥር አስቸጋሪ የሆኑ ህገወጥ የአሳ እርባታ ጉዳዮች የሚታወቁ ሲሆን፤ መንግስት በቪክቶሪያ ሀይቅ በካሄደው ኦፕሬሽን አዲስ የአሳ ማጥመጃ መረብ መገኘቱ ታውቋል፡፡

‹‹እነዚህን የአሳ ማጠመጃ መረቦች ዲዛይን በማየት ብቻ ሀይቁን የበለጠ እንደሚጎዱ መናገር ይቻላል›› በማለት ሩሀሳይል ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ መሰል የማጥመጃ መረቦች ወደ ጎን 400 ቀዳዳዎች እና በቁመት ደግሞ 600 ቀዳዳዎች አላቸው፡፡ የተወሰኑ መረቦችም ከተደበቁበት ኮረብታማ ቦታዎች ተገኝተዋል፡፡

ተከሳሹ ግለሰብ ህገ ወጥ መሆኑን እያወቀም ቢሆን ለበርካታ ቀናት በህገ ወጥ አሳ እርባታ ስራ ላይ መሰማራቱን አምኗል፡፡

‹‹እንደዚህ አይት ማጥመጃ መረቦችን ስጠቀም ብዙ ጊዜ ሆኖኛል›› የሚለው ካንዶ ማንኛውም አሳ አጥማጅ ከህግ በላይ እንዳልሆነ በመጥቀስ መንግስት ምህረት እንዲያደርግለት ለምኗል፡፡

የመንግስት ሀላፊዎች መረቦቹ የተቀበሩበትን አምስት ቦታዎችን ለይተው እንዳወቁ ሩሳይል ገልጸዋል፡፡ ሀያ አራት የጀልባ ሞተሮቸም በኦፕሬሽኑ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

በ2003 የአሳ እርባታ ህግ በክፍል 23 መሰረት ህገወጥ የአሳ እርባታ የሚሰራባቸው መሳሪያዎች ሲያዙ እንዲቃጠሉና ጥፋተኛውም ከበድ ያለ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

‹‹በአጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማዳከም ሲባል ጥፋተኛ የሆነ አካል 240 ሚሊዮን የታንዛኒያ ሽልንግ (105.386 ዶላር) በሀያ አራት ሰአት ውስጥ መክፈል ይርበታል›› በማለት የተናገሩት የአሳ እርባታ ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ ማገስ ቡልያ ናቸው፡፡

ይህ የሁለተኛው ምዕራፍ ኦፕሬሽን ዋነኛ አላማ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የሚበቃውን የአሳ ሀብት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያጠፋ ህገወጥ ተግባርን ማስቆም ነው፡፡

Share the Post:

Related Posts