ከአባይ ውሀ ጋር በተያያዘ በቂ መረጃ የማግኘት ችግር የጋዜጠኞችን ብቻ ፈተና አይደለም፡፡ በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ ኤክስፐርቶች፣ ተመራማሪዎችና ፖለቲከኞችም ተመሳሳይ ችግሮች የሚገጥሟቸው ሲሆን፤ የመገናኛ ብዙሀንን ተልዕኮም ፈታኝ አድርጎታል፡፡ ይህ የተገለጸው በሱዳን ካርቱም በመገናኛ ብዙሀንንና ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱ አካላት መካከል ያለው ግንኙነትንና የሳይንሳዊ መረጃ ችግሮችን በተመለከተ በተካሔደ አውደ ጥናት ላይ ነው፡፡
