የቪክቶሪያ ሀይቅ ውሃ ጥራትን የሚያሻሽል የቀላል ፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጀክት በኪሊማሄዋ

የቪክቶሪያ ሀይቅ ውሃ ጥራትን የሚያሻሽል የቀላል ፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጀክት በኪሊማሄዋ

በብዙ ኮረብታማ አካባቢዎች የመጸዳጃ ቤቶችና የቆሻሸ ውሃ ማጣሪያ ታንከሮችን የመሳሰሉ የንጽህና መጠበቂያዎችን አቅርቦትን በሚፈለገው ደረጃ ማሟላት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህም የቪክቶሪያ ሀይቅን ለብክለት በመዳረግ ለምዋንዛ አካባቢ ነዋሪዎች ትልቅ ፈተና ሆኗል፡፡

በመሆኑም የምዋንዛ የገጠር ውሀ አቅርቦትና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ያልተጣራ ውሃ ለሰው ልጆች አገልግሎት ወደ ሚውለው ቪክቶሪያ ሀይቅ ከመግባቱ በፊት የውሃን ንጽህና የሚጠብቅ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክትን አመነጨ፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ የሆነውን ካሊማሄዋ ስታር ቲቪ ከኢንፎ ናይል እና ኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመሆን ጎብኝቷል፡፡

ይህ እውነተኛ ክስተት እውን የሆነው ደግሞ በኮረብታዎች በተከበበችው ‹‹ድንጋያዋማ ከተማ›› በምትባለው ከተማ የተከሰተ ነው፡፡

በኪሊማሄዋ ያልተጣራ ፍሳሽ በተለይ በዝናባማ ወቅት በግልጽ ሲወርድ ማየት ያልተለመደ አይደለም፡፡

‹‹እዚህ አካባቢ መሬቱ ድንጋያማ በመሆኑ በተገቢው ደረጃ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤቶችን መቆፈር በጣም ያስቸግር ነበር፡፡ ስለዚህም ጥልቀት የሌለው የመጸዳጃ ጉድጓድ ለመቆፈር እንገደዳለን ነው፡፡ እናም ዝናብ ሲዘንብ በቀላሉ ሞልቶ ይፈሳል›› ሲል የኪሊማሄዋ መንደር እንደራሴ ፍራንሲስ ሱሙኒ ይናገራል፡፡

ይህንን አስተያየት ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ ራስቱታ ቪሴንት ይጋራል፡፡ ሁኔታው በሽታ እንዲስፋፋ ማድረጉንም ጨምሮ ተናግሯል፡፡

‹‹ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት መጸዳጃ ጉድጓዶቹ በቀላሉ ስለማይከደኑ በፍጥነት ይሞላሉ፡፡ ብዙዎቹን ራሳችን ስለምንቆፍራቸው በሽታም በፍጥነት ነው የሚስፋፋው›› ብሏል፡፡

ቀላል የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ፕሮጀክት አሁን ላይ ለኪሊማሄዋ ፍቱን አማራጭ ሆኗል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት የተነሳም ከ100 በላይ መንደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ነዋሪዎች ግን ምሽቱን ተገን አድርገው ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ አካባቢውን ይበክላል›› ይላል የአካባቢው ነዋሪ ጆኤል ኢብራሂም፡፡

ሌላው የአካባቢው ነዋሪ ጆግራቪታ ዲኦግራቲዋ እንደሚናገረው ከሆነ ከፕሮጀክቱ በኋላ ሁኔታው ከፍተኛ መሻሻል ተፈጥሯል፡፡

‹‹ሌላ የምንሄድበት ስለሌለን የጉድጓድ መጸዳጃዎች በፍጥነት ነው የሚሞሉት፡፡ ስለዚህ የመጸዳጃ ጉድጓዶቹን የሚመጥልን የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት መጠበቅ ይኖብን ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ ችግር የለብንም›› ይላል ዲዮግራቲዋ፡፡

የፕሮጀክቱ ዋኛ አላማ ንጹህ ውሀን ለማሻሻልና ለመጠበቅ ከመሆኑ ባሻገር፤ በምዋንዛ ከተማን አካባቢ ንጽህናንም ለማስተዋወቅ ነው፡፡

Like this article?

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp

Leave a comment

Related Posts