ለጋዜጠኞች የዘገባ እድል

ኢንፎናይል (InfoNile) ከሚዲያ ኢን ኮርፖሬሽን (MiCT)/ ዘ ናይልስ (The Niles) ጋር በመተባበር  በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ታንዛኑያ፣ ዩጋንዳ፣ ርዋንዳ፣ ብሩንዲና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋዜጠኞች በምርመራ ላይ ያተኮረ መልቲሚዲያ ጋዜጠኝነት ዘገባዎች ላይ ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። የዘገባ ታሪኮቹም ከአባይ ተፋሰስ ኢኒሺዬቲቭ የውሀ ሀብቶች ስትራቴጂክ ትንተና ጋር ተዛማችና በተፋሰሱ ዙሪያ ያሉ የዳታ ስብስቦችና አመላካች አዝማሚያዎች ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ናቸው። 

amharic 1

የዘገባ ታሪኩ ነጥቦች እንደመነሻ 

በናይል ተፋሰስ ሀገሮች መካከል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ ዋነኛው ጉዳይ እና በጋራ ከሚጠቀሙት የውሀ ሀብቶች ጋር በተያያዘ ያለመግባባታቸው መንስኤ በአብዛኛው በውሀ ፍላጎት እና ባለው የውሀ አቅርቦት መካከል አለመመጣጠን መኖሩ ነው። 

የህዝብ ብዛት እና የሚለሙ አካባቢዎችም እየጨመሩ በመሆናቸው በአባይ ተፋሰስ ሀገሮች የውሀ እጥረት እንደሚከሰት ይገመታል።

ለእነዚህ ፈተናዎች ትኩረት ለመስጠትም የአባይ ተፋሰስ ኢኒሺዬቲቭ Nile Basin Initiative እና አጋሮቹ የሚከተሉትን ፍሬ ጉዳዮች ያካተተ ስትራቴጂያዊ የውሃ ሀብቶች ትንተና Strategic Water Resources Analysis (SWRA)  በማከናወን የመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ላይ ይገኛሉ። 

. የውሀ ፍላጎት እና የተፋሰሱ የውሃ ሀብቶች አቅርቦት ግምት፣

. በብሔራዊ ደረጃ ያሉ ቀጣይ የልማድ እቅዶች፣

. ወደፊት የሚጠበቀውን አለመመጣጠን ላይ ትኩረት ያደረጉ የዳሰሳ ቀመሮች፣

. የፍላጎት ትንበያዎች ሁኔታን እና ለውሀ ቁጠባና የአሰራር እድገት አማራጮችን ለማብራራት የሚያስችል በጥልቀት የተሰራ ልዩ የጥናቶች “የማዕዘን ድንጋይ” የሚሆን ፦ በተረጋገጠ ናሙና፣ ትንተና እና ዳሰሳዎች የሚያቀርብ።

ከዘገባው ትንታኔ ዳታና መረጃን በማቀናጀት ሊሸፈኑ ከሚችሉ የዘገባ ታሪኮች ለአብነት ያህል የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል።

 የመስኖ ብቁነትን ለማሻሻል የሚሰሩ ገበሬዎች፣ የንጥለ ጨው ፕሮጀክቶች፣ ዝናብ መገብ የግብርና አሰራርን የማሳደግ ጠቀሜታ፣ ናይልን ለዳሰሳ/ለንግድ ጥቅሞች ማዋል፣ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን መተግበር፣ ለስርአተ ምህዳር የአካባቢያዊ ፍሰትን መጠበቅ… የሚሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ለዘገባ ታሪኮቻችሁ ተጨማሪ ግብአቶች ሊሆኑ ከሚችሉ ሰነዶች መካከል ይጠቀሳሉ።

and desalination in the Nile Basin

ዘገባዎቹ በጋዜጠኛው ሚዲያ ከቀረቡ በኋላ ለኢንፎናይል ተዘጋጅተው ይቀርባሉ። የተመረጡ ዘገባዎችም The Niles በተሰኘው የህትመት ውጤት ላይ ለህትመት ተስማሚ ሆነው ይቀርባሉ።

እንዴት ማመልከት ይቻላል

ጋዜጠኞች በተናጥል ማመልከት ትችላላችሁ። ነገር ግን በአንድ ሀገር ውስጥ በተለያየ ሚዲያ ወይም በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሀገሮች የሚገኙ ጋዜጠኞች በጋራ ቢያመለክቱ ተመራጭ ነው። በጋራ ለመስራት የምታመለክቱ ከሆነ የቡድኑ አባላትን ሰነዶች ያካተተ አንድ ማመልከቻ በአንድ ኢሜይል አድራሻ ብቻ ተጠቀሙ።

እባክዎትን ማመልከቻዎን እስከ 15 ቀን 2022 ድረስ በinfo@infonile.org ይላኩ።

ማመልከቻው ማካተት ያለበት፦

ልትሰሩት ስላሰባችሁት ዘገባ አንድ ገጽ ዝርዝር ፕሮፖዛል። ፕሮፖዛሉ በግልጽ የተደራጀ፣ የዘገባው ታሪክ ሀሳብ ስለምን እንደሆነ በግልጽ የሚያስረዳ፣ ዘገባው እንዴትና የት እንደሚሰራ፣ ምንን ለመግለጽ እንዳለመ ወይም ምን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት፣ የትኛው ሚዲያ ላይ እንደሚቀርብ (ሚዲያው ተለይቶ መጠቀስ አለበት) እንደዚሁም ምን አይነት ተጽዕኖ ሊያስክትል እንደሚችል የሚገልጽ መሆን አለበት። በተጨማሪም ፕሮፖዛሉ ለመጠቀም የታሰበውን ዳታ ማካተት ይኖርበታል። እባክዎን የመልቲሚዲያ ዘገባውን (ከጸሁፍ ጋራ የፎቶ፣ ድምጽ፣ እና ግራፊክሶችን ያካተተ ዘገባው) እንዴት እንደምትሰሩትም ግለጹልን።

. እንደዚሁም ከ800 ዶላር ያልበለጠ የወጪ ዝርዝር

. የትምህርት እና የስራ ልምድ (ሲቪ)

. ሁለት የስራዎቻችሁ ናሙናዎች (ለህትመት የበቁ ወይም ብሮድካስት የሆኑ ስራዎች በተለይ ሊንክ ያላቸው ተያይዘው ቢቀርቡ ተመራጭ ነው)

. የደጋፍ ደብዳቤ። ደብዳቤው ከተቋምዎ ኤዲተር ሚዲያው ዘገባውን እንደሚያትም/ እንደሚያስተላልፍ የሚገልጽ፣ ዘገባውም በቅርቡ እንደተጠናቀቀውና Pandemic Poachers  የተሰኘው ዘገባን አይነት ሁሉንም ዘገባዎች የሚያካትተው እትማችን ላይ እንዲወጣ የሚፈቅድ መሆን አለበት። 

.የምታቀርቡት የዘገባው ሀሳብ ከቀረበው መረጃዎችና ሌሎች የዳታ ምንጮች በመጠቀም የተቀናጀ ዳታንና የሚታይ ዳታን የማካተት እቅዱን መግለጽ አለበት።

የመጨረሻው ዘገባም ጥልቅ የሆነ የጽሑፍ፣ የቪዲዮ፣ ፎቶግራፍ፣ የድምጽ እና የዳታ ምስል/ ካርታንም ያካተተ የመልቲ ሚዲያ ዘገባ መሆን ይኖርበታል። ለራዲዮ፣ ቴሌቭዥን እና ህትመት ውጤቶች ሊውል የሚችል መሆን አለበት። 

እነዚህ የህትመት ስራዎች ፕሮዲውስ የሚደረጉት በኢንፎናይል እና ሚዲያ ኢን ኮርፖሬሽን ኤንድ ደቼ ከናይል ተፋሰስ ኢንሺዬቲቭ ትብብር እና በአውሮፓ ህብረት እና የጀርመን መንግስት በሚደገፈው Deutsche Gesellschaft fuer Internationale Zusammenarbeit (GIZ) ድጋፍ ነው።

Print Friendly, PDF & Email
Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp