ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብን ደህንነት ለመጠበቅ ሱዳንና ኢትዮጵያ ጥምር ወታደራዊ ሀይል ለማቋቋም ተስማሙ፡፡ በሁለቱም ወገን ከፍተኛ የጦር መሪ የሆኑት ከማል አብዱል ማሩፍ አል ማሂ እና ሳሞራ የኑስ በሁለቱ ሀገሮች የመከላከያ ፕሮቶኮል ስምምነትና በሌሎችም የጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ ባለፈው አርብ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡