ግብጽ ከ53 ሀገሮች የተውጣጡ የውሀ ባለሞያዎች የሚሳተፉበትን ‹‹የካይሮ የውሀ ሳምንት›› ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ ነው፡፡ በፈረንጆቹ ወር ከኦክቶበር 14-18 ቀን በውሀ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውን ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስፖንሰር ማድረጋቸውን የሀገሪቱ የውሀ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር የእቅድ ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት ሰይድ አህመድ አስታውቀዋል፡፡