በአባይ ግድብ ግንባታ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ግብጽ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ውይይት በድጋሚ ፍሬ አልባ መሆኑን የግብጽ ባለስልጣን ማክሰኞ እለት አስታውቀዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ በሶስቱ ሀገሮች የመስኖ ሀብት ሚኒስቴሮች መካከል ለሁለት ቀናት የተደረገው ቴክኒካል ውይይት ያለምንም መፍትሔ መጠናቀቁን የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሆሳም ኤል ኢማም ለአሶሺትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡