ለጋዜጠኞች የተዘጋጀ የዘገባ እድል

በወረርሽኝ ወቅት የግብርና ውሀ አጠቃቀም እና ችግርን የመቋቋም ብልሀት

ኮቪድ-19 በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገሮች በግብርና የውሀ አጠቃቀም ላይ እንዴት ያለ ጫና አሳድሯል? 

የታሪኩ ዳራ እና የመነሻ ሐሳብ 

ግብርና የአፍሪካ ምጣኔ ሐብት የጀርባ አጥንት ሲሆን፤ በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ገቢ ከ20-30 ያህሉን ይሸፍናል፡፡ 

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ደግሞ አለምአቀፋዊ የጤና ጉዳይ የሆነና በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና ማድረሱን እንደቀጠለ የሚገኝ ነው፡፡ 

በብዙ ሀገሮች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቀነስ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች በግብርናውን ዘርፍ የዋጋ እና አቅርቦት ሰንሰለት ላይ ጉዳትን አስከትለዋል፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ሀገሮች ግብርናን እና የምግብ ግብርናውን ዘርፍ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን በማመን ከሚዘጉ ከሚዘጉ የንግድ ስራዎች እና ከእንቅስቃሴ ገደቦች መካከል እንዳይመደቡ አድርገዋል፡፡ 

ውሃ፣ ምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ደህንነት እርስ በእርስ የተያያዙ ናቸው፡፡ ውሀ ከግብርና ለሚገኝ የምግብ ምርት፣ ለተሻሻለ አመጋገብ እና ለተሻሻለ ንጽህና አጠባበቅ አስፈላጊነቱ የማያከራክር ነው፡፡ ውሀ የእንስሳት ምርትን፣ ምግብ ማቀናበርና ዝግጅትን ይደግፋል፡፡ ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የውሀ ፍላጎት መጨመር፣ መጠነ ሰፊ የውሀ እጥረት፣ ብክለት እና ኮቪድ-19 በውሀ ደህንነት ስነ-ምህዳር እና ዘላቂነት ላይ የአደጋ ስጋት ማስከተላቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ 

በአለም ላይ ከ2.2 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የመጠጥ ውሀ ባጡበት እና 4.2 በላይ ሰዎች የንጽህና አገልግሎቶችን ባላገኙበት ሁኔታ ኮቪድ-19 የንጹህ መጠጥ ውሀ እና የንጽህና አጠባበቅ አስፈላጊነት ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል፡፡ የውሀ፣ ጽዳት እና የንጽህና አጠባበቅ (WASH) እና ውሀ ለምግብ ምርት አስፈላጊነታቸው የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ብቻ አይደለም፡፡ ለማህበረሰቡ ችግር መፍቻ መፍትሔንም ለመገንባትም ጭምር ነው፡፡ ያለ ንጹህ ውሀ እጅ መታጠብ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ያለ ውሀ የምግብ ደህንነትን ማረጋገጥም የሚሳካ አይደለም፡፡

በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ባሉ አዳጊ ሀገሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የምግብ ደህንነት እና አኗኗር ላይ ከፍተኛ የሆነ ስጋትን አሳድሯል፡፡ ምክንያቱም የግብርና አመራረት ዘዴዎች በሰው ሀይል ጉልበት ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው እና የማክሮ ኢኮኖሚውን ጉዳት ለመቋቋም አነስተኛ አቅም በመኖሩ ነው፡፡ 


ለጋዜጠኞች የዘገባ እድል 

በአባይ ተፋሰስ ሀገሮች የምትገኙ ጋዜጠኞች ኮቪድ-19 በገበሬዎች በመስኖ እና ውሀ አቅርቦት እና አጠቃቀም ላይ ያደረሰው ተጽዕኖዎችን በተመለከተ ጥልቅ የሆነ ዘገባ ለማዘጋጀት የሚያስችል የስራ ሐሳብ እንድታቀርቡ ኢንፎናይል ይጋብዛል፡፡ 

ይህ በቡድን የሚዘጋጅ ዘገባ ነው፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኞች የሥራ እቅዳችሁን ጥንድ ወይም ሶስት ሆናቹ በጋራ እንድታቀርቡ እንጋብዛለን፡፡ ጋዜጠኞች በተለያየ ሀገር ሆናችሁ በተመሳሳይ ታሪክ ላይ ለመስራት ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ በአንድ ተመሳሳይ ሀገር የምትገኙ ጋዜጠኞችም በቡድን የስራ እቅችሁን ማቅረብ ትችላላቹ፡፡ በቡድን የምታመለክቱ ጋዜጠኞች በተለያየ ቋንቋዎች በሚዘጋጁ የሚዲያ አይነቶች የምትሰሩ ልትሆኑም ትችላላቹ፡፡ ለምሳሌ በሀገር ውስጥ ራዲዮ ላይ የሚሰራ ሪፖርተር ከቲቪ ወይም ጋዜጣ ላይ ከሚሰራ ጋዜጠኛ ጋር በመጣመር ለመስራት ማመልከት ይቻላል፡፡

ኮቪድ-19 ገበሬዎች ለመስኖ የሚጠቀሙት ውሀ ላይ እንዴት ያለ ተጽዕኖ ፈጥሮባቸዋል? ወረርሽኙ ባስከተለው ክልከላዎች የተነሳ ገበሬዎች በመስኖ ለማጠጣት የሚጠቀሙባቸው የቴክኖሎጂዎች ቁሳቁሶችን፣ ግብአቶችን የጥገና አገልግሎቶችን የማግኘት ተግዳሮቶች ገጥሟቸዋል? ወይም ደግሞ ገበሬዎች በታሪፍ፣ በገበያ አቅርቦት እጦት፣ በሰው ሀይል እጥረት እና በሌሎች የኢኮኖሚ መንስኤዎች የተነሳ የኢኮኖሚ ችግራቸው ጨምሯል? በመስኖው ዘርፍ የተፈጠሩ አዳዲስ እድሎችና የፈጠራ ውጤቶችስ ምንድን ናቸው?

የስራ እቅዶቹ በተጨማሪም በግብርና የውሀ አቅርቦት፣ ጽዳት እና ንጽህና አጠባበቅ ((AgriWASH) ላይም ምርመራ የሚያደርጉ እንዲሆኑ እንጋብዛለን፡፡ ጥሩ የጽዳት እና ንጽህና አጠባበቅ ለመልካም ጤንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የግል ልማዶች ናቸው፡፡ በግብርናው ደግሞ፤ የግብርና እርሻ ንጽህና አጠባበቅ ማዕከል የሆኑት፤ ገበሬዎች፣ የግብርና ሰራተኞች እና ሌሎች የምግብ ቢዝነስ አንቀሳቃሾች ሲሆኑ፤ ንጹህና ደህነቱ የተጠበቀ እና ለተረፈ ምርቶች አዋጪ የሆኑ የውሀ ማከሚያ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም፤ ምንም እንኳ የግብርና ኬሚካል እና ጸረ-ተህዋስ ኬሚካሎችን በምግብ አመራረት ዘዴዎችን በጥንቃቄና በሀላፊነት መጠቀም ቢቻልም እንኳ፤ የእንስሳትና አሳ ማርቢያ የሚለማ ውሀን የማስወገድ አሰራር እና አያያዝ አላማው በሽታዎችን መቀነስንና ጸረ ተህዋስን መቋቋም መሆን አለበት፡፡  

ጋዜጠኞች በአባይ ተፋሰስ ባሉ ሀገሮች ላይ ኮቪድ-19 በግብርና ውሀ አጠቃቀም ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ ላይ ያተኮረና ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ የመልቲሚዲያ ዘገባ እንድታዘጋጁ እንፈልጋለን፡፡

የስራ እቅዳችሁ ተቀባይነት ካገኘ ኢንፎ ናይል በሚያዘጋጀው የዳታ ጆርናሊዝም ስልጠና ላይ የመካፈል እድሉን እንድትጠቀሙ እናደርጋለን፡፡ ዘገባችሁን ግራፊክስ፣ ዳታ ቪዝዋላይዜሽን (Data Visualization) እና ካርታን በመጠቀም የምታጠናቅሩበት እገዛንም ታገኛላችሁ፡፡

የዘገባዎቹ ታሪኮች በማንኛውም ቋንቋ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በእንግሊዘኛ ቋንቋም ሊተረጎሙ ይገባል፡፡

ለስራው የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ይህን ያህል ተብሎ የተወሰነ ገደብ ባይኖረውም ወደ 1,000 ዶላር አካባቢ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ በጣም ከፍተኛ የሆነ የምርመራ ስራዎችን የሚፈልግና ብዙ ጋዜጠኞች በቡድን የተሳተፉበት ከሆነ የገንዘቡ መጠን በተወሰነ ደረጃ ሊጨምር ይችላል፡፡ እባክዎትን ለስራው የሚያስልገውን ያህል የገንዘብ መጠን ብቻ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡


ለዘገባ ያዘጋጃችሁትን ሐሳብ ፕሮፖዛሉን እስከ ጁላይ 31 ድረስ info@infonile.org መላክ ትችላላችሁ፡፡

በማመልከቻችሁ ላይ የምታቀርቡትን የዘገባ ሐሳብን በተመለከተ ከአንድ ገጽ ያልበለጠ ማብራሪያ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ለመስራት ያሰባችሁት ታሪክ ሐሳብ በግልጽ የተጠናቀረ፣ እንዴትና የት ሊሰራ እንደሚችል፣ ምን አይነት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው፣ በየትኛው ሚዲያ እንደምታቀርቡት (በግልጽ የሚጠቀስ የሚዲያ ተቋሞች) እና ከዘገባው ታሪክ የሚጠበቀው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ ማካተት ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሮፖዛሉ ግብአት የሚያደርገውን የዳታ እቅዱ ምን እንደሆነ ማካተት አለበት፡፡ በምታቀርቡት ዘገባ ላይ ምን አይነት መልቲሚዲያ (የቪዲዮ፣ ፎቶዎችና፣ የድምጽ እና የግራፊክሶች ግብአቶችን ከጽሁፍ ጋር) ለመጠቀም እንዳሰባችሁም እንድትልጹልን እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከማመልከቻችሁ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ያለባችሁ፤ 

  • አስፈላጊው የባጀት ፕሮፖዛል፤
  • ሲቪ፤
  • ሁለት የናሙና ስራዎችን / የታተሙ ወይም ብሮድካስት የሆኑ ስራዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ስራዎቹ የታተሙ ከሆኑ ሊንኩን ብቻ ማስቀመጥ ይበቃል፡፡
  • ከሚሰሩበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤንም ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ ደብዳቤው የሚዲያ ተቋሙ የሚሰሩትን ዘገባ ለማተም ወይም ለማስተላለፍ ፈቃደኛ መሆኑን የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

ስለ ኮቪድ 19 ያታውሱ፤  እባክዎትን እንደዚህ አይነቱን እድሎችን መስጠታችንን እንደምንቀጥል ያስታውሱ፡፡ ይሁንና በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ደህንታቸውን ጠብቀው ከሚሰሩ የተመረጡ ጋዜጠኞች ጋር በተናጥል መስራታችንን የምንቀጥል መሆናችንንም እናስታውቃለን፡፡

Share on Facebook
Share on Twitter
Share on Linkedin
Share on Pinterest
Share on Telegram
Share on WhatsApp