ኢንፎናይል InfoNile የናይል ተፋሰስ ውሀን በመጠቀም በተፋሰሱ ሀገሮች የሚገነቡ የሀይል ማመንጫ ግድቦች የሚሰጡትን ጥቅምና ጉዳቶች በተመለከተ ጥልቅ የሆነ የምርምራ ዘገባዎችን እንዲያቀርቡ በተፋሰሱ ሀገሮች የሚገኙ ጋዜጠኞችን ይጋብዛል፡፡
የዘገባው መነሻ ሐሳብ
በቀጣዮቹ አመታት በመላው አለም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ግድቦችን የመገንባት እቅድ አለ፡፡ ከእነዚህ መካከልም የተወሰኑት በናይል ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ ናቸው፡፡ ግድቦች በእርግጥ የታዳሽ ሀይል መገኛ ምንጭ ናቸው፡፡ ነገር ግን ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ግድቦቹ በሚገነቡበት ቦታ ባሉት አካባቢና በህብረተሰብ ክፍሎች ላይም አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ እነዚህ ተጽዕኖዎች በናይል ተፋሰስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ2700 አመት ጀምሮም ይገኛሉ፡፡
የናይል ተፋሰስ ኢኒሺየቲቭ Nile Basin Initiative በተፋሰሱ ውስጥ ያለው የሀይል ማመንጫ አቅም ከ20 ጊጋ ዋትስ በላይ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ይሁንና ከዚህ ውስጥ አሁን 26 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው መጠቀም የተቻለው፡፡ በተመሳሳይ የህዝብ ብዛት ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፤ በ2035 የሚኖረው የሀይል ፍላጎት አሁን ካለው በ300 በመቶ ያህል እንደሚልቅ ተመልክቷል፡፡
ግድቦች የሀይል አቅርቦትን ለማሳደግ፣ ለምጣኔ ሀብት እድገት፣ ለስራ እድል፣ ለጎርፍ መከላከል እና ለመስኖ ስራ ጥቅም የሚሰጡ ቢሆኑም፤ ስነ ምህዳሩን በማቃወስ፣ ሰዎችን ከአካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ፣ ጎርፍ እንዲጨምር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት እና የስራ እድል እንዲጠፋ በማድረግም አስተዋጽኦ አላቸው፡፡
የዘገባው ታሪክ ለቀጣዮቹ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ እንዲሆን ይጠበቃል
- የተገነቡ ግድቦች ህብረተሰቡ፣ መንግስት፣ ድጋፍ አድራጊዎች የሚጠብቁትን ግምት አሳክተዋል?
- ከግድቦቹ ይጠበቅ የነበረውና ያልተጠበቀው ተጽዕዎች ምን ነበሩ? እንዴትስ ተግባራዊ እየሆኑ ይገኛሉ? ችግሮቹን ለመቅረፍ የተገቡ ቃሎች ተግባራዊ ሆነዋል?
- ቀደም ሲል ከተገነቡ ግድቦች ምን መማር ተችሏል?
- ግድቦች ሙሉ በሙሉ ከተጽዕኖ ነጻ የሀይል መገኛ ናቸው? ሁልጊዜም በአካባቢ ጥበቃ እና ሀይል መካከል ተቃራኒ ናቸው ወይስ ስነ ምህዳሩን በመደገፍ በአርአያነት የሚጠቀሱ ሀይድሮ የሀይል ማመንጫ ግድቦች አሉ?
- ግድቦች መጀመሪያ ይሰጣሉ የተባሉትን ጥቅሞች እየሰጡ ነው ወይስ እርባና ቢስ የሀገሮች ምልክቶች ሆነው ቀርተዋል?
- የአየር ንብረት ለውጥ በግድቡ ላይ የፈጠረው ተጽዕኖስ ምንድነው? የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖንና ተያያዥ ጉዳቶችን በመቋቋም ረገድ ግድቡ ሀገሪቱን በምን መልኩ እያገዘ ነው?
የግድብ ግንባታ ገንዘብ ድጋፍ እና ፖለቲካው
- ግድቦች በድንበር ተሻጋሪ ፖለቲካው ላይ የፈጠሩት ተጽዕኖ ምን ይመስላል? በናይል ተፋሰስ ውስጥ በአርአያነት የሚጠቀሱ አሉ?
- አለምአቀፍ ለጋሾች ፍላጎት እና ሒደት ምንድናቸው?
- ሀገራት በሀገር ውስጥ አቅም የግድቦች ግንባታ ላይ ለማቀድ እና ለማስተዳደር አቅም ግንባታ ላይ እየሰሩ ነው? በግድቦች ዲዛይን፣ ግንባታ እና አስተዳደር ላይ የሚመረጡ ድርጅቶች ከጂዮ-ፖለቲካው ጋር ትስስር አላቸው?
- ግድቦች ከተሰሩና ውሀ ከሞሉ በኋላ በክልሎች፣ በሀገር ውስጥ፣ በአህጉራዊና በአለምአቀፋዊ ፖለቲካው ላይ የፈጠሩት ተጽዕኖ ምን ይመስላል?
እንዴት ማመልክ ይቻላል
ዘገባውን ለመስራት ጋዜጠኞች በተናጥል ማመልከት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ሀገሮች የሚገኙ ጋዜጠኞች ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው በጋራ ሆነው እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡ ቅድሚያ የማግኘት እድልም ይኖራቸዋል፡፡ ከሌሎች ጋር በጥምረት የሚያመለክቱ በአንድ የኢ-ሜይል መልዕክት ላይ ብቻ የሁሉንም የቡድን አባላት አስፈላጊ ሰነዶችን በማያያዝ ማመመልከት ይችላሉ፡፡
ማመልከቻውን በኢንፎናይል ኢ-ሜይል info@infonile.org ከሴፕቴምበር 10 ቀን 2021 በፊት እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
- በማመልከቻው ላይም ምን ለመዘገብ እንደተፈለገ የሚገልጽ አንድ ገጽ ፕሮፖዛል ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ፕሮፖዛሉ በግልጽ ስለምን መስራት እንደታቀደ፣ ዘገባው የት እንደሚሰራ፣ ምን አይነት እውነታን ለማሳየት እንደሚፈልግ፣ ዘገባው የትኛው ሚዲያ ላይ እንደሚቀርብ፣ ዘገባው ሊፈጥር የሚችለውን ተጽዕኖዎች በተመለከተ ማካተት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የመረጃ ዳታዎችን እንዴት ለማካተት እንዳቀደ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ የመልቲሚዲያ ዘገባውን (የቪዲዮ፣ የፎቶዎች፣ የድምጽ እና የግራፎች መረጃን ከጽሑፍ ጋር ያካተተ) እንዴት ለመስራት እንደተዘጋጀም ማሳወቅ ይጠበቃል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከ1000 ዶላር ያልበለጠ የበጀት ፕሮፖዛልን ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
- የጋዜጠኛው ሲቪ
- ከዚህ በፊት የተላለፉ /የታተሙ/ ማሳያ ስራዎች (ሊንኮቹን ማስቀመጥ) ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡
- ከምትሰሩበት ተቋም ወይም ኤዲተር በኩል የሰራችሁት ዘገባ እንደሚተላለፍ/እንደሚታተም እናም የመጨረሻውን ዘገባም Pandemic Poachers በተሰኘው የቅርብ ጊዜ ፕሮጀክታችን ላይ የምናቀርበው መሆኑን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
የዘገባ ፕሮፖዛላችሁ የሀይል ማመንጫ ግድቦች በተለያዩ ዘርፎች ወይም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማጣመር የዳታ ትንተና እና visualization ለመስራት እንደሚችል ማሳየት አለበት፡፡ ለአብነትም ዘገባው በሀይል በግብርና፣ በምጣኔ ሐብት ፣ በምግብ ደህንነት፣ በውሀ በመሬት፣ በአደጋዎች፣ በአኗኗር ሁኔታ እና መሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ተያያዥነት ያለው መረጃን ማጣመር አለበት፡፡ ካርታዎችንና ቪዥዋላይዝ የሆኑ ታሪኮችን የምንሰራባቸው ጂኦ “Geo-coded” ወይም geographical data ይበልጥ ተመራጭ ናቸው፡፡ ይሁንና ሌሎች ተአማኒነት ያላቸው ዳታዎችን ማቀናጀትና መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
የዘገባው የመጨረሻ ውጤት የጽሑፍ፣ ቪዲዮ፣ የፎቶግራፎች፣ የድምጽ፣ እና የዳታ መረጃዎችን/ ካርታዎችን ያካተተ ጥልቅ የመልቲ ሚዲያ ዘገባ In-depth Multimedia story መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በራዲዮ፣ ቴሌቭዥን፣ እና ህትመት ውጤቶች ላይ የሚቀርብ መሆን አለበት፡፡