ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ አሁን ድረስ 11. 58 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበርያ ፅ/ቤት አስታወቀ::
የህዝቡን ተሳትፎ የበለጠ ለማጎልበት በመጪው ዕሁድ ግንቦት 19 በሚካሄደውና ለአባይ እሮጣለሁ በሚል ለሚካሄደው ሩጫም 250 ሺህ ሰው ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እስካሁን የ230 ሺው መረጋገጡን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል:: ሩጫው በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የሚካሄድ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ብቻ 90ሺህ ሰው በሰባት ኪሎሜትሩ ሩጫ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቀ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል::