የፕሮጀክቱ ርዕሰ፤ #EverydayNile፡ የፎቶ ታሪኮች እና ሳይንስ ለውሀ ዲፕሎማሲ
ኢንፎናይል በብሩንዲ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ግብጽ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ውስጥ የሚሰሩ የፎቶግራፍ ባለሞያዎችንና የፎቶ ጋዜጠኞች ከናይል (አባይ) ወንዝ ጋር የተያያዙ ታሪኮች እና ሳይንሳዊ መረጃን በኦንላይን የፎቶ ጋዜጠኝነት ዘመቻ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡
የፎቶ ዘገባ ታሪኮችን ለማዘጋጀት የተመደበው የገንዘብ መጠን 1,000 የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡
የዚህ ፕሮጀክት አላማ በአባይ ተፋሰስ ሀገሮች ያለውን የሰዎችን የእለት ተእለት ህይወት፣ የገጠማቸው ፈተናዎች እና መፍትሔዎችን ጭምር የሚያስቃኙ በርካታ የፎቶ ታሪኮችን ለማዘጋጀት ነው፡፡
የፎቶ ታሪኮቹ በአባይ ተፋሰስ ሀገሮች ዙሪያ ያለውን ህይወት፣ ሰዎች ከአባይ ወንዝ እና ከውሀ ጋር ያላቸውን ትስስር እና የገጠማቸው ፈተናዎች እና መፍትሔዎችን በተመለከተ ግዙፍ ምስል ለመፍጠር ይሞክራሉ፡፡
የፎቶግራፍ ባለ ሞያዎች በኦንላይን ተከታታይ የስልጠና እድሎችን የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ዳራ
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቀሴ ክልከላ በአባይ ወንዝ ላይ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል እየተካሔደ ባሉ ድርድሮች ላይ ብሔራዊ ስሜት የተቀላቀለበት ህዝባዊ ክርክሮች እንዲጨምሩ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ዲፕሎማቶች፣ ጋዜጠኞች እና ተመራማሪዎች ጉዞ ማድረግ፣ መገናኘት እና ከቦታው ሆነው መዘገብ ባለመቻላቸው ሁኔታውን አስከፊ አድርጎታል፡፡ ብሔራዊ ስሜትን ያዘሉ ድምጾች፣ የሚያወዛግቡ ውይይቶች እነ ፍረጃዎችም በማህበራዊ እና መደበኛ መገናኛ ብዙሀኖች እየተሰራጩ ነው፡፡
በመሆኑም አሁን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ በላይ በናይል ተፋሰስ ሀገሮች ዘንድ መግባባት እና ትብብር እንዲኖር የሚያስችሉ ሰፊ እና የተለያዩ አመለካከቶች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክት የምስል እይታን ሐይል በመጠቀም የናይል ወንዝ የጋራ ሀብት መሆኑን የሚያስረዱ የተለያዩ ትንታኔዎችን ያስተዋውቃል፤ ግንዛቤዎች እንዲኖሩም ያደርጋል፡፡
ከቴክኒል እና ሳይንሳዊ መረጃዎች ጀርባ ያሉ ሰዋዊ ታሪኮች ለማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል እንዲደርሱ በማህበራዊ የትስስር ገጾች እንዲተዋወቁ እና እንዲጋሩ ይደረጋል፡፡
የተመረጡ የፎቶ ጋዜጠኞች በኦላይን በሚሰጡ ተከታታይ የፎቶ ጋዜጠኝነት፣ ታሪክነጋሪነት እና የሳይንስ ጋዜጠኝነት ክህሎቶች ስልጠናዎች ላይ እንዲካፈሉ ይጋበዛሉ፡፡ በታላላቅ የፎቶ ባለሞያዎችም ከዲሴምበር 2020 ጀምሮ ሙያዊ እገዛዎችን ያገኛሉ፡፡
ከአመልካቾች የሚጠበቅቸው፤
- ከውሀ ምርምር/ሳይንስ ጋር የተያያዘ የፕሮጀክት ፍሬ ሐሳብ ማዘጋጀት፤
- የፎቶ ታሪክን ለመግለጽ ሰዋዊ እና ታሪክተናጋሪ እይታ አንጻር መጠቀም፤
- መረጃ ሰጪ እና ታሪክነጋሪ በሆኑ የፎቶ መግለጫዎች (ካፕሽኖች) አማካኝነት ሰዋዊ ታሪኮችን ከሳይንስ፣ ምርምር እና ዳታዎች ጋር ማገናኘት፤
- በማህበራዊ የትስስር ገጾች EverydayNile ዘመቻዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን፤ (እባክዎን በኢንስታግራም @everydayafrica, @everyday.nile, @everydayegyt, @ihedelt እና በትዊተር InfoNile ገጾችን ይመልከቱ)
አመልካቾች ከላይ ከተጠቀሱት መካከል የትኛውንም ማድረግ ባይችሉም በምናዘጋጃቸው አውደጥናቶች እና ስልጠናዎች ላይ እንዲያውቁት እናግዛለን፡፡
በዚህ ፕሮጀክት የምንፈልገውን ሐሳብ ለመረዳት ይቻል ዘንድ ለምሳሌነት የቀረቡ ተከታዮቹን የፎቶ ዘገባ ታሪክ ሐሳቦች ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡
- ውጤታማ የውሀ አስተዳደር በተለይም በግብርናው ዘርፍ
- የተሻሻለ የውሀ ማከማቻ አካባቢ አስተዳደር
- ንጹህ የመጠጥ ውሀ እና መሰረታዊ ጤና አጠባበቅ
- ከውሀ ጋር በተያያዘ ስርአተ ጾታ እና አካታችነት
- በድንበር ተጋሪ ሀገሮች እና ማህበረሰቦች መካከል የናይልን በሰብአዊነት እና በፍትሀዊነት ለመካፈል የሚያስችል የውሀ ዲፕሎማሲ
- የውሀ ብክለት
- በእርስዎ ሀገርዎ የናይል ወንዝን በተመለከተ የተሰሩ ስኬታማ እና የፈጠራ ሐሳቦች
- እንደፎቶ ባለሞያ ከናይል ጋር ያለዎትን ቁርኝት የሚገልጽ የግል ታሪክ
ከፕሮጀክቱ የሚጠበቁ ውጤቶች
- በናይል ተፋሰስ ሰዎችንና ከውሀ ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያሳይ የውሀ ታሪኮን ያካተተ አሳማኝ የፎቶ ዘጋቢ የፎቶ ታሪክ
- EverydayNile የማህበራዊ ትስስር ገጽ፣ በኢንፎናይል እና የአፍሪካ ውሀ ጋዜጠኞች ገጽ እና ከሌሎች እንደ ኤቭሪዴይ ግብጽ፣ ኤቭሪዴይ አፍሪካ ካሉ ሰፊ ተደራሽነት ካላቸው የኤቭሪዴይ ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበበር በናይል ወንዝ ላይ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የፎቶ ታሪኮችን ለህትመት ማብቃት፤
- በኔዘርላንድስ እና አፍሪካ ውስጥ በሚዘጋጁ አውደርዕዮች ላይ የፎቶ ባለሞያዎችም የሚገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት የፎቶ ታሪኮች ለእይታ እንዲቀርቡ ማድረግ፤
- በናይል ተፋሰስ ሀገሮች በሚገኙ የህትመት ውጤቶችም ሆነ በኢንፎናይል እና በአፍሪካ የውሀ ጋዜጠኞች ድረ ገጽ ላይ የፎቶ ታሪኮችን ማውጣት፡፡ በምናዘጋጃቸው አውደጥናቶች ላይ በአለምአቀፍ ሚዲያዎች ላይም እንዲሁ ለህትመት እንዲበቁ የዘገባ ታሪኮችን ፍሬ ሐሳብ በማዘጋጀት እገዛ እናደርጋለን፡፡
ታሪኮቹ ከእንግሊዘኛ ውጪ በሆኑ በሌሎች ቋንቋዎችም ሊዘጋጁ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእንግሊዘኛ ተተርጉመው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ይህ አለምአቀፍ የዘገባ ድጋፍ ከናይል የፎቶዎች፣ ታሪኮች እና ሳይንስ ጋር የሚያያዝ የኤቭሪዴይ ናይል ፕሮጀክት አካል ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት በኔዘርላንዱ IHE-Delft Global Partnership for Water and Development የገንዘብ ድጋፍ እና በኢንፎናይል /በአፍሪካ የውሀ ጋዜጠኞች እና በኤቭሪዴይ ናይል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ነው፡፡
ማመልከቻ የሚቀርብበት መንገድ
አመልካቾች ከኖቬምበር 20 ቀን 2020 በፊት infonile2017@gmail.com የኢሜይል አድራሻን በመጠቀም በኢሜይሉ ሰብጀክት ላይ “EverydayNile ስም እና ሀገር” በማካተት ፕሮፖዛላቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ ‘’EverydayNile – ጆን – ኬንያ
- የምታቀርቡትን የፎቶ ታሪክ የሚያስረዳ አንድ ገጽ የፕሮፖዛል መረጃ የሚያስፈልግ ሲሆን፤ ፕሮፖዛሉ በግልጽ የተዋቀረ፣ የታሪኩ ሐሳብ ምን እንደሆነ በግልጽ የሚያብራራ፤ ታሪኩ እንዴት እና የት እንደተሰራ የሚናገር፣ ታሪኩ ለመግለጽ ወይም አስተዋጽኦ ለማበርከት የፈለገው አላማ ምን እንደሆነ፣ ታሪኩን ለማዘጋጀት ያላችሁ ግብአቶች እና ታሪኩ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖን የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
- ስራዎን የሚያሳዩ ስብስብ (የኦንላይን ማስፈንጠሪያውን ወይም በፒዲኤፍ ማቅረብ ይቻላል)
- የኢንስታግራም አድራሻ (ካለ)
- የሚጠቀሙበት ካሜራ እና መሳሪያዎች
- ከ1,000 ዶላር ያልበለጠ የወጪ ዝርዝር (Budget proposal)
- የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅትን የሚገልጽ ሲቪ
ብቁ አመልካቾች ኖቬምበር 22 ቀን ይፋ ይደረጋሉ
የተመረጡ የፎቶ ባለሞያዎች ፕሮጀክቱን እየሰሩ ስራቸውን ለማሻሻል የሚረዱ ቢያንስ ሁለት የኦንላይን ስብሰባዎች እና ሶስት አውጥናቶች ላይ የሚገኙ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ ኮቪድ 19ን በተመለከተ– እባክዎን እነዚህን ድጋፎች በማድረግ እንደምንሰራ ይወቁልን፡፡ ይሁንና በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ደህንነትን በጠበቀ ሁኔታ መዘገብና ፕሮጀክቶችን ማከናወን በሚቻልበት መንገዶች ላይ ከተመረጡ ጋዜጠኞች ጋር የተናጥል እገዛ በማድረግም የምንሰራ ይሆናል፡፡
ኢንፎናይል ድንበር ተሻጋሪ የአካባቢያዊ “ጂኦ” ጋዜጠኞች ስብስብ ሲሆን፤ በአፍሪካ የናይል ተፋሰስ በውሀ ጉዳዮች ላይ አንገብጋቢ ታሪኮችን በዳታ በተደገፈ የመልቲሚዲያ ታሪክነገራ አማካኝነት ሽፋን የመስጠት አላማን ያነገበ ነው፡፡ በተፋሰሱ ሀገሮች ዙሪያ አንገብጋቢ በሆኑ በውሀ እና የአካባቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የመልቲሚዲያ ዳታ ጋዜጠኝነት ፕሮጀክቶች ላይም እንሰራለን፡፡ ቀደም ሲል ከሰራናቸው ስራዎች መካከልም፤ በተፋሰሱ ዙሪያ የተካሔዱ የመሬት ወረራዎች፣ በምስራቅ አፍሪካ ለረግረጋማ መሬቶች መጥፋት የህብረተሰብ ተኮር መፍትሔዎች እና በሱዳን የነዳጅ እና ጋዝ ኢንዱስትሪ በአካባቢ እና በጤና ላይ ያስከተለው ተጽዕኖዎች የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡