በታላቄ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባና በካይሮ መካከል አለመግባባት ቢኖርም የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር መሀመድ አበደል አቲ አርብ እለት ኢትዮጵያ በመገኘት ከግድቡ ጋር በተያያዘ የቴክኒክ ጥናቶች በሚቀርብበት 18ኛው ዙር የሶስት ሀገሮች ብሔራዊ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ፡፡